Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
#ነግሥ_ነግሥ_ነግሥ
በማንኛውም ወርኀዊና ዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ማኅሌት ሲቆም፤ መጀመሪያ የሚባለውን ነግሥንና የነግሥ መቅድምን አዘጋጅተንላችኋል፡፡
*ነግሥ ምን ማለት ነው
*ዚቅ ምን ማለት ነው
*የነግሥ መቅድምና ነግሥ
ቀመረ መረግድ፤ (ማንኛውም ማኅሌት ሲቆም ባለ 5 መስመር ግጥም ሲሆን እያንዳንዱ መስመር 28ት ጊዜ በከበሮና በጸናጽል ይመረገዳል ፤ የአመረጋገዱን ቅደም ተከተል እንዲቀላችሁ በማሰብ በቀመር (በቊጥር አስቀምጠንላችኋል፡፡) ከጽሑፉ ያገኟቸዋል፡፡
ይህን ነግሥ በሁሉም ማኅሌት መጀመሪያ የሚባል እንደመሆኑ መጠን በቃላችሁ አጥኑት፡፡
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/
t.me/finotehiwott
68🔥6🙏5👍1
✤✤ እንኳን ለማኅሌተ ጽጌ አደረሳችሁ

ምንም እንኳን በመጽሐፈ ገጽ (Facebook) ጽሑፎችን ማቅረብ ከጀመርን በርካታ ዓመታት ብናስቈጥርም፤  ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፈ ገጽ(Facebook) ፋና ወጊ ኾነን ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘን መቅረብ ከጀመርን ግን 12ኛ ዓመታችን ኾነ፤ እንደ መድኀኔዓለም ፈቃድም ዘንድሮም 12ኛ ዓመታችን (የ2ኛ ዙር ዓመት ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ሥርዐተ ማኅሌትና በዓመት ውስጥ የሚገኙ የክብረ በዓላት ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡)

✤ የማኅሌት ቁመት የላይ ቤትና የታች ቤት ኾኖ እንደየአድባራቱ ይትበሃል የሚቆም እንደመኾኑና ማኅሌተ ጽጌ በኹሉም አድባራት በደመቀ ኹኔታ ስለሚቆም የላይ ቤቱንም ኾነ የታች ቤቱን በአንድነት አቅርበንላችኋል፤ የላይ ቤት የምትቆሙ አድባራት ‹‹ዘግምጃ ቤት›› የሚለውን፤ የታች ቤት የምትቆሙ ‹‹ዘጎንደር በዓታ›› በሚል አስቀምጠንላችኋል፡፡ ደብራችን ቀጨኔ ደብረ ሰላም የላይ ቤት የሚቆምበት ደብር እንደመኾኑ ላይ ቤቱን እያስቀደምን ታች ቤቱን አስከትለን አስቀምጠናል፡፡ የላይ ቤት የሚቆምባቸው አድባራት የታች ቤቱን እየዘለሉ፤ የታች ቤት የሚቆሙ አድባራት የላይ ቤቱን እየዘለሉ እንዲጠቀመቡት ኹሉንም አዘጋጅተነዋል፡፡ የላይ ቤትና የታች ቤት በአንድነት የሚቆሙት ቀለም ሲኾን ግን ‹‹ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ›› ብለን አስቀምጠነዋል፡፡

/በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምንና ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡

✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤

✤ ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡

✤ የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው፡፡ ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡

✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤

1) ከማኅሌተ ጽጌ፦ ጽጌ አስተርአየ (የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብረ ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡

2) ከሰቈቃወ ድንግል፦ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡

✤ ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡

✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡

✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው

✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
26👏2
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)
(፪ኛ ዙር ዓመት፤ ፩ኛ ሳምንት፥ጥቅምት ፪)
በዓለ አባ ሕርያቆስ፡፡

http://t.me/finotehiwott
66🙏8👍5😢4🥰3👏2
የጥቀምት 2 የማኅሌተ ጽጌ ዚቅ፤ በደብራችን ርዕሰ ደብር ጥሩነህ፡፡
1) 1) መሥ- ለአፉክሙ… አሰርጎካ ለምድር-1
2) 2) ማኅ - ጽጌ አስተ… ናሁ አስተርአየ ጽጌ-1
3) 3) ማኅ- እንዘ ተሐቅ… ንዒ ርግብየ-1
4) 4) ማኅ - ክበበ ጌራ ወርቅ… ውድስት አንቲ-1
5) 5) ማኅ - ቅዳሴኪ ማርያም… አስተምሕር ለነ-1
6) 6) ሰቆ. በስመ እግዚ… እወ አማን-1
http://t.me/finotehiwott
11😢1
የጥቀምት 2 የማኅሌተ ጽጌ ወረቦች፤ በሊቀ ጕባኤ ደምፀ አንበርብር፣ በሊቀ ጠበብት ኤርምያስና በደብራችን ሊቃውንት፡፡
1) 1 ጽጌ አስተርአየ
2) 2 ናሁ አስተርአየ
3) 3 እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ወረብ
4) 4) ንዒ ርግብየ ሐዋርያት (የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱ ቀለም)
5) 5 ክበበ ጌራ ወርቅ ወረብ
6) 6 ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት
7) 7 አርአዮሙ ለመምህራን
8) 8 ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን ወረብ
http://t.me/finotehiwott
28