ለ64 ዓመታት ታላቁን ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምን በጸሎት ያገለገሉት ጸሎተኛው አባት አባ ወልደ አረጋዊ ዐረፉ፡፡
፨ ‹‹ወኢትጸመም ሞቶ ለዘተልአከከ (ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል አትበል)፡፡›› ሲራ. 38÷16
ሁልጊዜም ጠዋት ጠዋት ከደወል ቤት ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ጸሎት ማድረስ የዘወትር ተግባራቸው በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ይታወቃሉ! አባ ወልደ አረጋዊ፡፡
አባ ወልደ አረጋዊ አብርሃ ጎሹ መካነ ትውልዳቸው ትግራይ ገርዓልታ ማይ ደዓሮ ሲሆን፡፡ በተወለዱበት አካባቢ በሚገኘው፤ በቦታው አቀማመጥ በሀገራችን እና በዓለማችን ዕፁብ ድንቅ በተባለለት በታላቁ ገዳም በገርዓልታ ማይቁዲ ዮሐንስ (በገመድ የሚወጣ ገዳም ነው) የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ በዚሁ ገዳምም በወጣትነት ዘመናቸው በዲቁና እያገለገሉ ቤተሰቦቻቸውንም ደግሞ በግብርና ሥራ እያገለገሉ አድገዋል፡፡
በዚሁ አገልግሎት እያሉ ሕመም ስላጋጠማቸው ለሕክምና ወደ ራያ ወደሚገኝ ሐኪም ቤት፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደመጡም መጀመሪያ ወደ ዘነበ ወርቅ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በማቅናት ለጥቂት ጊዜ ቆይተዋል፤ ነገር ግን ሕመማቸው የአንድ እግራቸውን አሳጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም በደጅ ጸኚነት መጡ፡፡ ደብራችንም ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ አገልጋዮች ማረፊያ (ወደ አዲስ አበባ የመጣ ካህንን ቀጨኔ ፈልጉት) እስከሚባል ድረስ የደረሰ የእንግዳ ተቀባይነት ታሪክ ስላለው፤ በዚሁ መሠረት በወቅቱ የነበሩት የደብራችን አባቶችም ለአባ ወልደ አረጋዊ መኖሪያ ቤት ሰጥተው፣ የሚያስፈልገውን ነገርም አሟልተው በጸሎት እያገለገሉ እንዲቀመጡ አደረጓቸው፡፡ እርሳቸውም በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የ64 ዓመታት የአገልግሎት ቆይታቸውም፤
1ኛ) ለ64 ዓመታት ሁልጊዜም በጸሎት ይተጉ ነበረ፤ የጾም ሰዐታቸውም ሁልጊዜም ዘነፍ አትልም ነበረ፡፡
2ኛ) በጸሎት አስቡኝ የሚላቸውንም ማንኛውንም ምዕመን ያለምንም ክፍያ በጸሎት ያስቡ ነበረ፡፡
3ኛ) ጥንታዊ የሆነውን የገርዓልታ ድጉም አቡነ ስምዖን ገዳም ሕንፃ ቤ/ክ ለብቻቸው አሣንጸዋል፡፡
4ኛ) ለ131 አብያተ ክርስቲያናት መቀደሻ አልባሳት፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ለመሥዋዕት መገበሪያ፣ …… አበርክተዋል፡፡
5ኛ) በተለያዩ ቦታዎች ላሉ ረጂ ለሌላቸው፤ እናት አባት ለሞተባቸውም ሕፃናት ከ3መቶ ሺሕ ብር በላይ እየላኩ ረድተዋል፡፡
፨ ዕድሜ ዘመናቸውን በዚህ ዓይነት አገልግሎት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ የዕረፍት ጊዜያቸውን ቀድመው በማወቃቸው ይረዷቸው እና ይላላኳቸው ወደነበረው ወደ አቶ ተክሌ ቤት ሄደው ለ10 ቀናት ከቆዩ በኋላ እመቤቴ እየመጣች ነው ጸሎት ላድርስ ብለው ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ለአቶ ተክሌ አንድ ቃል ብቻ ነግረዋቸው በብዙኃን ማርያም ቀን መስከረም 21 ቀን በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፈዋል፡፡ ሥርዐተ ግብዓተ መሬታቸውም በኑዛዜያቸው መሠረት መስከረም 22/2018 ዓ.ም. ባሣነጹት ትግራይ ገርዓልታ ድጉም አቡነ ስምዖን ገዳም ተፈጽሟል፤ መላ ዘመናቸውን በድንግልና ያገለገሉ ድንግላዊ አባት ነበሩ፡፡
‹‹…በጺሐኪ ድንግል ጊዜ ዕረፍትየ፤
ጽጌ ዕፀ ገነት ገሪ ላዕሌየ፤
በመዐዛሁ ትትመሠጥ ነፍስየ፡፡
(ድንግል በዕረፍቴ ጊዜ ደርሰሽ የገነት የዛፍ አበባን በእኔ ላይ ጣዪ፥ ዕጠኚ፤ በመዐዛው ነፍሴ ከሥጋዬ ትለይ ዘንድ፡፡) /ማኅሌተ ጽጌ ቊ.፻፲፮/

😢23❤13
#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ
✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣ ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ እያሰቡ እና ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡
✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡
#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡
#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡
የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን
#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ ተጠቀሙ፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
የ2013 ዓ.ም እና የቀደሙት ዓመታት የፎቶ ማስታወሻዎች

❤14🙏1