#ጥር_4_ተዝካረ_ፍልሰቱ (በዓለ ስዋሬው ) #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
በተለያዩ ቅጽል ስሞች የሚጠራ፤ ጌታቸችንን ሥነ ስቅለት የሳለ፡፡
ከ81ዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 5ቱንና ሌሎች መጻሕፍትን (ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤
#ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያስተማረ፤
ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡
✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤)
✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤)
✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /መጽሐፈ ሰዐታት/
፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤
ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡
ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
ወልደ #ዘብድዮስ ፥
ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥
ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥
ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡)
ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥
ዮሐንስ #ድንግል
ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡
1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) ፣ 2. ዮሐንስ ድንግል ፣3. #ዮሐንስ_ፍንው፣4. #ዮሐንስ_ካህን ፣ 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ ፣
6. ዮሐንስ ሥርግው፣7. #ዮሐንስ_ምዑዝ8. ዮሐንስ ቅኑይ ፣ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት ፣ 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ ፣ 11. #ዮሐንስ_ክቡር12. ዮሐንስ ጻድቅ ፣ 13. #ዮሐንስ_ረድእ፣ 14. ዮሐንስ ማኅቶት፣ 15. #ዮሐንስ_ድንግል፣ 16. ዮሐንስ ንጹሕ ፣ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ ፣18. ዮሐንስ መረግድ፣ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ ፣ 20. ዮሐንስ መልአክ ፣21. #ዮሐንስ_ኪሩብ ፣22. #ቁጽረ ገጽ
#ስዋሬው፤
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡
ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አርገጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡
በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ፡፡ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው ፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡
ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል ›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡
በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤10
#ጥር ፮፤ #በዓለ_ግዝረቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ፡፡ #በዓለ_ዕርገቱ_ለኤልያስ_ነቢይ፡፡ #በዓለ_ዕረፍቱ_ለኖኅ_አቡነ፡፡
#ግዝረተ_እግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
፠ ጌታችን በተወለደ በ8ኛ ቀኑ ዕጉለ ማዕነቅ ይዞ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
፠ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› /ሮሜ.፲፭፥፰/፡፡
፠ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡
፠ የእመቤታችን ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደመውጣቱ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ፡፡
እንዲሁ በተዘጋ ቤት መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እነዲሁ እንደፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ፡፡
#ቅዱስ_ኤልያስ_በእሳት_ሰረገላ_ወደ_ብሔረ_ሕያዋን_ያረገበት_ዕለት_ነው፡፡
**በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡
✤ የሰማርያው ነቢይ ቴስቢያዊው ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ እናቱ ደግሞ ቶናህ(ቶና) ሲባሉ ሲወለድ መላእክት በእሳት ሰፋድል (መጠቅለያ መጐናጸፊያ) ጠቅልለውት ነው፡፡ የስሙ ትርጉምም ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ነው›› ማለት ነው፡፡
** ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ? ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡
✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር፥ ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን
✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡
✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ. 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማሯል፡፡
✤ 4. ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡
✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት የሰራፕታዋ ሴት ልጇ /ኋላ ዮናስ ነቢይ የሆነው/ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23
✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ፥ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ፥ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ፥ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ ሐሰቶች የነበሩትን 850 የሚጠጉ የጣዖት ካህናትንም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ ፈጅቷቸዋል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18 20 -29
✤ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት (ተቀበለለት) 1ኛ ነገሥ. 18፥30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡
✤ 8. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት፥ ምሉአነ ኀጢአት፤ የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ፥ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13
✤ 9. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብና መጠጥ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ተጉዟል 1ኛ ነገሥ. 19፥5-7፡፡
✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሻግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11፡፡ ለደቀመዝሙሩም ሀብተ መንገፈስ ቅዱስን አድሎታል፡፡
✤ 11. በትህትናው ‹‹ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ›› ብሎ እንዲሞት ለመነ፡፡ እግዚአብሔር ግን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራውን ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አሳርጎታል፡፡ 2ኛ ነገሥ. 2፥6-9
✤ 12. እንደ አስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል፡፡
✤✤#ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17፥3፡፡
ዳግመኛም ዛሬ የአባታችን ኖኅ መታሰቢው ነው፡፡ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ …ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ፥ ፍጹምም ሰው ነበር፡፡ ኖኅ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡ /ዘፍ. 6፥7/
#ዳግመኛም በዚህች ዕለት በበረሃ ስልሳ ዘመናት የኖረ የቅዱሳንን ልቡና ከማየቱ የተነሣ ያደነቀ፤ ፊቱም ተለውጦ እንደእሳት ፍሕም ሆነ አባ ሙሴ በዓለ ዕረፍቱ ነው፡፡
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የጌታችን_በዓለ_ግዝረት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው #፮ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
#በአዲስ_አበባ_የጌታችን_በዓለ_ግዝረት_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ፤
ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ ሞቢሉ ጋር (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ/ኢየሱስ/፤
፪. ገዳመ ኢየሱስ ቤ/ክ
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከመርካቶ → ኮልፌ፡፡
ወይም ከጦር ኃይሎች ዊንጌት/አስኮ/ → (በሚል ታክሲ) (በቀለበት መንገድ)
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የጌታችን_በዓለ_ግዝረት_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ ገዳም፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ እንሳሮ ወረዳ፥ ጀማ በረሃ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መራካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሃ ቤቴ /አለም ከተማ/ መንገድ → ጀማ በረሃ → በልበሊት ኢየሱስ፡፡
ወይም፤ ከደቡብ ወሎ (ደሴ ወይም ወግዲ) → አለም ከተማ ጀማ በረሃ → በልበሊት ኢየሱስ፡፡
፪. ለብቃ ኢየሱስ፤ (ተአምረኛ የኾነ ፍልውሃ ጠበል የሚፈልቅበት፤ በቆዳ በሽታ በአካል፥ ደዌ የፈራረሰን ሰውነት ሳይቀር የሚጠግን)፡፡ ከገናናነቱ ተነሣ የሚከተለው ግጥሞች ተገጥሞለታል፡፡
፨ የለብቃው ኢየሱስ፥ የለብቃው፤
የፈረሰ ገላ ትጠቅማለህ አሉ፡፡ እየተባለ የሚዘመርለት፡፡
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ መርሐ ቤቴ፥ ሚዳና ወረሞ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መራካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሃ ቤቴ /አለም ከተማ/ → ሚዳ ወረሞ ወረዳ → ለብቃ ኢየሱስ፡፡
ወይም፤ ከደቡብ ወሎ (ደሴ ወይም ወግዲ) → መርሃ ቤቴ /አለም ከተማ/ → ለብቃ ኢየሱስ፡፡
፫. በለስ ዋሻ ኢየሱስ ገዳም፤ (ጥንታዊና የቅዱሳን መናኸሪያ፤ በተጕለት ከሚገኙ ከ5ቱ የቅዱሳን መናኸሪያ ገዳም አንዱ፡፡)

❤9👌1
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለትና ቡልጋ፥ አይዞሽ አሞራ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → አይዞሽ አሞራ (ወደ ደብረ ሲና እየተጓዙ ሳለ በመገንጠል) → በለስ ዋሻ ኢየሱስ፡፡
ወይም ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → በኩክ የለሽ መንገድ → ዘንባባ ኢየሱስ → በለስ ዋሻ ኢሱስ (በእግር የ2 ሰዓት መንገድ)
፬. አማኑኤል ኢየሱስ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደንበጫ፥ አማኑኤል ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በባሕር ዳር መስመር (ከደብረ ማርቆስ 27 ኪ.ሜ) (በደጀንና በደንበጫ መሃል ላይ)፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ በውስጥ አሳውቁን)
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → አይዞሽ አሞራ (ወደ ደብረ ሲና እየተጓዙ ሳለ በመገንጠል) → በለስ ዋሻ ኢየሱስ፡፡
ወይም ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → በኩክ የለሽ መንገድ → ዘንባባ ኢየሱስ → በለስ ዋሻ ኢሱስ (በእግር የ2 ሰዓት መንገድ)
፬. አማኑኤል ኢየሱስ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደንበጫ፥ አማኑኤል ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በባሕር ዳር መስመር (ከደብረ ማርቆስ 27 ኪ.ሜ) (በደጀንና በደንበጫ መሃል ላይ)፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ በውስጥ አሳውቁን)
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤4
#ጥር ፯፤ #በዓለ_ሥላሴ_ (#ዝርወተ_ባቢሎን)፡፡
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_ቅድሥት_ሥላሴ_የሰናዖርን_ግንብ_ያፈረሱበት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው #፳፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
#በአዲስ_አበባ_የቅድስት_ሥላሴ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #መካነ_ሥላሴ ( #መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ.ክ.)፤ (አዲስ አበባ ላይ በ1883 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ነገር ግን ታቦቱ ቀድሞ የነበረና ከ600 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው)
አድራሻው፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ 4 ኪሎ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → 4 ኪሎ፤
፪. #መንበረ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ሽሮ ሜዳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከአራዳ ጊዮርጊስ)(ከመርካቶ)(ከቦሌ)(ከካዛንቺስ)(ከስታዲየም) → ሽሮ ሜዳ፡፡
፫. #ደብረ_ሲና_ቅዱስ_እግዚአብሔር_አብ፤ (በድርብነት ይከበራል)
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ በአዲሱ ገበያ በቀጨኔና በእንጦጦ መሃል ላይ የሚገኝ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ) → አዲሱ ገበያ(ቀጨኔ) → ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፡፡
፬. #መሪ_ምሥራቀ_ፀሐይ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አያት መሪ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → መሪ/አያት/፡፡
፭. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ካራ አሎ፡፡
፮. #ጠሮ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ከተማ፥ ጠሮ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ/መርካቶ/ → ኮልፌ፡፡
፯. #ጀሞ_ፈለገ_ኮሬብ_ቅድስት_ሥላሴና_ቅድስት_ማርያም
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ ሸዋ ዳቦ ቤት /ሜክሲኮ/ → ጀሞ፡፡
፰. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔ ዓለም፤ (በድርብነት ይከበራል)
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቀራንዮ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → ቀራንዮ፡፡
፱. #አየር_ጤና_አንቀጸ_ብርሃን_ቅድስት_ኪዳነ_ምሕረት፤ (በድርብነት ይከበራል)
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አየር ጤና፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → አየር ጤና፡፡
ወይም፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → አለም ባንክ/ኤር ጤና/፡፡
፲. #ሰፈረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 4፤
ታክሲ፤ ከሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡
፲፩. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡
፲፪. #ቂሊንጦ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9 ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → /በጎሮ/ ቂሊንጦ
ወይም ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቂሊንጦ፡፡
፲፫. #ኤረር_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፥ ጎሮ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ጎሮ፡፡
፲፬. #መሪ_ቅድስት_ሥላሴ
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ መሪ አያት፥ ወረዳ 13፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → መሪ/አያት/፡፡
፲፭. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤ (በድርብነት ይከበራል)
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ፡፡
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የቅድስት_ሥላሴ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (ከ2014 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ የብዙ ቅዱሳን /የአባ ዐምደ ሥላሴ፣ የአባ ክፍለ ማርያም፣ የ7ቱ ዘሥላሴ፣ የአባ አርከ ሥሉስ ቅዱስ፣ …….. ) መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ቋራ (መተማ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር/አዘዞ/ → ሸዲ/መተማ/ → በእግር፡፡
፪. #ዱጉም_ሥላሴ_ገዳም፤
አድራሻ፤ ትግራይ፥ ገርዓልታ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → በመቀለ (በጎንደር) → ገርዓልታ፡፡
፫. #ደብረ_ወገግ_አሰቦት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሳሙኤል፤ (በ13ኛው ክ/ዘመን በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተስፋፋ፥ ቅዱስ ዑርኤል የጌታን ደም በጽዋው የመጨረሻውን እንጥፍጣፊ ያፈሰሰበት፥ በርካታ ቅዱሳን የተሰወሩበት፥ አሁንም የሚሠወሩበት፥ የምሥጢር ቦታ)
አድራሻ፤ ሐረርጌ፥ አሰበ ተፈሪ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት/አዳማ/→ አሰበ ተፈሪ → አሰቦት፡፡
፬. #ሰሜን_ሸዋ_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዓፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን ከተማ፡፡
፭. #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ (በ1500ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዐፄ ልብነ ድንግል ሥራው የተጠናቀቀ፤ ባለ 16 መንበር፥ በዕንቊና በወርቅ የታነጸ የነበረ፤ /ኋላ በግራኝ የፈረሰ/፤ ነገር ግን ጽላቱ በዐፄ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ቀድሞ 4 ኪሎ መካነ ሥላሴ አሁን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል የሚጠራው)፤ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና በቀድሞው ቅርጹ በባለ 16 መንበር ተደርጎ 2009 ዓ.ም. አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በመገንባት ላይ ይገኛል፤ (ለሕንፀታ ቤቱ ሁላችንንም ያብቃን)፡፡
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ወረኢሉ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወረኢሉ፡፡
፮. #ፀዓዳ_አምባ_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል_ገዳም፤ (በ1669 ዓ.ም. የተገደመ፤ መሄጃ መንገዱ እጅግ አስደናቂና በ2ቱም በኩል ገደል የኾነ)
አድራሻ፤ ኤርትራ፥ ዞባ አንሰባ፥ ከረን፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ (በአውሮፕላን)→ ኤርትራ → ከረን → /25ኪ.ሜ/ ፀዓዳ አምባ፡፡
፯. #ጎንደር_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በጥር 26 ቀን 1683 ዓ.ም. በዓፄ አድያም ሰገድ የታነጸ፤ በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ 44ቱ ታቦታተ ጎንደር በአሠራሩ ልዩ የኾነ፤ በ1880ዎቹ ድርቡሽ ጎንደር ከተማን ሲያጠፋ ከ44ት አብያተ ክርስቲያናት በተአምራት ሳይቃጣል የቀረ፤ የታላላቅ ሊቃወንት /የእነ ሊቁ ክፍለ ማርያም/ መፍለቂያ፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፰. #ናርጋ_ሥላሴ_ገዳም፤ (በጣና ሐይቅ ላይ ካሉ ደሴቶች ትልቁ በሆነው በደቅ(7ት ደብር ሃገር) ደሴት ከሚገኙ 7 ገዳማት አንዱ)፡፡ (በአፄ በካፋ ባለቤት በበእቴጌ ምንትዋብ /1730-1755 ዓ.ም./ የተሠራ፤ ግድግዳዎቹ በሚያስደንቁና ልቡናና መንፈስን በሚመስጡ ሥዕላት ያሸበረቁ፡፡)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጣና ሐይቅ (ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ /በጀልባ 3 ሰዓት/፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባህር ዳር/ጎንደር → በጀልባ/በታንኳ/ /በመርከብ/ ናርጋ ሥላሴ፡፡
፱. #ጨለቆት_ሥላሴ_ትግራይ፤ መቀለ አጠገብ፡፡ (በ1787 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲኾን ተካዩ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ክፍለ ኢየሱስ ሃገረ ገዢ ናቸው) (የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያ ነው፤ ለአብነትም በዐፄ ዮሐንስ /1864 – 1881ዓ.ም./ ዘመነ መንግሥት አራት ጳጳሳትን እንዲያመጡ ከተላኩት መካከል አንዱ ሊቅ አለቃ ዐሥራት ዘውጉ ዘጨለቆት ሥላሴ ናቸው፡፡) (የእንግሊዝ ጦር ዐፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ሰብስቦት የነበረውን ዘርፈው ሲወስዱ የበዛባቸውን ለዚህ ደብር ሰጥተው ሄደዋል፡፡)
አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ እንደርታ አውራጃ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ /እንደርታ/፡፡

❤6🔥1
፲. #ሐረር_ሐድሬ_ጥቆ_መካነ_ሥላሴ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ሐረር ከተማ፥ ሐድሬ ጥቆ ወረዳ፤ (በአፄ ኀይለ ሥላሴ በ1941-43 ዓ.ም. የተሠራ)
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐረር፡፡

❤2