Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ ፡፡
ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ማኅሌት ማለት ምስጋና፣ ማወደስ ማለት ሲኾን፤ ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ያለው ማለት ነው፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም እና የማሕፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ በዳዊት መዝሙር መጠን በ150 እንዲሁም እንደ መልክዕ በባለ 5ት መስመር ግጥም ተደርጎ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡
ጽጌ የዘመን (የወራት) ስምም ይኾናል፤ ዘመነ (ወርኃ) ጽጌ 40 ቀን ነው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ነው፡፡ በዚህ ወራት የሚጾመው ጾም ጾመ ጽጌ ሲባል ጾሙም የፈቃድ ጾም ነው፡፡
በሀገራችን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀመራል፡፡ ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበት እና ሜዳዎችን እና ተራሮችን የሚስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችንን በአበባ እየተመሰሉ በምሥጢራዊ ግጥም ቀርበዋል፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግልም የአበቦችን ነገር ከእመቤታችን ስደት ጋር እያደረገ፣ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን እያጣቀሰ ማኅሌተ ጽጌ (የአበባ ማኅሌት) የተባለውን ጸሎት ደርሷል፡፡
በዘመነ ጽጌ ወቅት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ማኅሌት ይቆማል፤ የሚቆመው ቁመትም አባ ጽጌ ድንግል የደረሱት ማኅሌተ ጽጌና ሰቈቃወ ድንግል ነው፡፡
አባ ጽጌ ድንግል ጓደኛቸው አባ ገብረማርያም የጀመሩትን ማኅሌተ ጽጌ አብነት በማድረግ በተለይም በጎንደር ዘመነ መንግሥት በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቊም ማርያም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት መቆም ተጀምሯል፤ ቆይቶ ግን ይህ ማኅሌት ወደ ዘንሥር ዮሐንስ ማእከላ ለጎንደር ተዛውሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ሲቆም ቆይቶ በመምህር ተክሌ ጊዜ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ተዛውሮ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት በብቸኝነት በዚህችው ደብር የጎንደር አድባራት ሊቃውንት በመሰባሰብ ሲቆም ቆይቷል፤ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ ባሊ አብያተ ክርስቲያናትም የጽጌ ቁመት ተስፋፍቷል፡፡
ከ1999(2000)ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋምና የተወሰኑ የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ጀምረዋል፤ ነገር ግን ቢጀምሩም ቅሉ አሁንም ግን የጎንደር አድባራት ሊቃውን በዋነኛነት በመካነ ነገሥት ግምጃቤት እየተሰባሰቡ የሚቆሙት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት እጅግ በጣም ልብን የሚማርክና ኅሊናን የሚመስጥ በሃገራችን በኢትዮጵያ ደረጃም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡
በሌሎች የሃገራችን ክፍሎችና በመዲናችን በአዲስ አበባ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የአገልጋይ ካህናት እጥረት በሌለባቸው ኹሉ ይቆማል፡፡
ሰቈቃወ ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ፥ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ወይም /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርከ ሥሉስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡

ፎቶዎቹ፤
ቤተ ክርስቲያኖች
*ደብረ ጽጌ ገዳም፤ የአባ ጽጌ ደንግል ገዳም፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት፤ ወሎ ወግዲ አጠገብ፤ ኅዳር 6 ይከብራል፡፡
*ጎንደር ደብረ ፀሐይ ማርያም፤ ለበርካታ ዘመናት ማኅሌተ ጽጌ ይቆምባት የነበረች ታላቋ ደብር፡፡
*ጎንደር ዘንሥር ዮሐንስ፤ እስከ አፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ ይቆሙበት የነበረ ደብር፡፡
*ጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም፤ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ እስከ አሁን ድረስ የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ የሚቆሙባት ታላቂቷ ደብር፡፡

መምህራን
መምህር ተክለማርያም ፤ የታለቁ ገዳም የማኅበረ ሥላሴ አበምኔት፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት መምምህር፤ የድጓና የአቋቋምም መምህር፤ የጎንደር አድባራት በጋራ በመኾን የማኅሌተ ጽጌን ቁመት በአንድ ላይ ይቆሙበት ከነበረው ዘንሥር ማዕከላ ለጎንደር ዮሐንስ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ያመጡ ታላቁና ይህ ቀረሽ የሚይባሉ ሊቅ
✤፠ መምህር ክፍለ ማርያም ይመር፤ የመጻሕፍት ትርጓሜ ብርሃን፤ የየቀኑን  ምሥጢር ከድጓ፣ ከጾመ ድጓ፣ ከዝማሬ መዋሥዕት፣ ከቅዳሴ፣ ከሰዐታት እየተመለከቱና እያውጣጡ ዚቁን ያዘጋጁ፤ ይህ ቀረሽ የማይባሉ የሊቆች ሊቅ፡፡
✤፠ ሊቀ ማዕምራን ወመጋቤ ሐዲስ ወሰንበት ባይነሳኝ፤ የጽጌ ዚቅን (የላይ ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ዋና ምስክርና የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ዋና አስተዳዳሪ፤ የሚያስተምሩት የሚኖሩ፤ ሊቅነትና ከትሕትና የያዙ፤ ከቀደምት ዐበይት ሊቃውንት መካታቻ የሆኑ፤ በቅርቡ ያረፉ፤ ጕባኤ እያሄዱ (እያስተማሩ) የሚያሳይ ፎቶ
✤፠ ሊቀ ማዕምራን ሐዋዝ ጥሩነህ፤ የግምጃ ቤት ማርያም አለቃ፤ ከላይ የተጠቀሱ ሊቃውንት የደረሱትን ዚቅ በእጅ ጽሑፍ ለትውልድ ያቆዩ ብልህ አስተዳዳሪ፡፡
✤፠  መምህር ክፍሌ ወለደ ጻድቅ፤ የጽጌ ዚቅን (ዚቅን) (የታች ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ የአቋቋም ዋና ምስክር የነበሩ፡፡ የአሁንን ዝክረ ቃልን በቀድሞ ስሙ አባጃሌ የተባለውን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት ያበቁ፡፡
መምህር ላዕከ ጊዮርጊስ ደምሴ፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት ምክትል መምህር የነበሩና ዜማ አዋቂ ምሁር፤ በወርኃ ጽጌ የዕለቱን ምሥጢር በተመለከተ ዚቅ እያዘጋጁ ለሊቃውንቱ ያቀርቡ የነበሩ
✣✤✣ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም፤ ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ባለውለታ የኾነች ጥንታዊት ቤ.ክ.፤ በደርቡሽ ወረራ ጊዜ መመህራን ጕባኤያችንን (ማስተማራችንን የታሪክ መዘክርነታችንን) ለቅቀን አንሔድም በማለት ሰማዕት የኾኑባት፡፡ **የብዙ ሊቃውንተ መፍለቂያ፤ እስከ ዐፄ ኀይለሥላሴ ዘመን ድረስ (ከሠለስቱ ምዕትና ከልደታ አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ ቤት በመቀጠል) በሃገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የታች ቤት የመጻሕፍት /አንድምታ ትርጓሜ/ (የ4ቱ ጕባኤያት) ብቸኛ ማስመስከሪያ፡፡ /በአሁኑ ሰዓት በዋነኛነት በኢትጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ ሐዲሳት የታች ቤት ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (university)/፡፡ እዲሁም የላይ ቤት የአቋቋም የዜማ የድርሰት ማዕከልና ዋና አብነት  ነች፡፡ በውስጧ ተዓምረኛ የኾነች የእምቤታችን ሥዕል ይገኝባታል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
14👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የዘመነ አበው ቀደምት ማኅሌት

ዛሬ በአፀደ ነፍስ ያሉ አባቶቻችን ሊቀ መዘምራን ሰምረ ወሌ፣ ሊቀ ጉባኤ አድማሱ ውበቱ ፣መምህር መርአዊ፣ መጋቤ ምስጢር መንግስቱ፣ሊቀ ጠበብት ምሕረቱ፣መዘምር ዘውገ እርገጤ፣ መዘምር ንጉሴ ሀብተ ወልድ፣መምሬ ታፈሰ፣ሊቀ አበው መኮንን፣ሊቀ አበው ሽፈራው፣መምሬ ካሳ፣መምሬ እስጢፋኖስ..... የሚገኙበት የዛሬዎቹ አበው በውርዝውና ዘመናቸው ሳሉ... በትውስታ ወደኋላ የጎተተን ማኅሌት

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
28🙏4
ዘጥቅምት ፱፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፪ኛ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፱)
በዓለ እስጢፋኖስ ካልዕ ወቶማስ ሰማዕት ዘመርዓስ፡፡

✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤
✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው

✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

✤በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምን፤ ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡✤

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
22
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ፊልጶስ_
** በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ ቅዱስ ፊልጶስ ዕረፍቱ ነው፡፡
✤ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ባለውለታችን (በእግዚአብሔር ፈቃድ ሰማያዊውም ሆነ ምድራዊውን ውለታ የዋለልን) የኾነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔርን ቃል የተናገረን፤ የክርስትና ጥቀምት አባትና አጥማቂያችን ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የኾነው ቅዱስ (ሐዋርያው) ፊልጶስ #በሀገራችን__ብቸኛ_በኾነውና በአ.አ ኮልፌ አጠና ተራ በሚገኘው ቤ.ክ. #ደብረ_ምጥማቅ-ቤ.ክ በዓለ ዕረፍቱ ይከበራል፡፡
" እነሆ በውሀ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው? " የሐዋርያት ሥራ ፰÷፴፮
**በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውና በአዲስ አበባ የሚገኘው ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ቤ.ክ የተመሠረተው በ3ኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆን፤ የቅዱስ ፊልጶስ ክብረ በዓል በዓመት 2ት ጊዜ ነው፤
#ጥቅምት 14 በዓለ ዕረፍቱ
#የካቲት 20 ቅዳሴ ቤቱ ነው
‹‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።"ዕብ. 13፥7
፠፠፠ ‹‹ደብሩሰ ለቅዱስ ፊልጶስ ትመስል ደብረ ሲና፤
ወሀደረ ላዕሌሃ እግዚአብሔር ሐፁር የዐውዳ ወጽጌረዳ በትምዕርተ መስቀል፡፡››

#አድራሻ_- ኮልፌ አጠና ተራ ወደ፡ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ኢንዱስትሪ መንደር ሳይደርሱ
፠1. ከመርካቶ በባስ ቁጥር 69 ጠሮ በሚወስደው መንገድ፣21 ልኳንዳ ወርደው ወደ ቀድሞ 04 ቀበሌ
፠2. ከአየር ጤና እና ዙሪያው በባስ ቁጥር 87 አጠና ተራ ወርደው የቀለበት መንገድ የእግረኛ መሻገሪያ ተሻግረው ባለው አስፋልት ቀጥታ በመሄድ ያገኙታል
፠3. ከቡራዩ አስኮ አካባቢ ለምትመጡ በባስ ቁጥር 28 አጠና ተራ ወርደው በቀኝ በኩል ባለው አስፋልት ቀጥታ በመሄድ ያገኙታል።
27👍1🙏1