በአዲስ አበባ የመድኀኔ ዓለም ክብረ በዓል ያለባቸው አብያተ ክርስቲያናት #ጥቂቶቹን እንጠቁማችሁ፤ (ስብስብ 2)
👉 በየአካባቢያችሁ ያሉትን የመድኀኔዓለም አድባራት በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልን፤ ያሏችሁንም ፎቶዎች አጋሩን።
1) ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ፤
በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡
(በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)
2) ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉኀን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን (ታሪኩን በሰፊው በቀጣዩ ፖስት ይልከቱ)
3) ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔዓለም፤ (ታቦተ ሕጉ ባይወጣም በሰዐታትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡)፤ 6 ኪሎ
4) አቃቂ ጋራው መድኀኔዓለም፤
5) ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኀኔዓለም፤ረጲ
6) መንበረ ሕይወት መድኀኔዓለም፤ አቃቂ ክ/ከተማ
7) ደብረ ቅዱስ ደብረ ቀራሜሎስ ካራአሎ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ፤ የካ ክ/ከተማ
8) መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም፤ የካ ክ/ከተማ
9) ቦሌ ቡልቡላ ደብረ ገነት መድኀኔ ዓለም፤ቦሌ ቡልቡላ
10) ድልበር መድኀኔዓለም፤ ጉለሌ (ቶታል)
11) ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ.ክ ልደታ ሜክሲኮ
12) ደብረ ሳሌም ቦሌ መድኀኔዓለም ወቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን
13) ምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔዓም ቤተክርስቲያን፤ቀበና
14) አያት መድኃኔዓለም፤ አያት
15) ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔዓለም፤ደቡባዊ አ.አ
16) ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡
17) ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል ፡፡ ጎተራ
18) የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ወኢሉጣ ቤ.ክ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፤ ለገሃር
19) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡
20) ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል)
21) መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም ቤ.ክ (የመድኀኔዓለምና የመብዓ ጽዮን ታቦት በድርብነት ይገኛል)
22) ኮተቤ(ሲምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል)

❤13
ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤
የ114 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የልጅ ኢያሱ ደብር፤ ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመችው፡፡)
የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ መድኀኔዓለም ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤
የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤
ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡
#አጽዶቹ ሳይቀሩ በቁጥር በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት።
በጣሊያን ወረራ ወቅት እንኳን አንድም ቀን አገልጎሎት ያልቋረጠበት፤ 365 ቀን በሰዓታቱ፣ በማኅሌቱ፣ በመቅደሱ ያለ ማቋረጥ የምስጋና ወንዝ የሚፈስበት፤ ሁልጊዜ ወር በገባ ከ፩ አስከ ፯ ምሕላ የሚደርስበት።
አረጋውያኑ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በአዘቦት ቀን ለቅዳሴ እና ለጸሎት የሚገኙበት፤ የስውራን ቅዱሳን አባቶች መናሐሪያ የሆነ፤
ከጥንት ዘመን እስከ ዛሬ መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ በብቸኝነት የሚቀድስበት ደብር
#ፍጹም መንፈስ ቅዱስ የረበበት ታላቅ እና ልዩ ደብር ነው፡፡
✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም፤ በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡

❤22🥰3
ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥቅምት ፳፯
በዓለ መድኀኔዓለም ወመብዓ ጽዮን
✤ ልዩ አዋጅ ዘጥቅምት መድኀኔዓለም ✤
የጥቅምት መድኀኔዓለም የማኅሌቱ ሥርዐት ‹‹የመልክአ መድኀኔዓለምን›› እና ‹‹የመልክአ መስቀልን›› የሚከተል ነው፡፡
‹‹የመልክአ መድኀኔዓለም››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘአዲስ አበባ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የሚለውን እንዲከተሉ፤
‹‹የመልክአ መስቀል››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም›› የሚለውን እንዲከተሉ እናሳስባለን፡፡
✤ መልካም በዓል ✤
https://t.me/finotehiwott

❤39🙏4