Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ደብተራው ደራሲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም.) የጻፋቸው መጻሕፍት

-ለኢትዮጵያ ቤ/ን ብዙ የደከመና ያገለገለ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዕረፍት ጳጉሜን 3 1460 ዓ.ም ነበር፡፡

-ደብተራ ዘርዓ ያዕቆብ(1400-1460 ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ታሪክ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ የጻፈ ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከጻፋቸው መጻሕፍት መካከል የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. መጽሐፈ ብርሃን
2. መጽሐፈ ሚላድ
3. መጽሐፈ ሥላሴ
4. መጽሐፈ ባሕርይ
5. ተዓቅቦ ምሥጢር
6. ጦማረ ትስብእት
7. ስብሐተ ፍቁር
8. እግዚአብሔር ነግሠ
9. ድርሳነ መላእክት (ጌታቸው ኃይሌ፣ ባሕረ ሐሳብ፣ገጽ 236)

10. ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ በቅርቡ ባሳተሙት “ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋር ብዙ አፍታ ቆይታ” መጽሐፍ ላይ ደግሞ ድርሳን ወገድለ ያሬድን የጻፈው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

-ፕ/ር ጌታቸው በመጽሐፋቸው እንደሚነግሩን “ዘርዓ ያዕቆብና ደብተራዎቹ ለዘመኑ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ብዙ ድርሳናት ደርሰዋል፡፡ የሚታወቁት መጽሐፈ ብርሃን፣ መጽሐፈ ሥላሴ ወመጽሐፈ ሚላድ፣ እግዚአብሄር ነግሠ፣ ጦማረ ትስብእት፣ መጽሐፈ ባሕርይ፣ ስብሐተ ፍቁር፣ ተዓቅቦ ምሥጢር፣ ድርሳነ መላእክት፣ መልክአ ፍልሰታ እና ጥቂት ተአምራተ ማርያም ናቸው፡፡” (ጌታቸው ኃይሌ፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ-38)

-የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን ዕረፍት ጳጉሜን 3 ይታሰባል፡፡
ከዲ/ን ዮሴፍ ፍሥሐ ገጽ
36👍4
#በዓለ_ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት_ዮሐንስ_ወቅዱስ_ራጉኤል
#እንኳን_አደረሳቹ

#ዐዲስ_ዓመት

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና /ሔኖክ. 21፥49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ በፍል ውኃ አጥለቅልቆ በኃጢአት ሕይወት ይኖሩ የነበሩት የኖኅ ዘመን ሰዎች ቀጥቶ ካጠፋ በኋላ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው /ኩፋሌ. 7፥1/፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስቀምጣሉ፡፡


የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በክታባቸው እንዳስቀመጡት በአራቱ ወንጌላውያን ዘመኑን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ በዘመነ ማርቆስ ተጠምቋል፡፡ በዘመነ ሉቃስ ተሰቅሎ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ አውጥቷል፤ እያሉ ታሪካዊ ሐረጋቸውን ጠብቆ አራቱ ወንጌላውያን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ::

#እንቁጣጣሽ

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ስትመለስ “እንቁ ለጣትሽ /ለጣትሽ እንቁ/ በማለት ከእንቁ የተሠራ የጣት ቀለበት ንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ እንዲሆናት አበርክቶላት ነበርና ይህን ታሪክ መነሻ አድርገው “እንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ ከዚያ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ያስረዱናል ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ምድሪቱ በክረምቱ ዝናብ ረስርሳ ድርቀቷ ተወግዶ በአርንጓዴ እጸዋት ተውባ ሜዳው፣ ሸለቆውና ተራራው በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠው የሚታዩበት ወቅት በመሆኑ ዕለቱ “እንቁጣጣሽ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ ወቅት ሕፃናትና ልጃገረዶች ነጭ ባሕላዊ ልብስ በመልበስ ለምለም ቄጤማና አደይ አበባ በመያዝ በአካባቢያቸው በመዞር አዲስ ዘመን መበሠሩን “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት በቸርነቱ ዓመታትን የሚያፈራርቀውን እግዚአብሔርን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡

መልካም_አዲስ_ዓመት

#ራጉኤል ሊቀ መላእክት:-

ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው።

አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው። በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23) አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው። በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል።

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
19👍1🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቅዱስ ፓትርያርኩ የአዲስ ዓመት መልእክት
©️ EOTC_TV
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#የአዲስ_ዓመት_ጸሎት
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

አቤቱ ጌታ ሆይ ዓመቱን የተባረከ አድርገው
አንተን ደስ የሚያሰኝ ንጹሕ ዓመት ይሁን።
መንፈስ የሚገለጥበት ዘመን ይሁን ከእኛ ጋራም ይሥራ።

እጆቻችንን ያዝና አሳቦቻችንን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ማብቂያው ድረስ አንተ ምራቸው።

አንተ ደስ ያሰኝህ ዘንድ ይህ ዓመት የአንተ ይሁን፡፡
ይህ ዓመት አዲስ ዓመት ስለሆነ በኃጢአታችንና
በበደላችን አናርክሰው።

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ዓመት ልንሠራው ባቀድነው
በማንኛውም ሥራ ውስጥ አንተ ከእኛ ጋር ሁን
እኛ ዝም እንላለን አንተ ሁሉንም ነገር ታደርጋለህ፡፡

አቤቱ ጌታ ሆይ ይህ ዓመት መልካም ይሁን
በእያንዳንዳችን ላይ ፈገግታን ግለጥ የሁላችንንም ልብ አስደስት፤ በችግራችን ውስጥ ጸጋህ ይገለጥ
የተፈተኑትንም አንተ እርዳቸው፤ የአሳብ ሰላምንና ጸጥታን
አድለን፡፡

ለተቸገሩት ስጣቸው፤ የታመሙትን ፈውሳቸው፣ ያዘኑትን
አጽናናቸው፡፡
ጌታችን ሆይ ለራሳችን ብቻ አንጠይቅህም ያንተ ስለሆኑት
ስለሁሉም እንጠይቃለን።

የፈጠርካቸው ባንተ ደስ እንሲሰኙ ነው ይህ ከሆነ በአንተ
ደስ እንዲሰኙ አድርጋቸው
ቃልህ ለሁሉም ልብ ይደርስ ዘንድ ስለ ወንጌል አገልግሎትና ስለ ቤተ-ክርስቲያናችን እንጠይቅሃለን፤

ስለሃገራችንም እንጠይቅሃለን፡ መንግስትህ በሁሉ ስፍራ እንድትመጣም ስለ ዓለም ሰላም እንጠይቅሃለን፡፡

ዓመቱ ፍሬያማና በመልካም ነገሮች የተሞላ ይሁን፡፡

እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት የራሱ የሆነ ሥራ አለው

አንተ የሚባክን ጊዜ ይኖርህ ዘንድ አትፍቀድ፡፡

ሕይወታችንን በእንቅስቃሴ በሥራና በምርት የተሞላ
አድርግ፤ ለምርታማና ለተቀደሰ ልፋታችን በረከትህን
አድለን፡፡

በተግባሮቻችን ውስጥ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ከእኛ
ጋር ይሁን።

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ እስከዚች ሰዓት ድረስ
ጠብቀህ ስላቆየኸንና ይህንን ዓመት ስላደልከን
እናመሰግንሃለን፣ እንባርክህማለን፡፡
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
23🙏8