Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
#ዘመነ_በርዮድ_
#ጳጕሜን_
ዓመትን በዘመናት ስንከፋፍለው በ4ት ዘመናት ይከፈላል፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ዘመነ ክረምት (ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25) ነው፤ በዘመነ ክረምት ውስጥ ደግሞ ከሚውሉት መካከል ከነሐሴ 28 እስከ ጳጕሜን ፭ት (በሠግር ዓመት ፮ት) ድረስ ያለው #ዘመነ_በርዮድ_ ይባላል፤ ይህም ወደ አዲስ ዘመን የሚያሻግረን ነው፡፡ በቅዱስ ያሬድ ድጓ መሠረትም ጎሕ (ውጋገን)፣ ነግህ (ንጋት)፣ ጽባሕ (ጥዋት)፣ ብርሃን፣ መዓልት (ዕለት)፣ ጌና (ልደት) ይባላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም (ዘመንን ቀንን በቊጥር ሰጣቸው፣ በውስጧም ያለውን ፍጥረት አስገዛቸው፡፡) እንዲል /ሲራክ 17፥2/
ጳጕሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፤ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት በስድስት መቶ ዓመት አንዴ ደግሞ ሰባት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ ጳጕሜን በአራት ዓመት አንዴ (ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ ቅበላ ስድስት ቀን ትሆናለች)፤ የዘንድሮውን #የ2018 ዓ..ም ወርኀ ጳጕሜን ልብ ይሏል፡፡ በዚህም ሃገራችን ኢትዮጵያ የዐሥራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃች፡፡

#የጳጕሜን_ጾም_ጾመ_ዮዲት_
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጕሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህ ጾም  በተጨማሪ ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፤ ጾሙ እንደ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ጾመ ዮዲት የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ /እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡/ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉሥ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ፥ ድንበር አስፋ፤ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ፥ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ /ዮዲት 2፥2-7/፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት፤ ከወንድ ርቃ፥ ንጽሕናዋን ጠብቃ፥ በጾም፥ በቀኖና፥ በሐዘን ተወስና የምትኖር ነበረችና፤ በተፈጠረው ጥፋት ሕዝቡ ላይ ለመጣው መከራ፤ ማቅ ለብሳ፥ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክን ሕዝቡ የሚድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለጸላት /ዮዲት 8፥2/ ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንንና ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን ለመጎናጸፍ ጳጕሜን በፈቃድ እንጾማለን፡፡

#ጳጕሜን_የዕለተ_ምጽአት_መታሰቢያ_
የጳጕሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጕሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ፤ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፥ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡

#ጠበል_በወርኀ_ጳጕሜን_
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጕሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጠበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጠበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፥ የተቀደስንም ያደርገናል፤ መጪውንም ሕይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ ጷጕሜን ይሁንልን፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
12👍4
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ ጳጉሜን ፩ ሊደረግ የነበረው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላልተወሰነ ጊዜ ስለተራዘመ ተለዋጭ ቀኑን በቅርብ ጊዜ እናሳውቃለን። እናሳውቃለን ።    

ሰንበት ትምህርት ቤቱ
1
ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉዟቸውን አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በብፁዓን አበው አቀባበል መደረጉ ተገለጸ!!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን።

ቅዱስነታቸው ጠዋት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት  ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ጠባቂ፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የማኅበራት ክትትልና ቁጥጥር ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት በስፍራው ተገኝተዋል።
©️የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ሕ.ግ
10