Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር  መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። 

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።

በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል።

©ማኅበረ ቅዱሳን
😢6115🤝1
#ጥቅምት_20_በዓለ_ልደቱ_ለኤልሳዕ_ነቢይ
#በዓሉ_በእንጦጦ_ራጉኤል_ይከብራል

ኤልሳዕ የስሙ ትርጒም “እግዚአብሔር ደኅንነት ነው” ማለት ነው፡፡ነቢዩ ኤልሳዕ እጅግ ባለጠጋ የሆነ ሰው ነበር።

ከዕለታት በአንደኛ ዕለት በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ አድሮበት ለረጅም ጊዜ እግዚአብሔርን አገለገለ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኢያሪኮ ከተማ በሚገባበት ጊዜ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ እንደመጣ ባዩ ጊዜ “የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ውኃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች” አሉት፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ይህን ልመና ለኤልሳዕ ያቀረቡት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ነገርን ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ይታመኑ ስለነበር ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሰዎቹን ችግር ከተረዳ በኋላ የከተማውን ሰዎች አዲስ ማሰሮ እና ጨው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ሰዎቹም ኤልሳዕ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አዲስ ማሰሮ በውስጡ ጨው አድርገው አመጡለት፤ ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ ውሃው ምንጭ ወደ አለበት ስፍራ መጥቶ ጨው ጣለበት እና “እግዚብሔር እንዲህ ይላል ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፉ አይሆንበትም” ብሎ ለከተማው ሰዎች ተናገረ፡፡ ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ከዛ ጊዜ ጀምሮ ንጹሕ ውሃ መጠጣት ጀመሩ፡፡ የምድሪቱንም ፍሬ ተመገቡ፡፡ እግዚአብሔር በነቢዩ አልሳዕ ድንቅ ነገር ሰለአደረገላቸው ዘወትር ያመሰግኑ ነበር፡፡

እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች።

ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነቢይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት19 ላይ በስፋት ተጽፏል ጥቅምት 20 ልደቱ ሲሆን ሰኔ 20 ቀን ደግሞ በዓለ እረፍቱ ነው።

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
21👍1
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)
(፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፬ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፳፫)
በዓለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት፡፡
✤፠ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤ ፠
 ማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን(የሸዋን) የተከተለ ነው፤
 የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡
https://t.me/finotehiwott
80🙏11👍3