Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ!!!!
ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. (ዳግመኛ የማይገኝ ግብዣ፤ እንዳያመልጥዎ!!!)

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በኪደቱ እግሩ መጥቶ በጸለየበት እንጦጦ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ራጕኤል ወኤልያስ ቤ/ን (በአዲስ አበባ ጻድቁን በመዘከር 2ኛ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ) ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል፡፡
ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡

ዋና ገዳማቸው የጋሥጫ ገዳም አባቶችና እናቶችም በአዲስ አበባ እንጦጦ #ዳቤ አዘጋጅተው ይጠብቁናል!!
ጥቅምት 3 ቀን 1357 ዓ.ም.፤ ጽንሰቱ፤
ሐምሌ 7 ቀን 1358 ዓ.ም. ልደቱ፤
ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም. ዐረፍቱ ነው፡፡

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
፠ ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ ጸሓፊና አታሚ፥
፠ ቅዱስና ጻድቅ፥
፠ ፈላስፋና ደራሲ፥
፠ መናኝና ባሕታዊ፥
፠ ሊቅና ተመራማሪ፥
፠ ገጣሚና ባለቅኔ፥
፠ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥
፠ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፡፡
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ደብረ_ባሕርይ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ወደብረ_ጎል_አባ_በጸሎተ_ሚካኤል_ገዳም
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ባሕርይ፤
ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ከላላ፡፡
ወይም፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐቤቴ (መርጡለ ማርያም) → ከላላ፡፡

፪. #ደሴ_መስቀለ_ክርስቶስና_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገ ስብከት፥ ደሴ፥ ጦሳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → ደሴ → ጦሳ፡፡

፫. #አ.አ. #ፈረንሳይ #መድኀኔዓለም_ወአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
አድራሻ፤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ ኢየሱስ ከፍ ብሎ፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (4 ኪሎ) → ፈረንሳይ ኢየሱስ፡፡

፬. #ርዕሰ_አድባራት_ወገዳማት_እንጦጦ_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ራጕኤል_ወኤልያስ_
አድራሻ፤ አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (4ኪሎ) → ሽሮሜዳ → ቊስቋም → ራጕኤል፡፡
/ #ክብረ_በዓላት #Feasts /
/ #ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches /
17
#አቡነ_በርተሎሜዎስ_ዘደብረ_ዘመዳ
፠ተወልደው ያደጉት በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሸዋ ቡልጋ፤ በጥራ መረዋ አካባቢ ነው፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ሚስት አጭተው ቢያጋቡትም፤ እንደ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ጠብቆ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ ወግር ወደሚባል ተራራ ሂዶ 40 ቀን ሱባዔ ገባ፡፡ ሱባዔውን እንደጨረሰም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባ፡፡
፠ በደብረ ሊባኖስ ገዳምም ከታላቁ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የምናኔ ሕይወትን ተማሩ፡፡
፠ምንኵስናን ከጓደኛቸው ከኤዎስጣቴዎስ ጋር አበአንድነት የተቀበሉትም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆን፤ ከትግራይ ወሰን እስከ አንገት ያለውን እንዲያስተምሩም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተልከዋል፡፡
፠ ወደ እንፍራንዝ (ጣና) ከጌርሎስ ከአኖሬዎስ ልጅ ዘንድ ሄደው ሰነበቱና ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡
፠ ክርስትናን ለማስፋት ተመርጠው ከተሾሙ ዓበይት ንቡራነ ዕድ አንዱ ሲሆኑ፤ የተሾሙበት ሃገረ ስብከታቸውም በቆባ፣ የጠጠርና የኮረም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ነው፡፡ በተለይም በወሎና በአፋር ድንበር አካባቢ ወንጌልን በትጋት አስተምረዋል፡፡
፠ 12ቱ ንቡራነ ዕድ ከያሉበት ሃገር ወደ ደብረ ሊባኖስ በመምጣጥ ወር ወር የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን አጽም ያጥኑ ነበር፤ የጻድቁ ዘቡነ በርተሎሜዎስ የማዕጠንት ተራቸውም በወርኃ ጳጕሜን ነበር፡፡
፠ አፄ ዐምደ ጽዮን የአባቱን ሚስት በማግባቱ ቅዱሳኑና ግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በመቃወማቸው፤ በአፄ ዐምደ ጽዮንና በልጁ በአፄ ሰይፈ አርዕድ መሰደድ ደረሰባቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ከጳጳሰ ጋር ወደ ግብጽ መሰደድ ጀመሩ ነገር ግን፤ አቡነ ያዕቆብ ለአቡነ በርተሎሜዎስ ጽላተ ማርያምን ሰጥተው እንዲመለሱ አደረጓቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ጽላተ ማርያምን በደብረ ዘመዳ በክብር አስቀመጣት፡፡
፠ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ ጥቅምት አርፈው በደብረ ዘመዳ ገዳም ዐጽማቸው በክብር አርፏል፡፡

#ደብረ_ዘመዳ_ማርያም_አቡነ_በርተሎሜዎስ_ገዳም (#ደብረ_ዠመዳ)
ገዳሙ የሚገኘው ወሎ ላስታ ውስጥ ሲሆን የመሠረቷት አቡነ በርተሎሜዎስ ናቸው፡፡
በዚህ ገዳም እንደ አኵሱምና ደብረ ሊባኖስ ሰዐታትና ማኅሌት ሁልጊዜም ይቆምባታል፡፡
በዚህ ገዳም በርካታ ጥንታውያንና ድንቅ የሆነ ቅርሶች አሉ፤
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ስዕል የምትገኘውም በዚሁ ገዳም ሲሆን፤ መልኳ የሚቀያየርና ቅዱስ ዮሐንስ የሚባል ደግ ሰው ነው ወደዚህ ገዳም ያመጣት፡፡
** ገዳሙ የሚጠበቀው በዋነኛነት እንደ ነብር ባሉ የዱር አራዊት ነው፡፡

፠፠፠የደብረ ዘመዳ ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበረው በጥቅምት 4 በአቡነ በርተሎሜዎስ በዓለ ዕረፍታቸው ቀን ነው፡፡
፠፠፠ ታላቁ ገዳም ደብረ ዘመዳ የሚገኘው፤ ሰሜን ወሎ ዋጃ ከተማ ከተደረሰ በኋላ የተወሰኑ ሰዓታት የእግር ጕዞ በመጓዝ ነወ፡፡

ከጻድቁ ከአቡነ በርተሎሜዎስ ረድኤት በረከት ይክፈለን፤ አሜን፡፡
/ምንጭ፤ ገድለ አቡነ በርተሎሜዎስ የብራና፤ የአማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፣ ዶ.ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዝክረ ቅዱሳንና ከገድላት አንደበት የፊት ገጾች፡፡)
/የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/
8
#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ አፄ ገብረመስቀል፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ …) እግዚአብሔርንም ሰውንም ያገለገሉ ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ ቅድስናን ከሐናፄ ቤተመቅደስነት ጋር ደርበው የያዙም ጭምር ናቸው፡፡ በዚህም በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሏቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው፤ ጽላት የተቀረጸላቸው፥ ገድል የተጻፈላቸው፤ (ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ የኾኑ) ቅዱሳን ናቸው፡፡
ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 364 ዓ/ም አጽብሐ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ/ም በሞተ ሥጋ አርፈዋል፡፡
ክብረ በዓላቸው በትግራይ ባለ ውቅር ገዳማቸው፤
በአዲስ አበባ ደግሞ፤
* * በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ
**በየካ ተራራ ዋሻ ተክለ ሐይማኖት
**በአያት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን፡፡
32🥱1
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም  ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)

፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)

ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤
*ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
*ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤

፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ#አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡

፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
#በግብፅ_300_ዓመታት_#በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥
ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡
፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤
ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡

አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
29
ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን)፤ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ
       ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለጸሎት፣ ለማስጋና፣ ለልመና እና ምዕመናኖቿን ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው  የመዝሙር እና የጸሎት መጻሕፍት መካከል አንዱ በ14ኛው መክ.ዘመን በተነሱት ሊቅ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው ማኅሌተ ጽጌ ነው፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ ብሎም ወደ ኢትዮጵያ መሰደድ እና መንከራተት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ሌሊት የሚደርስ ምስጋናና ጸሎት ነው፡፡
       አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን)
በ14ኛው መ.ክ.ዘ የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡ በንጉሥ ሰሎሞን ፈቃድና በካህኑ አዛርያስ መሪነት የብሉያት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ተርጕመው ሊያስተምሩ፣ ታቦተ ጽዮንን ከኢየሩሳሌም ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና የብሉያት መጻሕፍት ሊቃውንት ከነበሩት ከ318 ሌዋውያን (ከቤተ እስራኤላውያን) ነገድ ነው፡፡ የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ መጀመርያ ኢእማኒ (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር፣ ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሰው፤ በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማድን ወደ ጫካ ሄደ፣ ጫካዋም በዚያው በይፋት አውራጃ የምትገኝና ልዩ ስሟ ደንስ (ገዳመ ደንስ) ትባላለች፣ በጫካዋ ውስጥም ፈቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ፣ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሥዕሏን ሲመለከት እንደ እርሱ ያልተጠመቀ ጓደኛው መጥቶ፣ ‹‹ምን እየፈለግህ ነው? የክርስቲኖችን ሥዕል ነውን?›› ብሎ ለድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀሥፎ ሞተ፣ ከዚህ በኋላ ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ የመሰለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ፡ ወደ እርሱ መጥቶ አንድ ቀይ መነኩሴ እሰኪመጣ ድረስ፣ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ፣
የአቡነ ዜና ማርቆስ የገድል መጽሐፍ፣ እንደሚናገረው ካህን ከነበረው ከአባቱ ከዘርዐ ዮሐንስ አና ከእናቱ ማርያም ዘመዳ በ1262 ዓ.ም. ኅዳር 24 ቀን በሰሜን ሸዋ ግዛት በሚገኘውና ልዩ ስሙ እቲሳ ቅዱስ ሚካኤል በሚባለው አጥቢያ የተወለደው አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስራት ከሚባለው ገዳሙ ወደ ይፋት መጥቶ ከነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ከምዕ. 11፥1 ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ እያለ በግእዝ ቋንቋ ሲያነብ አባ ጽጌ ድንግል በሰማ ጊዜ አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ፤ ትርጕሙን ግን አላውቀውምና ተርጕምልኝ አለው፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጕምለት እንዲህ አለ፤ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ፤ እመቤታችን ተወልዳ፣ ከእርሷም ጌታ በድንግልና ይወለዳል፣ ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው፣ ይህም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል ብሎ ተረጐመለት፡፡ ኢሳ 7፥14፣ ማቴ18፥24፡፡
    ይህ ሰውም (አባ ጽጌ ድንግልም) በዚህ ትርጕም ደስ ተሰኝቶ አባት ሆይ የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጐምከው፣ መልካም ነገርንም ተናገርክ አለውና፣ ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው፣ በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው ብትር ሲመታት ወዲያውኑ እንደተቀሠፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ፣ ‹‹አንድ ነጭ ወፍ /ቅዱስ ሩፋኤል/›› ወደ እርሱ መጥቶ ቀይ መነኵሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው፣ አቡነ ዜና ማርቆስም ከሥዕሏ የተደረገውን ተአምር ሰምቶ፣ እጅግ ደስ አለውና በል መጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በፈጣሪ ልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ይህችን ሥዕል ያስገኘ፣ ሰማይና ምድርን፣ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፣ እርሱ እንደኾነ እውቅ አለውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ ጽጌ ብርሃን ብሎ ሰየመው፡፡
  ከዚህ በኋላ ሥዕሏን በገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስዶ በዘመነ ጽጌ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጣት የምትከብርትንም ቀን ጥቅምት 3 እና ሰኔ 8 ቀን አደረገ፡፡
    አቡነ ዜና ማርቆስም ጽጌ ብርሃንን ለመዓርገ ምንኵስና አበቃው፤ የአባ ጽጌ ብርሃንም ጽጌ ድንግል የሚል ቅጽል ስም አለው፣ በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፣ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እንደምትባርክ፣ ካህናቱ በግልጽ ይረዱ ነበር፣ አባ ጽጌ ብርሃንም ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር፣ የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜን ግን ከአቡነ ዜና ማርቆስ ተማረ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ላሉ አሕዛብ ሁሉ የድኅነት ምክንያት ትሆኑ ዘንድ ብርሃናቸው፣ መምህራቸው አደረግኋችሁ ብሉ ጌታ ነቢዩ ኢሳይያስንና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን እንደመረጣቸው፣ ኢሳ 49፥6.፣ የሐ.ሥራ13፥47 ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ስብከተ ወንጌልን እንደ ዕለት ጉርስና እንደ ዓመት ልብስ አድርጎ፣ መላ ኢትዮጵያን ዞሮ፣ አስተምሮና ባርኮ የዕድሜ ባለጸጋም ሆኖ በተወለደ በ140 ዓመት በ1402 ዓ.ም ታኅሣሥ 3 ቀን ፣ ዐርብ ጠዋት ዐረፈ፡፡
     አባ ጽጌ ብርሃንም በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፣ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሸመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን፣ እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ፡ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፣ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችን በአበባ እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ነው፨
     ሰቈቃወ ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርኬላዎስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡
   ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ የማያደርግ የሕግ ፍጻሜ ነውና፤ ሮሜ 13፥10-11፣ አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያምም የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር (በአንድነት) አገልግለዋል፣ ማለትም አንድ ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25፣ ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ገዳመ ጽጌ (ደብረ ብሥራት) ገብቶ ከመስከረም 26 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎትን ከአባ ጽጌ ብርሃን ጋር ፈጽሞ ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፤ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ
10
አባ ጽጌ

ብርሃን ከገዳመ ጽጌ (ከደብረ ብሥራት) ወደ ደብረ ሐንታ ሄዶ እንደዚሁ እንደ አባ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አገልግሎ ይመለሳል፣ እኒህ ሁለቱ ቅዱሳን ሊቃውንትም ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው እንዲህ እያደረጉ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍቅርና በትሕትና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡
ምንጭ  ፡- የማሕሌት ጽጌ ትርጕምና ታሪክ፣ የቤተክርቲያን መረጃዎች፣ መዝገበ ታሪክ፣ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት/
5