🌼እንኳን ደስ አላችሁ🌼
በማኅበረ ቅዱሳን ዜማና ኪነ ጥበባት በኆኅተ ጥበባት ማዕከል መለከት የጥያቄና መልስ ውድድር ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በመሰብሰብ ጥቄና መልስ ውድድር ያደረገ ሲሆን ሰንበት ትምህርት ቤታችንን በመወከል ዲ/ን በሱቃል አቢዮት እና መቅደላዊት ጌቱ ውድድሩን በማሸነፍ 1ኛ በመውጣት ያሸነፉ ሲሆን የ20,000 ብር መጽሐፍት ተሸላሚ ሆነዋል።
https://www.youtube.com/watch?v=qygU60jXmXs&t=580s
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

❤67👏20🤬6🔥1
#መስከረም 10 ተቀጸል ጽጌ ፤
#ግማደ_መስቀሉ ከእስክንድርያ በንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ቀን
፨
ተቀጸል ጽጌ የሚለውን ምስጢራዊ መዝሙር የጀመረው የዜማና የቅኔ መሰራች የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
የመሠረተውም በ6ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን #በአጼ #ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው
የክረምቱና የልምላሜው ጊዜ አልፎ የአበባውና የፍሬው ጊዜ በሚተካበት በመስከረም 25 ቀን ቅዱስ ያሬደ ውደ ንጉሡ ዙፋን ቀረቦ #ተቀጸል_ጽጌ _ገብረ_መስቀል_አጼጌ በማለት ዘምራል ፡፡
ተቀጸል ጽጌ ብዙ ምስጢር ሲኖረው ጽጌ (አበባ) የተባለ የንጉሠ ነገሥቱ #ዘውድ ነው ፤ እግዚአበሔር የንጉሡን ዘመን እንዲባርክለት ዘውዱን እንዲቀድስለት ፤ ተቀጸል ጽጌ አጼጌ ፤ #ንጉሥ_ሆይ_ዘውድን_ተቀዳጅ_እያሉ_ለንጉሡ_ይጸልዩለታል ፡፡
ሌላዉ ትርጓሜ ደግሞ ጽጌ የተባለች #ሃይማኖት ናት ፡፡ በኦሪት ቤተ መቅድስ #ያቁምና #በለዝ የሚባሉ ሁለት አዕማዶች በቀኝና በግራ ተተክለው የቅዱስ #ጴጥሮስና #ጳውሎስ ምሳሌ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ በሁለቱ አዕማድ ራስ ላይ አንዲት አባባ ተቀርጻ ትታይ ነበር እሷም #የሃይማኖት ምሳሌ ነበረች፡፡ በዚሁ ዕለት በመዘምራኑ የሚነገረው ቀለም ፤ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሃይመኖት እልፍ ክርስቲያኖችን ማፍራታቸውን በጉልህ ያስረዳል፡፡በሃይማኖተ አበው ላይ ፤ አሕዛብ አስተጋብኡ ጽጌ ረዳ ወሦኩሰ ተረፈ በኃበ አይሁድ ( አሕዛብ አበባ ሰበሰቡ እሾህ ግን በአይዱ ዘንድ ቀረ ) ተብሎ ስለተጻፈ ጽጌ የሚለውን ቃል ሃይማኖት ተብሎ እንደሚተረጐም ታሞኖበታል ፡፡
ከዚህም በመነሳት ሊቃውንት መዘምራን ሁል ጊዜ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይህን ዝማሬ ለንጉሡ ያቀረባሉ ሊቃነ ጳጳቱም ከቤቱ መንግሥቱ የቀረበላቸውን የተጐነገጐነ አበባ በመስቀላቸው ባርከው ያማረውን አበባ ለንጉሡ #ያድላሉ ከዛም ደግሞ ለሌሎች አገልጋዮች እንደየ ማዕረጋቸው ይታደላል ፡፡
ይህ ስርዓት #ከአፄ_ገብረ_መስቀል ዘመነ መንግሥት እስከ #አፄ_ዳዊት_ዳግማዊ ድረስ በየዓመቱ መስከረም 25 ሲፈጸም ቆይቶ በአፄ ዳግማዊ ዳዊት አማካኝነት ግማደ መስቀሉ መስከረም 10 ወደ ኢትዮጵያ ባስገባበት ቀን እንዲከበር በሊቃውንት ተወስኖ የአፄ መስቀል ( መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት )ና የተቀጸል ጽጌ በዓል እስከ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይል ሥላሴ ድረስ በቤተ መንግሥት እና በቤተ ክህነት ሲከበረ ቆይቶ ኃላ ደግም በቤተ ክህነት እስከ አሁን ድረስ እየተከበረ ይገኛል ፡፡
ለመጨረሻም ጊዜ ለንጉሠ ነገሥቱ የተዘመረው #ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲሆን #ተቀጸል_ጽጌ_ኃይለ_ሥላሴ አጼጌ ተብሎ ተዘመሮ ሲያበቃ ለሊቀ ጳጳሳቱ ድግሞ ጸሎቱን ማቅረብ ቀጥሏል፡፡
በዓሉ በቅድስት ሥላሌ ቤተክርስቲያ አሁን ድረስ ስርዓቱ በዓመት በዓመት መስከረም 10 እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ
፨፨፨ ፨፨
#መስቀሉ እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እጅ ገባ ??
የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ #አባ ሚካኤል በአሕዛብ ንጉሥ በነበረው መርዋን ታሰሩ ይህ ንጉሥም ክርስቲያኖችን ማሰቃየትም ጀመረ ፡፡
በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ #ሠይፈ አርዓድ የግብጽ ክርስቲያኖች ላይ መከራ እንዳበዛባቸው በሰሙ ጊዜ ፤ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ወደ ግብጽ ዘመቱ ፡፡ ንጉሡ ከመድረሱም በፊት ደብዳቤ ጻፋ ፤ ሊቀ ጳጳሱን እንዲፈታና ክርስቲያኖችን እንዲተው አስተነቀቁት ፤ ደብዳቤውን ካየ በኃላ እጅግ ፈርቶ ሊቀ ጳጳሱን ከእስራት ፈታቸው ንጉሱም ለበረከት እንዲሆናቸው ከጌታ ወርቅ(የሰበዓ ሰገል ወርቅ ) ጋር እንዲቀመጥ የእጅ መንሻ ወርቅ ለሊቀ ጳጳሱ ላኩላቸው ከዛ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ ፡፡
ከዚህ በኃላ እርሳቸው ሞተው የእመቤታቸን ወዳጅ የሆነው ልጃቸው ዳግማዊ ዳዊት ነገሠ ፡ አሕዛቡ ንጉሥ ሞታቸውን በሰማ ጊዜ አባ ሚካኤልን ዳግመኛ አሰራቸው ፤ ከዚያም የሮም የቁስጥንጥንያ የሶርያ የአርመን ፣ የግብፅ ክርስቲያኖች በአንድ ሆነው ለኢትዮጵያው ንጉሥ ለዓጼ ዳዊት፤ የክርስቶስን ሃይማኖት ለማጥፋት የአህዛብ ነገሥታት ቆመዋል የሚል መልእክት ላኩ ፡ ዓጼ ዳዊት ይህን በሰሙ ጊዜ መሃላ በመማፋረሱ ተናደዱ ፡፡መንፈሳዊ ቅንዓትም አድረባቸው፡፡
ክተት ሠረዊት ብለው ለጦር ዘምተው ካርቱም ሲደረሱ #ግዮን (አባይ )ን መልስው ወደ ካሩተም በረሐ ሰደዱት የግብፅ ሰዎች ከእርሱ በቀር የሚጠጡት የለምና ፡፡
የምስሩ ንጉሥ እና መኳኳንንቶች ይህን በሰሙ ጊዜ ያረጉት ስህተት እንደሆነ ተረዱ ደንግጠው ሊቀ ጳጳሱን አባ ሚካኤልን ፈቱዋቸው ከሞት የተረፉትን ምእመናን ነጻ አወጧቸው ፡፡ ለዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ያማልዱት ዘንድ ለመነ። ክርስቲያኖችም ይህንን በሰሙ ጊዜ ነጻ ላወጣቸው ንጉስ አመላካቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ ፡፡
የግብፁ መኳንንት እጅ መንሻ ወደ ንጉሡ ላኩ ፡ ንጉሥ ዳዊትም ሊቀ ጳጳሱ መፈታታቸውን በሰሙ ጊዜ አስዋን ድረስ ወረዱ ይህም በጊዜው ለኢትዮጵያ እና ለግብጽ የወሰን ድካ የነበረው ነው ፡፡
ሰኔ 10 ቀን ከሊቀ ጳጳሳቱ እና ከመኳኳንንቱ ጋር ተገናኙ ፡፡ የአባይን ውሃ እንዲመልሱላቸው እልፍ ወርቅና ይዘው ቢጠይቋቸው ይህ ለኔ ነፍስ ለማዳን አይጠቅመኝም አሉ ፡፡ እኔ የምፈልገው የጌታቸንን መስቀል ነው አሉ ፡፡ እነርሱም ከተመካከሩ በኃላ መንፈሳዊ ንጉሥ መሆኑን አይተው ይገባዋል አሉ ፡፡
መስቀሉንም አስረከቧቸዉ እርሱን ብቻ ሳይሆን #ሉቃስ የሣላቸውን ሰባቱን #የእመቤታችንን ሥዕሎች ፣ #ዮሐንስ ወንጌላዊ የሣለውን የጌታቸንን #የኵርዓተ ርእሱን ሥዕል ጭምር እንጂ ፡፡
ይህ ሁሉ የሆነው #መስከረም 10 ቀን ነው በዚችም ዕለት በመላው ኢትዮጵያ ብርሃን ሆነ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ እያሉ ዘመሩ ይህን ልማድ በማድረግ አሁን ድረስ በዓሉ ይከበራል የበዓሉም ስም #አጼ_መስቀል እየተባለ ይጠራል፡፡
ከዚህ ቦኃላ ወደ ጥንት ላማዱ እንዲሄድ የአባይን ወንዝ መለሰው ለግብጻዊያኑ ለቀቁላቸው ፡፡
ከቅዱስ መስቀሉ ረድኤት በረከት ይክፍለን
አሜን!
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤14👍1
መስከረም ዐሥራ አንድ በዚች ቀን ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸውና መካሪያቸው የሆነ ቅዱስ ፋሲለደስ በሰማዕትነት አረፈ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼✥✞✥🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት፤ ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት።
ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ ፋሲለደስን እኅት አግብቶ ዮስጦስን፣ ገላውዴዎስን፣ አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው።
የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ።
በዚያም ወራት የቊዝና የፋርስ ሰዎች የሮምን ሰዎች ሊወጓቸው በላያቸው ተነሡ ያን ጊዜ የንጉሥ ልጅ ዮስጦስን የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስን ከጦር ሠራዊቶቻቸው ጋር ለውጊያ ላኳቸው ።
ንጉሡ ኑማርዮስም ሌሎች ጠላቶች በተነሡበት በኩል ለጦርነት ሒዶ በውጊያው ውስጥ ሞተ የሮም መንግሥትም የሚጠብቃትና የሚመራት የሌላት ሆነች።
እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት ስለ ጦርነት ለመደራጀት የሮም ሰዎች ከሀገሩ ሁሉ አርበኞች የሆኑ ሰዎችን ሰበሰቡ ከውስጣቸውም ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አለ፤ እርሱንም መኳንንቱ ወስደው በመንግሥት ፈረሶች ላይ ባልደራስ አድርገው ሾሙት እርሱም በጠባዩና በሥራው ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ ነበር።
ከንጉሥ ኑማርያኖስ ሴቶች ልጆች አንዲቱ ወደርሱ በመስኮት ተመለከተች ወደደችውም መልምላም ወስዳ አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰይማ አነገሠችው።
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖታትን አመለከ ቅዱስ ፋሲለደስም ሰምቶ እጅግ አዘነ የመንግሥትንም አገልግሎት ተወ።
ከዚህም በኋላ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው የጠላቶቻቸውንም አገሮች አጥፍተው ደስ ብሏቸው ተመለሱ፤ ነገር ግን የነገሠው ዲዮቅልጥያኖስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን አቁሞ አገኙት እጅግም አዘኑ ተቆጥተውም ተነሡ ሰይፎቻቸውን መዝዘው ዲዮቅልጥያኖስን ገድለው የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደዱ ፋሲለደስም ከዚህ ሥራ ከለከላቸው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን፣ ሠራዊቱን፣ አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው ሁሉም እንዲህ ብለው መለሱለት አንተ በምትሞትበት ሞት እኛ ከአንተ ጋር እንሞታለን በዚህም ምክር በአንድነት ተሰማሙ።
ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና።
የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኀርማኖስም ወደ ግብጽ አገር ይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲአሠቃዩአቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር፣ አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ፣ ገላውዴዎስንም እንዲሁ አደረጉ፤ በናድሌዎስ ቴዎድሮስም እሼ በሚባል ዕንጨት ላይ በመቶ ሃምሳ ሦስት ችንካር ተቸንክሮ ገድሉን ፈጸመ።
ቅዱስ ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት ወደ አፍሪካ ምድር ወደ መኰንኑ ወደ መጽሩስ ላከው መጽሩስም በአየው ጊዜ መንግሥቱን ክብሩን ስለ ተወ እጅግ አደነቀ።
ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም መልአኩን ልኮ በመንፈስ ወደ ሰማይ አውጥቶ በብርሃን ያጌጠ መንፈሳዊ ማደሪያን አሳየው ነፍሱም እጅግ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ወደነበረበት መለሰው።
ባሮቹን ግን ነፃ ያወጣቸው አሉ የቀሩትም ከእርሱ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን የተቀበሉ ሰባት ሺህ ሠላሳ ሦስት የሚሆኑ አሉ።
ቅዱስ ፋሲለደስንም ታላቅ ስቃይን አሰቃዩት በመንኰራኲርና በተሣሉ የብረት ዘንጎች ሥጋውን ሰነጣጥቀውት ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ጥፋት ከሞት አድኖ አስነሣው አሕዛብም ሁሉ ይህን ድንቅ
ተአምር በአዩ ጊዜ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ መኰንኑንም ረገሙት ጣዖቶቹንም ሰደቡ በእነርሱ ላይም ተቆጥቶ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ወንዶች ሠላሳ ሰባት ሴቶች ናቸው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን ሥጋው ሁሉ ቀልጦ እንደ ውኃ እስከሚሆን በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት መኰንኑም በተራራ ላይ ጥልቅ ጒድጓድ ቆፍረው በዚያ እንዲቀብሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ።
"ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፋሲለደስን ከሞት ደግሞ አስነሣው ወደ መኰንኑም መጥቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ መኰንን መጽሩስ ሆይ እፈር ከሀዲ ንጉሥህም የረከሱ ጣዖቶችህም ይፈሩ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጉዳት ከሞት ጤነኛ አድርጎ አስነሥቶኛልና።
ሕዝቡም ይህን ተአምር በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሆነ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን በውስጧ መጋዝ ካላት መንኰራኲር ላይ አውጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ በሆዱ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት ከዚያ ስቃይም ውስጥ አንስቶ ያለ ጉዳት ጤነኛ አደረገው እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው ፋሲለደስ ሆይ ዕውቅ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ ወይም ለድኆች በስምህ ምጽዋትን ለሚሰጥ ወይም ለተራቈተ ልብስን ወይም በመታሰቢያህ ቀን ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ በብዙም ቢሆን በጥቂት መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ እኔ በደላቸውን ሁሉ እተውላቸዋለሁ መኖሪያቸውንም በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋራ አደርጋለሁ ።
ጌታችንም ይህን ካለው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ቅዱስ ፋሲለደስም በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኘ።
ከዚህም በኋላ መጽሩስ መኰንን ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረ እንዲህም አላቸው ስሙ ፋሲለደስ ስለሚባል ስለዚህ ሰው ምን ላድርግ እርሱን ያላሠቃየሁበት የሥቃይ መሣሪያ ምንም የቀረ የለም ከሐሳቡም አልተመለሰም እነርሱም እንዲህ ብለው መከሩት ራሱን በሰይፍ ቆርጠህ ከእርሱ ተገላገል እነሆ የዚች አገር ሰዎች በእርሱ ምክንያት አልቀዋልና።
በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ፋሲለደስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልን ተቀበለ ንቆ ሰለ ተዋት ምድራዊት መንግሥት ፈንታም ሰማያዊት መንግሥት አገኘ፤ ከሥጋውም ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራት ተገለጡ ከእርሱም ጋር ሰማዕት ሁነው የሞቱ ሁሉም ቊጥራቸው ሃያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሦስት ሆነ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ፋሲለደስና በሰማዕታት ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም

❤10🙏1
🌻ተቀጸል ጽጌ🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
የተቀጸል ጽጌ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ተከብሯል።
በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በጥንት ጊዜ ወርኃ ክረምቱ አለፈ የጽጌ ዘመን መጣ ይህን ያደረገ እግዚአብሕር ይመስገን ሲሉ ተቀጸል ጽጌን መስከረም ፳፭ ቀን በታላቅ የምስጋና ማዕድ በቤተ ክርስቲያንንና ነገሥታቱ አብያተ መንግሥት ይከበር ነበር።
በኋላ አጼ ዳዊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀል ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መስከረም ፲ ቀን በመግባቱ ምክንያት መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ ነውና የተቀጸል ጽጌ በዓል በወደ ዚሁ ቀን በመሳብ አንድ ላይ ማክበሩ እንደቀጠለ ሊቃውንት ይናገራሉ።
የተቀጸል ጽጌ በዓል ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም ወዲህ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፭ኛው የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ አማካኝነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እስካሁን በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት እየተከበረ እዚህ ደርሷል።
©️ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

❤25