Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት::

ሐምሌ 27 ፤ የልጅ ኢያሱ (ክፍለ ያዕቆብ  ደብረ የሚሆነው የቀጨኔ  ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም   ቅዳሴ ቤት መታሰቢያ  መሆኑም እንዳይዘነጋ::

#ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ጥንታዊ የአቤቶ ልጅ ኢያሱ ደብር፡፡  ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ››
ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)
….. የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤ የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡
✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
15
#መድኃኔዓለም

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
20🥰7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ልዑል ሐነፃ በጽድቁ ሐወጻ
እምነ ፀሐይ ይበርህ ገጻ

"ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ"
27🥰3👏3
ለሁለት ቀናት የቆየው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት 11ኛ አመት 2ተኛ መደበኛ  ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቋም በመግለጽ ተጠናቀቀ።

የጠቅላላ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
1 በአንድነቱ የቀረበውን ዕቅድ ያፀደቅን ሲሆን ሁላችንም ለተግባራዊነቱ እንተጋለን ፡፡
2 የሰ/ት/ቤትን ዝማሬን በተመለከተ ጉባኤው ተወያይቶ ባፀደቀው መሰረት ሁሉም ሰ/ት/ቤት የሚጠቀምበትን ልብሰ ስብሀት የካህናት በተለይም የዲያቆናት  አክሊል የሆነና ተመሳሳይ የሆነ ከዚህ በኋላ የትኛውም ሰ/ት/ቤት እንዳይጠቀም፡፡ የልብሰ ስብሐትና የአክሊል ዓይነት ተወስኖ በመመሪያ እስኪወርድ ድረስ ከካህናትና ከዲያቆናት አልባሳትና አክሊል ውጪ ሰ/ት/ቤቶች ባላቸው ልብሰ ስብሐት እየተጠቀሙ እንዲቆዩ ተስማምተናል፡፡
3 አዘማመርን በተመለከተ ያሬዳዊ ዜማን የጣሰ ወደ ጭፈራ ያደላ አዘማመር እንዲቆም ይህንንም ለማስፈፀም ከክፍለ ከተማ አንድነት ክትትል እንዲያደርግ ተስማምተናል፡፡
4 የአጫበር ስም እየተተገበረ ያለ አዘማመርን በተመለከተ የዘርፉ ሊቃውንትን ጨምሮ ብዙአባቶችን እና ምዕመናንን ያሳዘነ ጉዳይ በመሆኑ በሊቃውንት ተጠንቶ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውሳኔ ተላልፎ እስኪተገበር ድረስ ሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤት የአጫበር ስም የሚደረግ ዝማሬን እንዲያቆሙ፡፡
5 ከላይ በተጠቀሱት የአለባበስና አዘማመር ጉዳይ በሀገረ ስብከት መመሪያ እንዲተላለፍ እና ሰበካ ጉባኤያት ቁጥጥር እንዲያደር ተስማምተናል፡፡
6 የ2018ዓ/ም የአጥቢያ የሰ/ት/ቤት የአመራር ምርጫ ለማስፈፀም ጉባኤው የተስማማ ሲሆን የምርጫ ወቅቱ እስከሚደርስ ድረስ አሁን ያለ ሁሉም  አመራር በአዲስ እያደራጀ እንዲቆይ እና ምንም አይነት የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር ምርጫ እንዳይካሄድ እና የተለየ ችግር ያለባቸው ሰ/ት/ቤቶች ብቻ ክክፍለ ከተማ አንድነቱ ጋር እየተወያዩ አደራጅ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙ ተስማምተናል ፡፡
7  የሰንበት ትምህርት ቤቶችን መረጃ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማራጀት በአንድነቱ በተዘጋጀው ፖርታል እንድንጠቀም የራሳቸው ዳታ ቤዝ ያላቸው ሰ/ት/ቤቶች ከሀገረ ስብከቱ አንድነት ዳታ ቤዝ ጋር እንዲያናብቡ እና በየደረጃው የሚያድገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉም ሰ/ት/ቤቶች ሀዋርያዊ አገልግሎታችንን ለመፈፀም በጋራ ለመስራት ተስማምተናል፡፡ 

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ
9👏1🤝1