❤22
ታላቁ ገዳማችን አሰቦት ደብረ ወገግንና ደብረ ኪሩብን ለመሠረቱት ለአባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ በዓለ ዕረፍት (ጥቅምት 29) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
✤✤ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ፡
፠ በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ‹እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ጣዖታትን የሚሰብር፣ የሚያጠፋ፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኀጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ› ተብሎ በተነገረለት ትንቢታዊ ብሥራት ከደጋግና ከበቁ አባታቸው እንድርያስና ከእናታቸው አርሶንያ ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም. በቡልጋ ተወለዱ፤ ሲወለዱም መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡
፠ስማቸውን ሳሙኤል በብለው የሰየሟቸውና ክርስትናም ያነሷቸው፤ ኋላም መዓርገ ምንኵስናን የሰጧቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡
፠ ብዙ ጻድቃንን (አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ታዴዎስ ዘደብረ ድኁኃን፣ ሮማኖስ ዘደብረ ዋምን፣ አቡነ አኖሬዎስ ዕንቈ ባሕርይ ዘመረግድ ወመስተጋድል ወምግባር ንጹሕን) በሥጋ የሚዛመዱ ናቸው፡፡
፠ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና አባቱ ዓምደ ጽዮን ለሠራው ክፉ ሥራ ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡
፠፠ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል፤
* በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡
* ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
* ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፥
* ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፥
* በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፥
* ይህን ኀላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፥
* በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፥
* በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ፤
* ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግም ይታወቃሉ፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት (በጥቅምት 29) በኦጋዴን ዘርዘር በተባለ ቦታ በሰላም አርፈዋል፤ ከ7 ወራት በኋላ ሠምረ ክርስቶስ የተባለ ልጃቸው ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ወገግ በክብር አሳርፎታል፡፡
፠ የአሰቦት ደብረ ወገግን (ምስራቅ ሐረርጌ) ና ደብረ ኪሩብ (አፋር) ገዳምን የመሠረቱ፥ ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና፤ የመሠረቱት ገዳም የምሥጢርና የብዙ ስውራን መኖሪያ የኾነላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡
፠ ከአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ ከተሾሙት 12ቱ ንቡራነ ዕድ አንዱ ናቸው፤ ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነው፡፡
፠ ‹‹ደብረ ወገግ›› ከ2-5 ዓ.ም. እመቤታችን ከነልጇ ስተሰደድ ለ6 ወር የተቀመጠችበት ሲኾን፤ ደብረ ወገግ የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል በ34ዓ.ም. የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ ወገግ ላይ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ ወገግን የብርሃን ውጋገን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም ቦታውን ‹‹ደብረ ወገግ›› (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት›› ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት አርጓል፡፡
✤✤ ደብረ ወገግ፤
፠ በደብረ ወገግ ቦታ ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡
፠ ገዳሙ በግራኝ ወረራ ወቅት ከጠፋ በኋላ እንደገና መልሶ የቀናው በ1911ዓ.ም. በታላቁ ሊቅና መናኝ በአለቃ ገብረ መድኅን ነው፡፡ በ1912 ዓ.ም. የአቡነ ሳሙኤልን ቤተ ክርስቲያንን በሣር ክዳን ሠሩ፤ በዓመቱ በ1918 ዓ.ም. ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥራት ጀምረው ፍጻሜውን ሳያዩ እርሳቸው ቢያርፉም፤ በ1919 ዓ.ም. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቋል፡፡ በ1929 ዓ.ም. በሶማልያ በኩል በገባው የፋሽስት ኢጣልያ ጦር ገዳሙ ተዘርፏል፥ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንም ፈርሷል፡፡ በወቅቱ በገዳሙ ከነበሩት ከ500 በላይ መነኰሳት መካከል ከፊሉ ታቦቱን ይዘው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲሸሹ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ከጣሊያን ወረራ በኋላ መነኰሳቱ በ1936 ዓ.ም. ተሰባስበው ወደ አሰቦት መጡ፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በ1952 ዓ.ም. ተሠራ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሶማሊያ ኢትጵያን ስትወርር ገዳሙ ላይ አደጋ ለመጣል የመጡ ጠላቶች በተአምራት ያለቁበት ነበር፤ የጃራ ጦር የሚባሉ ገዳሙን ለማጥፋትም መጡ ጠላቶች እንዲሁ በተአምራት አብደው የተመለሱበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ግንቦት 16 ቀን 1984 ዓ.ም. በአክራሪ ኃይል የገዳሙን መነኰሳትና የአካባቢው ምዕመናን ላይ የከፋ አደጋ ጥሏል፤ ብዙዎችም ሰማዕት ሁነዋል፡፡
በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡ ለአብነትም በ1972ዓ.ም. ሐምሌ 7 ብዙ ሰው እያያቸው አባ መዘምር የተሠወሩበት ታለቅ ገዳም ነው፡፡
የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘፍቅዳቲሁ ራብዕ፤
ውእቱ ልኩእ ዲበ ረቀ ሰማይ ሳብዕ፡፡
ሊቀ ካህናት ሳሙኤል ዘደብተራ ሐዲ ምሥዋዕ፤
አስተስሪ ኀጣውእየ በደመ ነቢብ በግዕ፤
ለቤዛ ሙታን ዘሞተ በግፍዕ፡፡
(ሳሙኤል ሆይ ቊጥሩ ዐራት ለኾነ በሰባተኛው የሰማይ ብራና(ወረቀት) ለተጻፈ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፤ የሐዲስ መሠዊያ አገልጋይ፥ የካህናት አለቃ ሳሙኤል ሆይ፤ ለሰዎች ቤዛ ለመኾን በግፍ በሞተ በነባቢ ክርስቶስ ደም ኀጢአቴን አስተሥርይ፡፡)
/ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት በበረከት በጤና ይጠብቅልን፡፡/

❤14
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)
፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፭ኛ ሳምንት፥
ዘጥቅምት ፴፤ በዓለ ቅዱስ ማርቆሰ ወንጌላዊ፡፡
✤ ልዩ_አዋጅ_ዘወርኃ_ጽጌ_ ✤
ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን(የሸዋን) የተከተለ ነው፤
የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡
የጥቅምት_30_የማኅሌተ_ጽጌ_ወረቦች_፤ በደብራችን ሊቃውንትና መምህራን፡፡ ድምፆቹን በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፤
5.1. ወረብ ፩.፩፤ ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪወላዲተ አምላክ፤/ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም) ፤ (በአጋፋሪ ይሁኔ)
ወረብ ፩.፪፤ ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ /ዘጎንደር/ (በ…)
5.2. ወረብ ፪፤ እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ (በ…)
5.3. ወረብ ፫፤ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ(፪) ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ (በ..)
5.4. ወረብ ፬፤ ንዒ ኀቤየ ምስለ መላእክት(፪)፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በሊቀ ጠበብት ይልማ የደብራችን የአቋቋም መምህርና በኢትዮጵያ ደረጃ የአቋቋም ተጠያቂና መምህር በሆኑት በመምህር ዳዊት)
5.5. ወረብ ፭፤ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ (፪)ዘየኀቱ እምዕንቈ ባሕርይ፤ (በ…)
5.6. ወረብ ፮፤ ሰአሊ ለነ ማርያም ሰአሊ ለነ ፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በመሪጌታ ተክለ ያሬድ)
5.7. ወረብ ፯.፩፤ ኅብረ ሐመልሚል(፪) አርአያ ኰሰኰስ፤ /ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም (የቤቱ ቀለም)፤ (በአጋፋሪ ይሁኔና በአጋፋሪ ዳዊት)
5.8. ወረብ ፰፤ጥቀ አዳም(፪) መላትሕኪ ጥቀ፤ (በ..)
5.9. ወረብ ፱፤ ናዝሬት ሀገሩ አብርሂ/፫/ ናዝሬት፤ (በ…)
5.10. ወረብ ፲፤ ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን(፪)
ወረብ ፲.፪.፩፤ ተመየጢ(፪)ማርያም ሀገረኪ ናዝሬት፤ (በ…)
ዓዲ፤ ወረብ ፲.፪.፪፤ ተመየጢ(፪)እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ (በ…)
5.11. ወረብ ፲፩፤ ሃሌ ሉያ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ (በ…)

❤25