እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሳችሁ!
ጾሙ የካቲት 9 ይገባል
#የዐቢይ_ጾም_ሳምንታት_ስያሜዎች
፩ኛ)የመጀመሪያው እሑድ(ሳምንት)፥ #ዘወረደ (ሙሴኒ፣ ጾመ ሕርቃል) ይባላል፡፡ አምላክ ከሰማይ መውረዱን፣ ሰው መሆኑንና ነገረ መስቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡
፪ኛ. የሁለተኛው እሑድ፥ #ቅድስት ይባላል፤ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው
፫ኛ. የሦስተኛው እሑድ፥ #ምኲራብ ይባላል፤ በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኲራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡
፬ኛ. ዐራተኛው እሑድ፥ #መፃጉዕ ይባላል፤ ድውያንን መፈወሱን፣ ዕውራንን ማብራቱን፣ የሚያነሣ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፭. አምስተኛው እሑድ፥ #ደብረ_ዘይት ይባላል፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሁኖ ያስተማረው ትምህርት፥ የዳግም ምጽአትን ነገር የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፮. ስድስተኛው እሑድ፥ #ገብርኄር ይባላል፡፡ የጌታውን ብር ተቀብሎ ያተረፈበት፣ በጌታውም ፊት ምስጋናን ያገኘው ሰው ታሪክ ይዘመርበታል፡፡
፯. ሰባተኛው እሑድ፥ #ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ እየመጣ ይማር የነበረውን የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፰. ስምንተኛው እሑድ፥ #ሆሣዕና ነው፡፡ ጌታ በአሕያ ውርንጭላ ሆኖ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡
፨ ከሠርክ ሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ያለው ሰባት ቀን #ሕማማት ይባላል:- የጌታን መከራና ስቃይ እንዲሁም ሞት የምናስታውስበት ሳምንት ነው ፡፡
#የዐቢይ_ጾም_ሌሎች_መጠሪያ_ስያሜዎች
፩. ዐቢይ ጾም ይባላል፤
፪. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤
፫. የካሣ ጾም ይባላል፤
፬. የድል ጾም ይባላል፤
፭. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፤
፮. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፤
፯. የቀድሶተ ገዳም ጾም፤
፰. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፤
፱. የሥራ መጀመሪያ ጾም፤
፲. ጾመ አርብዓ ይባላል፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤23
#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ
ጾም ማለት፤
፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።
፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።
፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤
ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤
ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤
አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤
እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤
አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤
….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም።
ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው።
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤
፩ኛ. #ዘወረደ_ይባላል፤
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ፤
ወሚመ ኢያእመሩ፤
እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ፡፡››
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ እመልዕልተ ኵሉ››፡፡
«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/
፪ኛ. #ጾመ_ሕርቃል_ይባላል፡፡
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው; እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡
፫ኛ. #ሙሴኒ
የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡

❤16
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን !!
በሀገር ውስጥና በልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፡-
በመዋዕለ ጾሙ ሰይጣንንና መስሓቲ ተግባሩን ድል በማድረግ ድል እንድንነሣ ያደረገን ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ኣርብዓ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
‹‹ወልበሱ ወልታ እግዚአብሔር በዘትክሉ ተቃውሞቶ ለመናግንተ ሰይጣን፤ የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ጋሻ ልበሱ›› (ኤፌ.፮፥፲፩)፤
እኛ ሰዎች ቀዋሚና ምሕረት የለሽ ጠላት እንዳለን እናውቃለን፤ ይህ ጠላት ሰይጣን፣ ዲያብሎስ፣ክፉ መንፈስ፣ ርኩስ መንፈስ ተብሎ እንደሚጠራም ቅዱስ መጽሓፍ ነግሮናል፤ዲያብሎስ ከጥንት ጀምሮ በክፉ ሽንገላው ሰዎችን ሲጥል ኖሮኣል፤ አሁንም ከዚህ ክፉ ተግባሩ ኣልታቀበም፤ ለወደፊቱም ይታቀባል ተብሎ አይጠበቅም፤ ጌታችን በዚህ ዓለም በሥጋ በተገለጠ ጊዜም ይህ ክፉና ርኩስ መንፈስ በሽንገላ ቃሉ ጌታችንን ሊጥል ያልተሳካ ሙከራ አድርጎኣል፡፡
ርኩሱ መንፈስ ጾም መንፈሳዊ ኃይልን እንደሚያቀዳጅ ያውቃልና፣ ጌታችን ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት መጾሙን ተመልክቶ፣ በሽንገላ ቃሉ ሊጥለው ሙከራ አድርጎኣል፤ ይህንን ያደረገበት ዋና ምክንያትም ጾም መንፈሳዊ ኃይል መሆኑን በውል ያውቃልና በጾም ኃይል ከእጄ ያመልጣል ብሎ በማሰቡ ነው፤ ይሁን እንጂ ሰይጣን የሰውን ደካማ ጠባይ በመጠቀም ያስለመደው ሽንገላ፣በተዋሕዶ ሰውም አምላክም በሆነው ጌታችን ላይ ሊሳካለት ባለመቻሉ ተሸንፎና ተስፋ ቆርጦ ሊሄድ ችሎአል፡፡
የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!
የጌታችን ድል አድራጊነት ያስተማረን ብዙ ነገር አለ፤በዚህ ተግባራዊ ትምህርቱ እኛ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስን ድል የምናደርግባቸው ሁለት መሣሪያዎችን በዋናነት አሳይቶናል፤ እነሱም የእግዚአብሔርን ጋሻ መልበስና በጾም መንፈሳዊ ኃይልን መቀዳጀት ናቸው፡፡
ሁሌም እንደምንማረው በውስጣችን ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ኣሉ፤ እነሱም ፍትወተ ሥጋና ፍትወተ መንፈስ ናቸው፤ እነኝህ ሁለት ነገሮች ኣንዱ ላንዱ ፍጹም ተቃራኒ መሆናቸውን ቅዱስ መጽሓፍ እንዲህ በማለት ያስረዳል፡-‹‹ እስመ ሥጋኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ መንፈስ፤ ወመንፈስኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ ሥጋ፤ ወይትኣበዩ በበይናቲሆሙ ከመ ኢትግበሩ ዘትፈቅዱ፤ ወባሕቱ እብለክሙ በመንፈስ ሑሩ ወፍትወተ ሥጋክሙ ኢትግበሩ፣ማለትም ሥጋ መንፈስ የማይወደውን ይወዳል፤ መንፈስም ሥጋ የማይወደውን ይወዳል፤ እርስ በርሳቸውም ይቀዋወማሉ፤ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ ኣትችሉም፤ ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ምኞት ግን ከቶ አትፈጽሙ››(ገላ.፭÷፲፮‐፲፰)፡፡
እነኝህ የውስጣችን ጠባዮች በዚህ ደረጃ እርስ በርስ የሚቃረኑ መሆናቸው ለምናስተውላቸው በግልጽ የሚታወቁ ናቸው፤ ከዚህ አንጻር ሰይጣን ይህንን ክፍተት ተጠቅሞ የሥጋችንን ፍላጎት እንድንከተል ይገፋፋናል፤ መሳሪያዎቹ ደግሞ ፍቅረ መባልዕት፣ ፍቅረ ንዋይና ፍቅረ ሢመት ናቸው፤ ይህም በመሆኑ ነው ሰይጣን፣ በነዚህ ጌታችንን ሊሸነግለው የሞከረ፤ይሁንና ጌታችን እነኝህን የሽንገላ መሣሪያዎች ሰባብሮ ጥሎኣቸዋል፤የጣላቸውም በጾምና በእግዚአብሔር ቃል ነው፤
ጾም መጾም ማለት ከፍቅረ መባልዕት፣ ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ፍላጎት ጨርሶ መራቅ ማለት ነው፤ ይህንን ኣደረግን ማለት ደግሞ ሥጋችን የማይወደውን፣መንፈሳችን ግን የሚወደውን ነገር ኣደረግን ማለት ነው፤ ይህ ሲሆን ሰይጣን ከሰረ፤ ድልም ሆነ ማለት ነው፤ በዚህ መንፈሳዊ ኃይል ዲያብሎስ ተሸንፎና ተስፋ ቆርጦ ይሄዳል፡፡
ከዚህ ኣኳያ እኛም በቃለ እግዚአብሔር እየተመራን የምንጾምበት ምክንያት የሥጋችንን ፍላጎት በመግራት ለነፍሳችን ፍላጎት ለማደርና በዚህ ኃይለ መንፈስ ሰይጣንን በማሸነፍ የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ለመሆን ነው፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!
የጾም ዋና ዓላማ ሥጋዊ ፍላጎትን መግራት፣ በምትኩ ደግሞ መንፈሳዊ ፍላጎትን ማጐልበት እንደሆነ ተነግሮናል፤ በመሆኑም ይህንን መርሕ ጠብቀን መጾም ግዴታችን ይሆናል፤ ዛሬ ባለንበት ዓለም ሥጋዊ ፍላጎታችን ያየለበት፣መንፈሳዊ ፍላጎታችን ግን የተዳከመበት ዘመን ላይ እንገኛለን፤ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከኣንድነት ይልቅ መለያየት፣ ከመራራት ይልቅ ጭካኔ፣ ከእምነት ይልቅ ክሕደትና ኣስመሳይነት በዓለማችን ላይ የበላይነቱን ይዞ መገኘቱ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡
ይሁንና ዓለም ቢሰማም ባይሰማም፣ ሓቁም ጠቃሚውም የመንፈስን ፍላጎት ማጐልበት ስለሆነ የመንፈስ ፍሬዎች የሆኑትን ማለትም፣ ፍቅርን ሰላምን፣ ኣንድነትን፣ ርኅራኄንና፣ ሃይማኖትን፣ ማስፈን ምርጫችን ልናደርግ ይገባል፤ ቤተክርስቲያንም እንድንጾም የምታስተምረን እነዚህን ለመተግበር ጾም ፍቱን መሳሪያ ሆኖ ስለሚገኝ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር የጾም ዓላማውና ግቡ ጽኑዕ ሃይማኖትን፣ እውነተኛ ፍቅርን፣ ዘላቂ ሰላምን፣ ልባዊ ኣንድነትን፣ የማይናወጽ ፍትሕንና እኩልነትን፣ ወሰን የሌለው ርኅራኄን በውስጣችን፣ ብሎም በዓለማችን ማሥረጽ እንደሆነ በውል ተገንዝበን ጾሙን መጾም ይገባል፤ልንለብሳቸው የሚገቡ እነዚህ የመንፈስ ፍሬዎች የእግዚአብሔር ጋሻዎች ናቸውና፡፡ ይህንን ካደረግን እንደ ጌታችን የሰይጣንን ሽንገላ በጣጥሰን በመጣል በኣስተማማኝ ሁኔታ ድል ማድረግ እንችላለን፤ የተጠራነውም ለዚሁ ነው፡፡
በመጨረሻም፡-
የሕዝባችንና የሀገራችን የራስ ምታት ሆኖ የሚገኘውን ያለመግባባት ዝንባሌ ለመቅረፍ ከልብ በመጸለይ፣ እንደዚሁም የተራቡትን በማጒረስ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ፍትሕ ለተነፈጉትም እውነተኛ ፍትሕን በመስጠት፣ መዋዕለ ጾሙን እንድንጾመው በእግዚአብሔር ስም ኣባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ”
ወስብሓት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፡፡
የካቲት ፱ ቀን ፳፻፲፰
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

❤22🙏8👍1
‹‹የአካፋው ሚካኤል››፤ የካቲት_12
ለሁለተኛ ጊዜ ሃገራችንን ልትወር በመጣችው የጣሊያን የጦር ሹም የነበረውን ግራዚያኒን ለመግደል ጀግኖቹ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጣሉት አደጋ ግራዚያኒ በመቁሰሉና አመራሮቹ በመሞታቸው የተቆጣው የጣሊያን ጦር በአዲስ አባባ በየካቲት 12/1929ዓ.ም. ለቅዱስ ሚካኤል ወርኋዊ በዓል በየቤተ ክርስቲያኑ የተገኙትን (ለምጽዋት የተሰበሰቡትን ጨምሮ)ና በየቤቱ በመግባት 30 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ በአካፋ ጭምር እንደ ቅጠል አረገፏቸው፤ 30ሺህ ሰማዕታት በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ከጥቂት ናት በኋላም የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኰሳትን አርበኞችን ደብቃችኋል በሚል በተቀደሰው ስፍራ ተረሸኑ፡፡ በዚህም ምክንያት ጣሊያን ይህን አሰቃቂ ግፍ ስትሠራና የሰማዕታቱን የከበረ አካል በአካፋ በመሰብሰቧ ‹‹የአካፋው ሚካኤል›› በሚል መጠሪያ ይጠራል፡፡ በተለይም በ6 ኪሎ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ የቅዱስ ሚካኤል ታቦተ ሕግ ወጥቶ በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡ (እናት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም ቢሆን የሃገርና የቤተ ክርስቲያን ባለውለታዎችን አትዘነጋምና!!!!)
(እናቶቻችንና አባቶቻችን እንደነገሩን በቀጨኔ የሚገኙ አያቶቻችን የተሠዉና ግማሾቹም ይህንን ዜና ሲሰሙ ወደ 6 ኪሎ ከመሄድ የተመለሱ እንዳሉ ልብ ይሏል)፡፡

❤13
#ለየካቲት_12_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_ማስታወሻ
የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ኢትዮጵያን ልትቀራመት ወሰኑ፡፡ ለዚህም ውሳኔ ያደረሳቸው ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላው አባ ማስያስን(የጣሊያ ንጉሥ የቪክቶሪ ንስሐ አባትን ቀድሞ በትንሹ ራስ ዐሊ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው) በአፄ ቴዎድሮስ ተባሮ፤ እንደገና በአፄ ዮሐንስ ዘመን ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበር፤ አሁንም መልሰው አፄ ዮሐንስ ሲያብርሩት ለጣሊያን መንግሥት የኢትዮጵያን ልዩ መልክአ ምድሮችና በዓለም ላይ ልዩ ሃገር መሆኗን 2ት መጻሕፍት ጽፎ ለጣሊያን መንግሥት በማስረከቡ በዚሁ መሠረት ጣሊያኖች በመቋመጣቸው ነው፡፡
#የመጀመሪያው_ወረራና_ጦርነት
መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ(እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘ በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡
ከኤርትራ ሲሻገሩ መጀመሪያ ጦርነት ያደረጉት በ1887ዓ.ም. በወርኃ ጥር በዶጋሊ ከአጼ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና ከሐማሴኑ ባላባት ከጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ ጋር ነው፡፡ ጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋም ጠላትን ድል በማድረግ ወደ ምጽዋ መልሰውታል፡፡
ለራስ አሉላ አባ ነጋም እንዲህ ተብሎ ተግጠሞላቸዋል፡፡
‹‹የአሉላ ፈረስ የረገጣቸው፤
እስካሁን ድረስ አለ ቊስላቸው፡፡
የአሉላ ፈረስ ተስቦ ወርዶ፤
ያንን ነጭ ገብስ አረገው ነዶ፡፡››
ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በማድረግ
በየካቲት 1885ዓ.ም. ዐጤ ምኒልክ የውጫሌ ውል እንደማይሠራ ለአውሮፓ መንግሥታት ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በዶጋሊ የተሸነፉትና በውጫሌ ውል አልሆን ያላቸው ጣሊያን በኅዳር 29/1888ዓ.ም. ጦርነት ከፈቱ ጀግኖች ኢትዮጵያኖችም ሻለቃ ቶዘሊንና ሌሎች ፋሽስቶችን እንደ ነፋስ ትቢያ አድርጎ በተናቸው፡፡ ቀጥለውም በየካቲት 23/1888ዓ.ም. ጠዋት 12 ሰዐት አመሻሽ 12 ሰዐት ባለቀው፤ እንኳን ለኢትዮጵያውይን ይቅርና ለአፍሪካውያን ኩራትና የጀግንነት ተምሳሌት የሆነው የአድዋ /የሶሎዳ ተራራ/ ጦርነት በጀግናው መሪ በዐጤ ምኒልክ ድል አድራጊት ተጠናቀቀ፤ ጣሊያንም የሽነፈት ጽዋዋን ጠጥታ ተመለሰች፡፡፡ዐጤ ምኒልክም ሚያዝያ 15/1889ዓ.ም. ወደ መናገሻ ከተማቸው ሲመለሱ የማረኳቸወን ጣሊያኖች ዛሬ ‹‹ጣሊያን ሰፈር›› በሚባለው ቦታ አኖሯቸው፡፡ ‹‹የአዲስ አበባ ውል›› ተብሎ በሚጠራው በኢትዮጵያና በጣሊያን በተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ ምርኮኞቹን እንድትፈታ፤ የውጫሌ ውል መሠረዙና፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ጣልቅ እንዳትገባ፤ የኤርትራ ድበር እስኪከለል ጣሊያን ከጦርነቱ በፊት ባለችበት እንድትረጋ በሚል ተከናወነ፡፡
#ሁለተኛው_ወረራና_ጦርነት
ሁለተኛው ጦርነት ከ1929ዓ.ም.-1933ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ (ለዚህ ጦርነት ደግሞ መሠረቱ ጣሊያን የቀድሞ ሽንፈቷ ቂም በመያዟ ነው)፡፡ የተጀመረውም በኅዳር 26/1927ዓ.ም. በወልወል (የኢትዮጵያ ሶማሌ ክፍለ ሃገር በኦጋዴን ውስጥ በዋርዴር አውራጃ አካባቢ የምትገኝ ወረዳ ስትሆን ንጹሕ የከርሠ ምድር ውኃ የሚገኝባትም ነች፤ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ 350 ጥልቅ የውኃ ጕድጓድ አስቆፍረውላታል) ላይ ጣሊያን ባንዲራዋን በመትከሏ ምክንያት ነው፡፡ በዚሁም ምክንያጥ የአውራጃው ገዢ ፋውራሪ ዓለማየሁ ከጣሊያኑ ጦር አዛዥ ካፒቴን ችማሩታ ጋር ጦርነት ገጠመዋል፤ በጦርነቱም ጀግናው ፊታውራሪ ዓለማየሁ በፋሽስታዊ ታንክ ነጂ በገዛ ታንኩ ላይ ላይ ተወርውረው በመውጣት ሰይፈውታል፤ ብዙ የጀግንንት ሥራንም አከናውነዋል፤ ቆይቶ ግን ለሃገራቸው በጀግንነት እየተዋጉ ሣለ ከሌሎች 107 ኢትዮጵያውያን ጋር አርፈዋል፡፡ በዚህ ውጊያ ላይ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ባንዳ በመሆን ለሃገራችን ጠላት ቢሆኑም (ለምሳሌ ሡልጣን ኢብራሂም አሰብን ለሮማ ልዑካን ሸጥኩላቸው የሚለውና፣ የአዳል ባላባት የራሄታ ሡልጣን ሐሰን ሙሐመድለሮማ ሚስዮናውያን የኢትዮጵያን ወደቦች እነሸጣለን ብሎ የመከረ)፤ ለሃገራቸው ሲሉ የተዋጉ የሙስሊም አርበኞችም ነበሩ፤ ዋነኞቹም ኑር ሑሴንና ደጃዝማች ዑመር ሰመትር ይጠቀሳሉ፡፡
በዚሁም ጣሊያን ‹‹ጅራፍ ረሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል›› እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዜጎቹን ገድላብኛለችና 200 ሺህ ሊሬ ካሳ ትክፈለን ብለው ለመንግሥታቱ ማኅበር ከሰሱ፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በድርድር ያልቃል ብላ ስትጠብቅ በጎን ግን ኢጣሊያ ለጦርነት ስትዘጋጅ ቆየች፤ በኅዳር 1927ዓ.ም የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስቴር ፒየር ላቫል ኢጣሊያ ከጀርመን ሂትለር ጎን እንዳትሰለፍ በማሰብ ኢትዮጵያን ብትወርር እንደማትቃወም አሳወቅ፤ ጦርነቱን የተቃመወችው ሩሲያ ብቻ ነበረች፡፡በመስከረም 22/1928ዓ.ም. ኢጣሊያ የመረብን ወንዝ ተሸግራ ጦሯን በ3ት መስመር አሰልፋ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ገባች፡፡ ያገኘችውንም እያጠፋች እንትጮንና አዲግራትን በያዝ ዓድዋ ደረሰች፤ ለዚሁም አስተዋጽዖ ያደረጉላት ለግል ጥቅማቸው ያደሩ የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑ ባንዳዎች ነበሩ ለአብነትም ዋነኞቹ (ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፣ ደጃዝማች ሀብተ ማርያም፣ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው) ናቸው፡፡ ባንዳ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው የጎንደርን ሕዝብ አሳምኖ ለኢጣሊያ ተገዢ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች ታደሰ ይማም ወንድይራድ ሲሰማ ያለበት ድረስ ደርሶ ድባቅ መትቶታል፤ ባንዳው እጅጉ በጣና ሐይቅ በታንኳ ተሸግሮ አምልጦ ወሎ ተደበቀ፤ ይህንንም ታላቁ አርበኛ ደጃዝማች ታደሰ ወሎ ድረስ ዘምቶና ከበባ አድርጎ ሃገሩን ለሸጠ ምሕረት አይገባውምና እንደ በግ አርደውታል፡፡
ጣሊያኖች በባንዳዎች በመታገዝ ጭምር በመርዝ ጋዝ ታግዘው በየካቲት 27 ከራስ ሙሉጌታ ጋር በተደረገው ውጊያ የራስ ሙሉጌታ ጦርን በመደምሰሳቸው በሐበሾች ዘንድ የሞራል ውደቀት አስከትሏል፡፡ ነገር ግን ጀግኖች አርበኞች እምቢ ለሃገሬ በማለት በተንቤን፣ በእንደርታ፣ በሽሬ፣ በአሸንጌ ላይ ተዋጉ፡፡ በአሸንጌው ጦርነት ጠላት ጣሊያን ከላይ በአውሮፕላን ጠላት ባንዳ ደግሞ ከታች በመሆን 8ሺህ የሚጠጉ አርበኞቻችን ላይ ጉዳት አደረሱ፡፡ በመጋቢት 24 ለ13 ሰዐታት በተካሄደው የማይቸው ጦርነት ላይ ኢትዮጵያውያን ድል አድረገው ጦርነቱ ማብቂያ ላይ የመርዝ ጋዝና የቦንብ ውርጅብኝ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ ጀግኖች አርበኞቻችን አብዛኞች አለቁ፤ ከማይጨው የተረፉና በአሸንጌ ላይ የነበሩትን ጀግኖች አርበኞችን 150አውሮፕላን ደርሰው ደብደቡት በመትረየስም ፈጁት፡፡ (ጣሊያኖች ዚሁ ወረራቸው በሰሜን 300፣ በደቡብ 150 አውሮፕላን አዝምተዋል፡፡)

❤6🥱1
በአምባ አራዶም 50 ሺህ፣ በሽሬና በተንቤን 15 ሺህ ሰው ሙቶ 200 ሺህ ሰው ቆስሏል፡፡
በሚያዝያ 24/1928 ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ለተባበሩት መንግሥታት አቤቱታ ሊያቀርቡ ወደ ጄኔቫ ሄዱ፤ በሃገሪቱ ንጉሠ ነገሥቱ አለመኖሩን ጣሊያኖ ሲያውቁ በ3 ቀናት በመገስገስ በሚያዝያ 27 አዲስ አበባን ተቈጣጠሩ፡፡ በእነዚህ 3ት ቀናት ውስጥም ሽብር ዘረፈና ግድያ በአዲስ አበባ እጅጉን በርቶቶ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች የሆኑት አርበኞችም፤ ጎራዴ መዝዘው ነፍጥ ይዘው በተለያዩ ቦታዎች እምቢ ለሃገሬ በማለት ሸፈቱ፤ በጎጃም ዱር ቤቴ ያሉት ለጣሊያን ፋታ አልሰጥ አሉት፡፡ ራስ አበበ አረጋይ ግንቦት 6/1928ዓ.ም. ጅሩ ገብተው የአርበኝነት ተግባራቸውን ሲጀምሩ ሌሎች ጀግኖች አርበኞችም እርስ በእርሳቸውም ተባበሩ፡፡ ለአብነትም ዋና ዋናዎቹ ከፊት መሪዎቹና አስተባባሪዎቹ ፊታውራሪ ዘውዱ አባ ኮራን፣ ዳዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ደጃዝማች ፍቅረ ማርያም ናደው፣ ፊታውራሪ በለው ቸርነት፣ ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ፣ ግራዝማች ዘውዱ አስፋው፣ ባሻ ወልደ ጻድቅ ሲሆኑ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በጎጃም ታላቁቅ የጅግንነት ጀብዱ ከፈጸመው ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ጋር ሕብረት ፈጠሩ፡፡ ይህ ሕብረትም ለጣሊያን ፋታ ሲያሳጣው፤ በሌሎች ቦታ ላሉ ኢትዮጵያውያኝ ፈር ቀዳጅ በመሆኑ ሁሉም ይተባባርና እምቢ ለሃገሬ ይል ጀመር፡፡
ለምሳሌም፤ ሰኔ 1928ዓ.ም. የሆለታ የጦር አካዳሚ ምሩቃን(ዶ.ር ያለም ወርቅ በየነን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጦ)ና በውጭ ሃገር የተሰማሪ ሲቪሎች በመተባበር የመሠረቱት ‹‹‹ጥቁር አንበሳ›› አንዱ ነው፡፡ ‹‹ጥቁር አንበሳ›› ራስ እምሩን መሪው በማድረግ ብዙ ጀብዱዎችን ፈጽሟል፤ ጣሊያን ደቡብ ኢትዮጵያን ለመያዝ ካቶሊካዊውን ደጃዝማች ሀብተ ማርያምን በመጠቀም ቦንጋ አውሮፕላኖቿን ስታሳርፍ የጥቁር አንበሳ ማኅበርም በቦንጋ አውሮፕላን ማረፊያ የሰራው ጀብዱ ግን ከሁሉም የላቀና የማይረሳ ነው፡፡
ስለ ታላቁ አርበኛ ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ እንዲሁም ለጃዝማች ኃይሉ እንዲህ ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፤
እውነተኛው ጀግና ኃይለ ማርያም፤
ስሙ እንዳይረሳ ጻፈልን በደም፡፡
እንዲህ ያለው ጀግና እንዲህ ያለ ወንድ፤
ጌጥ ይሆናቸዋል ለታሪኮች ዐምድ፡፡ የተባለለት
የደጃዝማች ኃይሉ እጁ ውድ ናት፤
የቀመሱ ሁሉ ሲያመሰግኗት፡፡
ሌላው ፋሽስትን በተባበረና ስልታዊ በሆነ መልኩ በሐምሌ 21/1928ዓ.ም. በአዲስ አበባ መቀመጫና መቆሚያ ያሳጡት የሸዋ አርበኞች ሲሆኑ አሰላለፋቸውም፤
በሰሜን አዲስ አበባ ወንድማማቾቹ ደጃዝማች አበራ ካሣና ወንድወሰን ካሣ የሚመሩት ሲሆን በውስጡ ሰማዕት የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ያካተተ ነው፡፡
በሰሜን ምሥራቅ አዲስ አበባ፤ በራስ አበበ አረጋይ የሚመራ፡፡
በምሥራቅ አዲስ አበባ፤ በደጃዝማች ፍቅረ ማርያም ናደው (አባ ተጫን)ና ነጋድራስ ቦጋለ የሚመራ፡፡
በደቡብ አዲስ አበባ፤ በደጃዘማች ባልቻ አባ ነፍሶ የሚመራ ሠራዊት ተጀምሯል፡፡ነገር ግን ወቅቱ ክረምት በመሆኑና ወንዞች በመሙላታቸው አርበኞች ተቀናጅተው እንዳይዋጉና ሕዝቡንም እንዳይቀሰቅሱ ትልቅ እክል ሁኖባቸው ነበር፡፡ በዚህም ሙሉ አዲስ አበባ ላይ አደጋ ጥሎ ጣሊያንን የማስለቀቁ ተግባር የታለመለትን ያክል ባየሳካም በጠቂት አቅጣጫዎች ጀግኖች አርበኞች ተዋግተዋል፡፡ የተወሰኑትም ወደ ፍቼ ሸሽተዋል፤ ታላቁ አባት ብፁዕ ጴጥሮስም የታያዙት በዚሁ ወቅት ነበር፡፡ ጀግኖቹም ጣሊያንን እምቢ ለሃገገሬ በማለት እስከ የካቲት 12/1929ዓ.ም. የጉያ ረመጥ ሁነውበታል፡፡
ከ1927-1934 ዓ.ም. ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀጋረችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤
*በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤
*ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤
**የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ የሞቱ፤
*በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤
*በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤
*ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤
*በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤
*ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤
*ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡
*ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣
#የካቲት_12/1929ዓ.ም. (#የሰማዕታት_ቀን)
ግራዚያኒ በናፖሊ መስፍን አልጋ ወራሹ ኡምቤርቶ ወራሽ በማግኘቱ ምክንያት ዐርብ የካቲት 12/1929ዓ.ም. በአዲስ አበባ የሚገኙ ድሃዎችንና ነዳያንን እንዲሰበሰቡ አደረገ፡፡ በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ቀትር ላይም ንግግር ማድረግ ሲጀምር በወቅቱ የተገኙትና የጣሊያን ፋሽስትነት ያንገፈገፋቸው አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ሰባት ቦንብ በግራዚያኑ ላይ ወረወሩ፤ በጥቃቱም ግራዚያኑ 365 ቦታዎች ላይ ቆሰለ /በይበልጥ እግሩ ቆሰለ/፣ 3ት ኢጣሊያናውያን ሞቱ፣ 50 ቆሰሉ፣ በተለይም የጦር አዛዡ አውራሊያ ሊአታ ከን ዓይኑ ጠፋ፡፡ በዚህም አንድም ኢትዮጵያዊ እንዳያመልጥህ ግደል በመታዘዙ በፋሽስት ኢጣሊያ በመትረየስ፣ .... በአካፋ ጭምር ሊረዳ የመጣውን ድሃና ነዳይን ጨምሮ 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሰዕትነት አረፈ፡፡ ይህ ግድያ ወደ ታላላቆቹ ገዳማትና አድባራትም በመዛመት በደብረ ሊባኖስ ያሉ 2200፤በዝቋላ ገዳምም 120 መነኰሳትና ምዕመናን ተረሸኑ፡፡ አስከሬናቸውንም ክብር ባለመስጠት በአካፋ በማንሳት አሰቃዩት፡፡ እንዲሁም 350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460 770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746 800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤ 300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤ 2000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡ ለአብነትም ካቃጠለቻቸው ገዳማትና አድባራት መካከል፤
*ይደመቆ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/
*አፈር ባይኔ ተክለ ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
*አክርሚት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
*ጎበጥ አገር ገብርኤል ቤ.ክ ሰሜን ሸዋ እም ምሕረት/
*አንኮበር ቅድስት ማርያም ቤ.ክ.
*ደረፎ ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/
*ጎንቻ መድኃኔ ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/
*አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ. ይገኙበታል፡፡ (ምንም እንኳን አልፎ አልፎ እንደ ማኅበረ ሥላሴ ያሉ ገዳማት አባቶች በጸሎታቸው አውሮፕላናቸውን እንዲከሰከሱ ቢያደርጉባቸውም)
ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡ (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡

❤6😢1