Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
የጥቀምት 2 የማኅሌተ ጽጌ ወረቦች፤ በሊቀ ጕባኤ ደምፀ አንበርብር፣ በሊቀ ጠበብት ኤርምያስና በደብራችን ሊቃውንት፡፡
1) 1 ጽጌ አስተርአየ
2) 2 ናሁ አስተርአየ
3) 3 እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ወረብ
4) 4) ንዒ ርግብየ ሐዋርያት (የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱ ቀለም)
5) 5 ክበበ ጌራ ወርቅ ወረብ
6) 6 ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት
7) 7 አርአዮሙ ለመምህራን
8) 8 ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን ወረብ
http://t.me/finotehiwott
28
እንኳን ደስ አላችሁ!!!!
ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. (ዳግመኛ የማይገኝ ግብዣ፤ እንዳያመልጥዎ!!!)

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በኪደቱ እግሩ መጥቶ በጸለየበት እንጦጦ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ራጕኤል ወኤልያስ ቤ/ን (በአዲስ አበባ ጻድቁን በመዘከር 2ኛ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ) ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል፡፡
ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡

ዋና ገዳማቸው የጋሥጫ ገዳም አባቶችና እናቶችም በአዲስ አበባ እንጦጦ #ዳቤ አዘጋጅተው ይጠብቁናል!!
ጥቅምት 3 ቀን 1357 ዓ.ም.፤ ጽንሰቱ፤
ሐምሌ 7 ቀን 1358 ዓ.ም. ልደቱ፤
ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም. ዐረፍቱ ነው፡፡

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
፠ ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ ጸሓፊና አታሚ፥
፠ ቅዱስና ጻድቅ፥
፠ ፈላስፋና ደራሲ፥
፠ መናኝና ባሕታዊ፥
፠ ሊቅና ተመራማሪ፥
፠ ገጣሚና ባለቅኔ፥
፠ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥
፠ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፡፡
#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ደብረ_ባሕርይ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ወደብረ_ጎል_አባ_በጸሎተ_ሚካኤል_ገዳም
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ባሕርይ፤
ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ከላላ፡፡
ወይም፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐቤቴ (መርጡለ ማርያም) → ከላላ፡፡

፪. #ደሴ_መስቀለ_ክርስቶስና_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገ ስብከት፥ ደሴ፥ ጦሳ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → ደሴ → ጦሳ፡፡

፫. #አ.አ. #ፈረንሳይ #መድኀኔዓለም_ወአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_
አድራሻ፤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ ኢየሱስ ከፍ ብሎ፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (4 ኪሎ) → ፈረንሳይ ኢየሱስ፡፡

፬. #ርዕሰ_አድባራት_ወገዳማት_እንጦጦ_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ራጕኤል_ወኤልያስ_
አድራሻ፤ አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ (4ኪሎ) → ሽሮሜዳ → ቊስቋም → ራጕኤል፡፡
/ #ክብረ_በዓላት #Feasts /
/ #ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches /
17
#አቡነ_በርተሎሜዎስ_ዘደብረ_ዘመዳ
፠ተወልደው ያደጉት በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሸዋ ቡልጋ፤ በጥራ መረዋ አካባቢ ነው፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ሚስት አጭተው ቢያጋቡትም፤ እንደ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ጠብቆ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ ወግር ወደሚባል ተራራ ሂዶ 40 ቀን ሱባዔ ገባ፡፡ ሱባዔውን እንደጨረሰም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባ፡፡
፠ በደብረ ሊባኖስ ገዳምም ከታላቁ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የምናኔ ሕይወትን ተማሩ፡፡
፠ምንኵስናን ከጓደኛቸው ከኤዎስጣቴዎስ ጋር አበአንድነት የተቀበሉትም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆን፤ ከትግራይ ወሰን እስከ አንገት ያለውን እንዲያስተምሩም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተልከዋል፡፡
፠ ወደ እንፍራንዝ (ጣና) ከጌርሎስ ከአኖሬዎስ ልጅ ዘንድ ሄደው ሰነበቱና ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡
፠ ክርስትናን ለማስፋት ተመርጠው ከተሾሙ ዓበይት ንቡራነ ዕድ አንዱ ሲሆኑ፤ የተሾሙበት ሃገረ ስብከታቸውም በቆባ፣ የጠጠርና የኮረም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ነው፡፡ በተለይም በወሎና በአፋር ድንበር አካባቢ ወንጌልን በትጋት አስተምረዋል፡፡
፠ 12ቱ ንቡራነ ዕድ ከያሉበት ሃገር ወደ ደብረ ሊባኖስ በመምጣጥ ወር ወር የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን አጽም ያጥኑ ነበር፤ የጻድቁ ዘቡነ በርተሎሜዎስ የማዕጠንት ተራቸውም በወርኃ ጳጕሜን ነበር፡፡
፠ አፄ ዐምደ ጽዮን የአባቱን ሚስት በማግባቱ ቅዱሳኑና ግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በመቃወማቸው፤ በአፄ ዐምደ ጽዮንና በልጁ በአፄ ሰይፈ አርዕድ መሰደድ ደረሰባቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ከጳጳሰ ጋር ወደ ግብጽ መሰደድ ጀመሩ ነገር ግን፤ አቡነ ያዕቆብ ለአቡነ በርተሎሜዎስ ጽላተ ማርያምን ሰጥተው እንዲመለሱ አደረጓቸው፤ አቡነ በርተሎሜዎስም ጽላተ ማርያምን በደብረ ዘመዳ በክብር አስቀመጣት፡፡
፠ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ ጥቅምት አርፈው በደብረ ዘመዳ ገዳም ዐጽማቸው በክብር አርፏል፡፡

#ደብረ_ዘመዳ_ማርያም_አቡነ_በርተሎሜዎስ_ገዳም (#ደብረ_ዠመዳ)
ገዳሙ የሚገኘው ወሎ ላስታ ውስጥ ሲሆን የመሠረቷት አቡነ በርተሎሜዎስ ናቸው፡፡
በዚህ ገዳም እንደ አኵሱምና ደብረ ሊባኖስ ሰዐታትና ማኅሌት ሁልጊዜም ይቆምባታል፡፡
በዚህ ገዳም በርካታ ጥንታውያንና ድንቅ የሆነ ቅርሶች አሉ፤
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ስዕል የምትገኘውም በዚሁ ገዳም ሲሆን፤ መልኳ የሚቀያየርና ቅዱስ ዮሐንስ የሚባል ደግ ሰው ነው ወደዚህ ገዳም ያመጣት፡፡
** ገዳሙ የሚጠበቀው በዋነኛነት እንደ ነብር ባሉ የዱር አራዊት ነው፡፡

፠፠፠የደብረ ዘመዳ ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበረው በጥቅምት 4 በአቡነ በርተሎሜዎስ በዓለ ዕረፍታቸው ቀን ነው፡፡
፠፠፠ ታላቁ ገዳም ደብረ ዘመዳ የሚገኘው፤ ሰሜን ወሎ ዋጃ ከተማ ከተደረሰ በኋላ የተወሰኑ ሰዓታት የእግር ጕዞ በመጓዝ ነወ፡፡

ከጻድቁ ከአቡነ በርተሎሜዎስ ረድኤት በረከት ይክፈለን፤ አሜን፡፡
/ምንጭ፤ ገድለ አቡነ በርተሎሜዎስ የብራና፤ የአማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፣ ዶ.ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዝክረ ቅዱሳንና ከገድላት አንደበት የፊት ገጾች፡፡)
/የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/
8
#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ አፄ ገብረመስቀል፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ …) እግዚአብሔርንም ሰውንም ያገለገሉ ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ ቅድስናን ከሐናፄ ቤተመቅደስነት ጋር ደርበው የያዙም ጭምር ናቸው፡፡ በዚህም በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሏቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው፤ ጽላት የተቀረጸላቸው፥ ገድል የተጻፈላቸው፤ (ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ የኾኑ) ቅዱሳን ናቸው፡፡
ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 364 ዓ/ም አጽብሐ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ/ም በሞተ ሥጋ አርፈዋል፡፡
ክብረ በዓላቸው በትግራይ ባለ ውቅር ገዳማቸው፤
በአዲስ አበባ ደግሞ፤
* * በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ
**በየካ ተራራ ዋሻ ተክለ ሐይማኖት
**በአያት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን፡፡
32🥱1