#ጥር ፫፤
የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው እና የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን_ጸበል_ያፈለቁ የታላቁ አባት አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት ነው ።
#በአ.አ. #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት ቀድሞ በቅዳሴና በውዳሴ ታቦተ ሕጋቸው ሲከበር የቆየው የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ታቦተ ሕጋቸው #ቅዳሜ_ጥር 3/2017 ዓ.ም.
ሰባተኛ ጊዜ_ታቦተ_ሕጋቸው_ወጥቶ_ይከብራል፡፡ (ሁላችሁም እንድትገኙ ገዳሟ ጥሪዋን አስተላልፋላች)፡፡
አባ ሊባኖስ #የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው፤
፠ ቅዱስ ላሊበላ ከ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን በስማቸው ያነፀላቸው፡፡
፠ #ከደረቅ_ዐለት_ላይ_ውሃ_እያፈለቁ_ድውያንን_የሚፈውሱ_ተአምረኛ_አባት
፠ በኤርትራ አካለ ጉዛይ ገዳመ መጣዕ፣ በአኵሱም ከተማ አጠገብ፣ በላስታ ላሊበላ፣ ደብረ ወርቅ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፣ እንዲሁም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአ.አ. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ክብረ በዓል የሚከበርላቸው።
፠ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ሊድሯቸው ሲሉ መመነን በመፈለጋቸው መልአክ በሌሊት መጥቶ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡
፠ አባ ጳኩሚስም ሥርዐተ ገዳምን፥ አስኬማ መላእክትን፥ ቅናተ ዮሐንስን አስተማሯቸው፤ አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡
፠ ቀድሞ የመራቸው መልአክ ከአባ ጳኩሚስ ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአኵሱም ተቀመጡ፡፡
፠ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው (ቀድሞ የዋልድባን ገዳም ባስፋፉ አባቶች የተመሠረተችውን #የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን እስፋፍተው፡፡) ተመልሰው ወደ አኵሱም ሄዱ፡፡
፠ በአኵሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ፥ ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአኵሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡ (ስዕላቸው የሚገልጸው ይህንን ተአምር ነው፡፡)
፠ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡
፠ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአኵሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ፤ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡
፠ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ (የአሁኗ ደብረ ሊባኖስ) መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት) ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡
፠ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አኵሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው አፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡
፠ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ አፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡
፠+፠ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ፤
፠+፠ ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው፤
፠+፠ በ140 ዓመታቸው ጥር 3 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
፠+፠ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡
* እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡
#እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም
፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡
፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው ጠበሏን አፍልቀው ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡
፠ በ197 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡
፠ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ይመስገን፨
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤12
#ጥር ፬፤ #በዓለ_ስዋሬሁ_ለዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_፡፡
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_በዓለ_ስዋሬ_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው #ገዳማትና_አድባራት፡፡
#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_፫ #ገዳማትና_አድባራት_፡፡
፩. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ማርያም ቤ.ክ.
ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣ፥ ከዐፄ ዮሐንስ ጋር በመቀለ፤ ከራስ ጉግሳ ወሌ ጋር በደብረ ታቦር፤ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ መናገሻ ገተ ጽጌ ያመጣችው፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ደግሞ አሁን ያለውን ሕንፃ ያሠሩት፤ በአዲስ አበባ በወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ስም በመሰየም ብቸኛው ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ ሰባራ ባቡር፥ አባ ኮራን፥ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል
ታክሲ፤ ከፒያሳ ጴጥሮስ ዐደባባይ → ዊንጌት አስኮ በሚለው ታክሲ ተሳፍረው ቤተ ክርስቲያኑን ያገኛሉ፡፡
ወይም ከመርካቶ ጎጃም በረንዳ → አዲሱ ገበያ (ቀጨኔ) በሚሉ ታክሲዎች ተሳፍረው ቤተ ክርስቲያኑን ያገኛሉ፡፡
፪. ብሔረ ጽጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኀኔዓለም ቤ/ክ (የሐዋርያው ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ታቦት ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ጀምሮ በድርብነት ይከብራል)
አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ፥ ብሔረ ጽጌ፤ ከብሔረ ጽጌ መናፈሻ 100 ሜትር ያህል ገባ እንዳሉ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሰታዲየም)(መርካቶ)(መገናኛ)→ አደይ አበባ/ሳሪስ/ → ብሔረ ጽጌ፡፡
፫. ምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም (ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ባይከብርም፥ ከቀድሞ ጀምሮ በኪዳንና በሰዐታት፤ በውዳሴ፥ በቅዳሴ ይከበራል፡፡)
አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ
ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሽሮሜዳ በሚለው ታክሲ (ምስካየ ኅዙናን ጋር)
ወይም ከመርካቶ ራጕኤል (ከጊዮርጊስ)→ ሽሮሜዳ በሚለው → መነን (የካቲት 12 ት/ቤት) ተወርዶ → ምስካየ ኅዙናን፡፡
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_፳፫ #ገዳማትና_አድባራት_፡፡
፩. መአቁዲ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ (ጥንታዊው ደብር፤ ለአንድ ቀን ብቻ ጠበል የፈለቀበት)፤
አድራሻ፤ ትግራይ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወልድያ → መአቁዲ፡፡
፪. ደቡብ ወሎ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ (ጥንታዊው ደብር፤ ከመካነ ሥላሴ አጠገብ የሚገኝ)፤
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → መካነ ሥላሴ፡፡
፫. ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ሐይቅ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደሴ → በወልድያ መስመር (ሐይቅ ከተማ)
፬. ደብረ በንኰል ገዳም አጠገብ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ
አድራሻ፤ ትግራይ፥ ሰለኽላኻ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ በንኰል አጠገብ
ትራንስፖርት፤ ከመቀለ(አኵሱም) → ሽሬ → ሰልኽላኻ → ደብረ በንኰል መስመር የቅ/ዮሐንስን ደብር ያገኙታል፡፡
ወይም ከጎንደር በሊማሊሞ ሽሬ (ዳንሻ፤ ሁመራ፤ ሽሬ) መስመር → ሰልኽላኻ → ደብረ በንኰል መስመር የቅ/ዮሐንስን ደብር ያገኙታል፡፡
፭. አደቁዋረክ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ አኵስም (ማዕከላዊ ትግራይ) ሃገረ ስብከት፥ ማኅበረ ዴጎ አጠገብ/፤፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደሴ → ወልድያ → መቀለ → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤
ወይም ከአ.አ. (በአውሮፕላን ) → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤
ወይም ወይም ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ/በሞጣ/ ባህርዳር → ጎንደር → ከጎንደር በሊማሊሞ ሽሬ (ዳንሻ፤ ሁመራ፤ ሽሬ) መስመር → ሽሬ → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤
፮. ገደፈና_ዮሐንስ /ማይጨው አጠገብ/፤
አድራሻ፤ ትግራይ፥ ማይጨው
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደሴ → ወልድያ → ማይጨው → ገደፈና፤
፯. መንዝ ማማ ሞላሌ ደዋ ዮሐንስ (900 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ፥ ሞላሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ሞላሌ → ደዋ፤
፰. ዣት ደብረ ፀሐይ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ጅሩ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደብረ ብርሃን በኩል → ጅሩ ፥ እነዋሪ → ዣት፤
ወይም ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በሙከጡሪ (መርሐ ቤቴ መስመር) → ለሚ → ጅሩ ፥ እነዋሪ፤
፱. ዘንስር ደብረ ተድላ ዮሐንስ ማዕከላ ለጐንደር፤ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፤ በጎንደር ከተማ የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ወደ ግምጃ ቤት ማርያም ከመዛወሩ በፊት በብቸኝነት የጎንደርና የመላው ኢትዮጵያ ሊቃውንት የማኅሌተ ጽጌን ቁመት ለመቆም የሚተሙት ታላቅ ደብር/፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አራዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ /በሞጣ/ መስመር → ባህር ዳር → ወረታ → ጎንደር ከተማ፡፡
ወይም ከመቀለ /አኵሱም/ → ሽሬ → በሊማሊሞ (በሁመራ ዳንሻ) → ጎንደር ከተማ፤
ወይም ከደሴ → ወልድያ → ደብረ ታቦር → ወረታ → ጎንደር ከተማ፤
፲. ሞያሌ ደጋ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ሞያሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. → ሞያሌ፤
፲፩. ደምበጫ አጠገብ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደምበጫ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → /በባህር ዳር መስመር/ ደምበጫ፤
፲፪. ቦኮሙራ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.ን፤
አድራሻ፤ ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት፥ ሚሻ ወረዳ፥ ቦኮሙራ ቀበሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ስልጤ → በኮሙራ፤
፲፫. ናዝሬት(አዳማ) ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ናዝሬት(አዳማ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → በደብረ ዘይት (በፈጣን መንገድ) → ናዝሬት (አዳማ) ከተማ፤
፲፬. ደሴ ዩኒቨርሲቲ ደብረ ነጎድጓድ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፤
፲፭. መቱ ደብረ ሳሌም ወነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤ (በ1915 ዓ.ም. የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ም.ወለጋ ሃገረ ስብከት፥ መቱ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ወለጋ/መቱ፤
፲፮. ጨንቻ ዶርዜ አይራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት ፥ ጨንቻ ወረዳ፥ ዶርዜ አይራ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ወለጋ/መቱ፤
፲፯. ፎገራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት ፥ ፎገራ ወረዳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ /በሞጣ/ መስመር → ባህር ዳር → ወረታ → ፎገራ፡፡
ወይም ከመቀለ /አኵሱም/ → ሽሬ → በሊማሊሞ (በሁመራ ዳንሻ) → ፎገራ፤

❤6
ወይም ከደሴ → ወልድያ → ደብረ ታቦር → ወረታ → ፎገራ፤
፲፰. ሐዋሳ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ሐዋሳ ሃገረ ስብከት ፥ ሐዋሳ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐዋሳ፡፡
፲፱. ሆሳዕና ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ሆሳዕና፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና፡፡
፳. ማፌድ ጓረባ ጠብረሪ ደብረ ዕንቊ ቅድስት ልደታ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ማፌድ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና → ማፌድ፡፡
፳፩. እዣ ስራይ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ እዣ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና → እዣ፡፡
፳፪. ደብረ ዘይት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤
አድራሻ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አድአ ወረዳ → ደብረ ዘይት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ዘይት፡፡
፳፫. አለም ገና ቤ/ን (ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በድርብነት ይከብራል)፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አለም ገና፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ → ጀሞ → አለም ገና፡፡ አቅጣጫ ምንጭ ገዳማት ገጽ

❤3