በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።
የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።
በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ ከተማ ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።
በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል።
©ማኅበረ ቅዱሳን

😢61❤15🤝1
#ጥቅምት_20_በዓለ_ልደቱ_ለኤልሳዕ_ነቢይ
#በዓሉ_በእንጦጦ_ራጉኤል_ይከብራል።
ኤልሳዕ የስሙ ትርጒም “እግዚአብሔር ደኅንነት ነው” ማለት ነው፡፡ነቢዩ ኤልሳዕ እጅግ ባለጠጋ የሆነ ሰው ነበር።
ከዕለታት በአንደኛ ዕለት በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።
የኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ አድሮበት ለረጅም ጊዜ እግዚአብሔርን አገለገለ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኢያሪኮ ከተማ በሚገባበት ጊዜ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ እንደመጣ ባዩ ጊዜ “የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ውኃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች” አሉት፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ይህን ልመና ለኤልሳዕ ያቀረቡት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ነገርን ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ይታመኑ ስለነበር ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሰዎቹን ችግር ከተረዳ በኋላ የከተማውን ሰዎች አዲስ ማሰሮ እና ጨው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ሰዎቹም ኤልሳዕ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አዲስ ማሰሮ በውስጡ ጨው አድርገው አመጡለት፤ ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ ውሃው ምንጭ ወደ አለበት ስፍራ መጥቶ ጨው ጣለበት እና “እግዚብሔር እንዲህ ይላል ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፉ አይሆንበትም” ብሎ ለከተማው ሰዎች ተናገረ፡፡ ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ከዛ ጊዜ ጀምሮ ንጹሕ ውሃ መጠጣት ጀመሩ፡፡ የምድሪቱንም ፍሬ ተመገቡ፡፡ እግዚአብሔር በነቢዩ አልሳዕ ድንቅ ነገር ሰለአደረገላቸው ዘወትር ያመሰግኑ ነበር፡፡
እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች።
ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነቢይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት19 ላይ በስፋት ተጽፏል ጥቅምት 20 ልደቱ ሲሆን ሰኔ 20 ቀን ደግሞ በዓለ እረፍቱ ነው።
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

❤21👍1
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)
(፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፬ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፳፫)
በዓለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት፡፡
✤፠ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤ ፠
ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን(የሸዋን) የተከተለ ነው፤
የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡
https://t.me/finotehiwott

❤80🙏11👍3
እንኳን ለቸሩ አምላካችን #ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል) እና #ለአቡነ_መብዓ_ጽዮን ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡
በመላው ሀገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት #በጣም #ጥቂቶቹ፤ (በየአካባቢያችሁ ያሉትን የመድኀኔዓለም አድባራት በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልን)
1) ዋልድባ አብረንታት መድኀኔዓለም ገዳም
2) ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም (ከ1,455 ዓመታት በፊት የታነጸ፤ ደቡብ ወሎ፤ ጃማ
3) ላሊበላ ቤተ መድኀኔዓለም
4) ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም
5) መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና
6) ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ
7) ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ
8) ጨነቅ ዋሻ መድኀኔዓለም፤
በቅዱስ ላሊበላ በዋሻ ውስጥ እንደገና ፎቅ ተደርጎ የተፈለፈለ፤ በሰሜን ተራሮች (በራስ ደጀን) እግር ሥር የሚገኝ፤ በፓርክ ክልል ውስጥ በመኾኑ በብዙ ኢትዮጵያውያን የማይታወቅ፤ ነገር ግን ብዙ ተዓምራትን የሚያደርግ እጅጉን ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበት፡፡
9) መናገሻ ጋራ መድኀኔዓለም፤
ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡
10) ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤
ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡
11) ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም
12) አርብዓሐራ ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም፤
ደመ ክርስቶስን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል የተቀበለበትን የብርሃን ጽዋ የሚያጥኑ ቅዱሳን እና የሌሎችን ቅዱሳንን አጽም በንሥር አሞራ የተመሰለ የጌታ መልአክ በቀስተ ደመና ተከብቦ በቀን የሚያመጣበት፤ እልፍ ታሪክና ብዙ፥ የብዙም ገቢረ ተአምራት የሚፈጸሙበት፤ ለተፈቀደላቸውና እንደሚገባ ሆነው በቦታው ላይ በበጎ ኅሊና ለሚጸልዩ ምዕመናን ሥውራኑ እየተገለጡ ጥያቄያቸውን የሚመልሱበት፤ ግርማ ያለው ክቡር ንዑድ የ40ዎቹ ቅዱሳን ሰማእታት መካነ ጸሎት የአቡነ ሐራ ግብፃዊ የቃልኪዳን ሥፍራ
13) ጨጨሆ መድኀኔዓለም፤ ወሎና ጎንደር ድንበር ላይ
14) በደሌ ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ ከ100 ዓመት በላይን ያስቈጠረ ጥንታዊ ቤ.ክ.
15) ደሴ ደብረ መድኀኒት መድኃኔዓለም፤ በ3ወር ከ14ቀን ተሠርቶ የተጠናቀቀ፤ በ1905 በንጉሥ ሚካኤል የተሠራ
16) ሬማ መድኀኔዓለም፥ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ገዳም፤ በ1414ዓ.ም በአቡነ ኖብ የተመሰረተ፤ የእናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አጽሟ የሚገኝበት፤ ጣና ሐይቅ
16) ወዘም ባሕታዊ መድኃኔዓለም፣ ፍቼ አጠገብ ሰሜን ሸዋ
17) ደጀን አበ ብዙኃን አብርሃም ወመድኃኔዓለም፤ ደጀን ጎጃም
18) አርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ አርባ ምንጭ ከተማ
19) ቦራራ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
20) ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ወቅዱስ ላሊበላ ቤ.ክ፤ ጎንደር
21) ጌቴ ሴማኔ ፈረስ ቤት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ደብረ ማርቆስ
22) ወልዲያ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም፡፡
23) መቅደላ መድኀኔዓለም
24) ባሕር ዳር ድባንቄ መድኄኔዓለም
25) አዴት መድኃኔዓለም
26) አዲስ አምባ መድኃኔዓለም፤ ከ1600 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ሙሴ የተፈለፈለ የዋሻ ገዳም
27) ወንጪት መድኃኔዓለም፤ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግስት ተመስርቶ እስካሁን ድረስ ነብር በቤተ መቅደሱ እየኖረ በሚጠብቀው፤ በታላቁ ወይን እንጨት ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ውስጥ የተሰራ
28) መቀለ ደብረ መድኀኒት መድኃኔዓለም
29) አድግራት መድኃኔዓለም ወቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳም፤ ብዙ ድንቅ ታሪክ ያለው
30) ደባርቅ መድኃኔዓለም
31) የሽረት መድኃኔዓለም እጅግ ተደንቀውና ተደምመው ምስጋናዎ ኢምንት ሆናብዎት የሚመለሱበት
32) ኮሶ በር መድኃኔዓለም
33) ሐረር መድኃኔዓለም
34) ምስካበ ቅዱሳን ጻድቃኔ ዋሻ መድኃኔዓለም ገዳም
34) እመኪና መድኃኔዓለም ገዳም፤ በመናኔው ጻድቅ ንጉሥ በአጼ ካሌብ ልጅ፥ በጻድቁ ንጉሥ በአጼ ገብረ መስቀል፥ በ6ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረተ ታሪካዊ ገዳም
35) በሬ አገር መድኃኔዓለም ገዳም፤ 1000 ሜትር ፍልፍል ዋሻ ገዳም
36) ተከዜ መድኃኔዓለም ገዳም፤
በ11ኛው መ.ክ.ዘ. የላስታ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም /ታላቁ ሐርቤይ/ ደቀ መዝሙር፤ እንደነ ነቢዩ ኤልያስና ወንጌላዊው ቅ.ዮሐንስም ሞትን ሳያይ እስከ ምጽዓተ ሐሳዊ መሲህ /ዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ዋዜማ/ ድረስ የተሰወረው፤ ጻድቁ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ከሰማይ ተቀብሎ የመሰረተው፤ ንዑድ ክቡር የሆነ መካነ ጸሎት ወአርምሞ ወትኅርምት
37) ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም
38) ናዝሬት መድኃኔዓለም
39) ምስካበ ቅዱሳ ዋሻ መድኃኔዓለም፤ ሰላ ደንጋይ፤ ጻድቃኔ አካባቢ)
40) ሰቃ መድኃኔ ዓለም፤ ለሚ፤ እንሳሮ
41) ገነተ ቅዱሳን ዋሻ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ደብረ ማርቆስ አካባቢ፤
42) ጅፋ መድኃኔዓለም፤ ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ፤ በዱሮው አጠራር መረሂመኖ፤ ከታች ተንታ ቅዱስ ሚካኤል 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ፤ ጥንታዊ ቤ.ክ.
43) ኦቦራ ዓለምገና ደብረ ገሊላ መድኃኔዓለም፤ ባሌ
44) ጎባ ደብረ ገነት መድኃኔዓለም፤ ባሌ
45) አዳባ መድኃኔዓለም፤ ባሌ
46) ዙላ መድኃኔዓለም፤ ባሌ

❤16