ለ64 ዓመታት ታላቁን ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምን በጸሎት ያገለገሉት ጸሎተኛው አባት አባ ወልደ አረጋዊ ዐረፉ፡፡
፨ ‹‹ወኢትጸመም ሞቶ ለዘተልአከከ (ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል አትበል)፡፡›› ሲራ. 38÷16
ሁልጊዜም ጠዋት ጠዋት ከደወል ቤት ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ጸሎት ማድረስ የዘወትር ተግባራቸው በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ይታወቃሉ! አባ ወልደ አረጋዊ፡፡
አባ ወልደ አረጋዊ አብርሃ ጎሹ መካነ ትውልዳቸው ትግራይ ገርዓልታ ማይ ደዓሮ ሲሆን፡፡ በተወለዱበት አካባቢ በሚገኘው፤ በቦታው አቀማመጥ በሀገራችን እና በዓለማችን ዕፁብ ድንቅ በተባለለት በታላቁ ገዳም በገርዓልታ ማይቁዲ ዮሐንስ (በገመድ የሚወጣ ገዳም ነው) የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ በዚሁ ገዳምም በወጣትነት ዘመናቸው በዲቁና እያገለገሉ ቤተሰቦቻቸውንም ደግሞ በግብርና ሥራ እያገለገሉ አድገዋል፡፡
በዚሁ አገልግሎት እያሉ ሕመም ስላጋጠማቸው ለሕክምና ወደ ራያ ወደሚገኝ ሐኪም ቤት፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደመጡም መጀመሪያ ወደ ዘነበ ወርቅ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በማቅናት ለጥቂት ጊዜ ቆይተዋል፤ ነገር ግን ሕመማቸው የአንድ እግራቸውን አሳጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም በደጅ ጸኚነት መጡ፡፡ ደብራችንም ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ አገልጋዮች ማረፊያ (ወደ አዲስ አበባ የመጣ ካህንን ቀጨኔ ፈልጉት) እስከሚባል ድረስ የደረሰ የእንግዳ ተቀባይነት ታሪክ ስላለው፤ በዚሁ መሠረት በወቅቱ የነበሩት የደብራችን አባቶችም ለአባ ወልደ አረጋዊ መኖሪያ ቤት ሰጥተው፣ የሚያስፈልገውን ነገርም አሟልተው በጸሎት እያገለገሉ እንዲቀመጡ አደረጓቸው፡፡ እርሳቸውም በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የ64 ዓመታት የአገልግሎት ቆይታቸውም፤
1ኛ) ለ64 ዓመታት ሁልጊዜም በጸሎት ይተጉ ነበረ፤ የጾም ሰዐታቸውም ሁልጊዜም ዘነፍ አትልም ነበረ፡፡
2ኛ) በጸሎት አስቡኝ የሚላቸውንም ማንኛውንም ምዕመን ያለምንም ክፍያ በጸሎት ያስቡ ነበረ፡፡
3ኛ) ጥንታዊ የሆነውን የገርዓልታ ድጉም አቡነ ስምዖን ገዳም ሕንፃ ቤ/ክ ለብቻቸው አሣንጸዋል፡፡
4ኛ) ለ131 አብያተ ክርስቲያናት መቀደሻ አልባሳት፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ለመሥዋዕት መገበሪያ፣ …… አበርክተዋል፡፡
5ኛ) በተለያዩ ቦታዎች ላሉ ረጂ ለሌላቸው፤ እናት አባት ለሞተባቸውም ሕፃናት ከ3መቶ ሺሕ ብር በላይ እየላኩ ረድተዋል፡፡
፨ ዕድሜ ዘመናቸውን በዚህ ዓይነት አገልግሎት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ የዕረፍት ጊዜያቸውን ቀድመው በማወቃቸው ይረዷቸው እና ይላላኳቸው ወደነበረው ወደ አቶ ተክሌ ቤት ሄደው ለ10 ቀናት ከቆዩ በኋላ እመቤቴ እየመጣች ነው ጸሎት ላድርስ ብለው ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ለአቶ ተክሌ አንድ ቃል ብቻ ነግረዋቸው በብዙኃን ማርያም ቀን መስከረም 21 ቀን በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፈዋል፡፡ ሥርዐተ ግብዓተ መሬታቸውም በኑዛዜያቸው መሠረት መስከረም 22/2018 ዓ.ም. ባሣነጹት ትግራይ ገርዓልታ ድጉም አቡነ ስምዖን ገዳም ተፈጽሟል፤ መላ ዘመናቸውን በድንግልና ያገለገሉ ድንግላዊ አባት ነበሩ፡፡
‹‹…በጺሐኪ ድንግል ጊዜ ዕረፍትየ፤
ጽጌ ዕፀ ገነት ገሪ ላዕሌየ፤
በመዐዛሁ ትትመሠጥ ነፍስየ፡፡
(ድንግል በዕረፍቴ ጊዜ ደርሰሽ የገነት የዛፍ አበባን በእኔ ላይ ጣዪ፥ ዕጠኚ፤ በመዐዛው ነፍሴ ከሥጋዬ ትለይ ዘንድ፡፡) /ማኅሌተ ጽጌ ቊ.፻፲፮/

😢23❤13