#መድኃኔዓለም
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤20🥰7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ልዑል ሐነፃ በጽድቁ ሐወጻ
እምነ ፀሐይ ይበርህ ገጻ
"ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ"
እምነ ፀሐይ ይበርህ ገጻ
"ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ"
❤27🥰3👏3
ለሁለት ቀናት የቆየው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት 11ኛ አመት 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቋም በመግለጽ ተጠናቀቀ።
የጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
1 በአንድነቱ የቀረበውን ዕቅድ ያፀደቅን ሲሆን ሁላችንም ለተግባራዊነቱ እንተጋለን ፡፡
2 የሰ/ት/ቤትን ዝማሬን በተመለከተ ጉባኤው ተወያይቶ ባፀደቀው መሰረት ሁሉም ሰ/ት/ቤት የሚጠቀምበትን ልብሰ ስብሀት የካህናት በተለይም የዲያቆናት አክሊል የሆነና ተመሳሳይ የሆነ ከዚህ በኋላ የትኛውም ሰ/ት/ቤት እንዳይጠቀም፡፡ የልብሰ ስብሐትና የአክሊል ዓይነት ተወስኖ በመመሪያ እስኪወርድ ድረስ ከካህናትና ከዲያቆናት አልባሳትና አክሊል ውጪ ሰ/ት/ቤቶች ባላቸው ልብሰ ስብሐት እየተጠቀሙ እንዲቆዩ ተስማምተናል፡፡
3 አዘማመርን በተመለከተ ያሬዳዊ ዜማን የጣሰ ወደ ጭፈራ ያደላ አዘማመር እንዲቆም ይህንንም ለማስፈፀም ከክፍለ ከተማ አንድነት ክትትል እንዲያደርግ ተስማምተናል፡፡
4 የአጫበር ስም እየተተገበረ ያለ አዘማመርን በተመለከተ የዘርፉ ሊቃውንትን ጨምሮ ብዙአባቶችን እና ምዕመናንን ያሳዘነ ጉዳይ በመሆኑ በሊቃውንት ተጠንቶ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውሳኔ ተላልፎ እስኪተገበር ድረስ ሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤት የአጫበር ስም የሚደረግ ዝማሬን እንዲያቆሙ፡፡
5 ከላይ በተጠቀሱት የአለባበስና አዘማመር ጉዳይ በሀገረ ስብከት መመሪያ እንዲተላለፍ እና ሰበካ ጉባኤያት ቁጥጥር እንዲያደር ተስማምተናል፡፡
6 የ2018ዓ/ም የአጥቢያ የሰ/ት/ቤት የአመራር ምርጫ ለማስፈፀም ጉባኤው የተስማማ ሲሆን የምርጫ ወቅቱ እስከሚደርስ ድረስ አሁን ያለ ሁሉም አመራር በአዲስ እያደራጀ እንዲቆይ እና ምንም አይነት የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር ምርጫ እንዳይካሄድ እና የተለየ ችግር ያለባቸው ሰ/ት/ቤቶች ብቻ ክክፍለ ከተማ አንድነቱ ጋር እየተወያዩ አደራጅ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙ ተስማምተናል ፡፡
7 የሰንበት ትምህርት ቤቶችን መረጃ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማራጀት በአንድነቱ በተዘጋጀው ፖርታል እንድንጠቀም የራሳቸው ዳታ ቤዝ ያላቸው ሰ/ት/ቤቶች ከሀገረ ስብከቱ አንድነት ዳታ ቤዝ ጋር እንዲያናብቡ እና በየደረጃው የሚያድገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉም ሰ/ት/ቤቶች ሀዋርያዊ አገልግሎታችንን ለመፈፀም በጋራ ለመስራት ተስማምተናል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ

❤9👏1🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት 11ኛ ዓመት 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አቋም መግለጫ!
https://vm.tiktok.com/ZMSKcY6TT/
https://vm.tiktok.com/ZMSKcY6TT/
❤16👏4👍3🥰1
ሐምሌ 29-ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ የነበሩትና በመንዝ በይፋት ያሉ ክርስቲያኖች ብርዱን ውርጩን በስማቸው የሚገዝቱባቸው አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ፡- ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ ‹‹በምን አውቀኸኝ ነው?›› ብላ አቅፋ ሳመችውና ‹‹ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ…›› ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡
ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በድብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡
ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡
አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡ ከዚኽም በኋላ ‹‹ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸው?›› ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም ‹‹አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?›› አሏት እርሷም ‹‹አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው ‹‹በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ›› ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ ‹‹የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣ የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ›› ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡
አቡነ ዩሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም መቋሚያቸው በመዳበር በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዩሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15 ነቢያት፣ ከ12 ሐዋሪያት፣ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ‹‹ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡ በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…›› የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኃላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ቅዱስ አባታችንም በ500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡ አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው ‹‹በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም›› አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ134 ዓመት በኃላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡ ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ግማሽ ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው አርባ ሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል-ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡
አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

❤35
እንኳን አደረሳቹሁ !
ጾመ ፍልሰታ
#ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡
በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ) 5. ✣ ጾመ ነነዌ
2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ) 6. ✣ጾመ ጋድ
3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 7. ✣ #ጾመ #ፍልሰታ
4. ✣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
#ጾመ_ፍልሰታ
ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።
ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።
ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

❤22🙏2🥱1