Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
✤እንኳን ለመስከረም 21፤ብዙኃን_ማርያም
#ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_
#ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤
#ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤
#ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት  (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም
#ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
✤✤✤✤
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ  ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ)
መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት  መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
   #ግሸን_ደብረ_ከርቤ
ደብረ #ንገሥት  ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡
በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ  ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ  ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ   #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡
  በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ  ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ  ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ  በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም  የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡
    እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ  ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡
    በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡
  መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው ፡፡
፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም
፠2ኛ) ደግሞ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ  በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡
ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤
#አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤
#ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤
#ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር ( ማብራርያ የጥቅምት 14 የለጠፍነውን እይ ) ፡፡
ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩  ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት  በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡  ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን  አዘጋጅተዋል፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
    #share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
     www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
13🙏2🥱1
በቀጨኔ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን ለሰባት ዓመታት አስተዳዳሪ የነበሩት መልአከ ገነት ምናሴ ዘለቀ የሕይወት ታሪካቸው በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን መስከረም 25, 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ አዳራሽ ይመረቃል።
49