#ታላቁ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ፤ የወላጆቹ አገር አስሊጥ የምትባል ስትኾን እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ
ከለባት (ውሻ ) ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡
በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና
የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ
መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና
ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሯቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሯቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና
የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም
የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡
መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብረውት ነበሩ፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን
እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች
ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና
‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ
ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ
ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጰዶቅያና
የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ
ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
✤ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እንዲሁም ጎርጎርዮስን ረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው
ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም
ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ በስዕሉ ላይ ያለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ይዞ ከተሳለው ጦር ጫፍ ላይም ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው
ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
✤ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡
ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡ መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ
ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡
በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና
‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኰሳትን አፍርቷል፡/

❤25
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
#ሐምሌ 26 ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን የተገባው #ዮሴፍ ጻድቅ ዕረፍቱ ነው ፡፡ አባቱ ያዕቆብ ይባላል:፡ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከቤተ ዳዊት የሆነ ደግ ሰው ነበር:: ድግር ጠርቦ ጥርብ አለዝቦ ሽጦ ይኖር ነበር:: ያዕቆብ ዮሳ ስምዖን ይሁዳ የተባሉ አራት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች ወልዷል: ፡ሚስቱ ከሞተችበት በኋላ አይሁድ በእመቤታችን ላይ በጠላትነት ተነስተው ከቤተ መቅደስ ትውጣልን ባሉ ጊዜ በሶስት ነገር ተመስክሮለት እመቤታችንን ወስዶ ከቤቱ አስቀምጧታል:
ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በደስታዋም በኀዘናም ጊዜ አልተለያትም። እመቤታቸን በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ።ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። ልጇን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማዳን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሀቡን ጽሙን ሐሩረ መዓልቱን ቁረ ሌሊቱን በተንከራተተችበትም ወቅት አልተለያትም። ከዛም በኃላ ጌታን እንደ አባት ሆነ አገልግሏል፡፡
ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ'ወንዶችና ሴቶችልጆቹን ጠርቶ ተሰ ናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን ለእግዚአብሔር 'እጅ ሰጠ " የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ።
በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃብር አኖሩት። ያረፈውም በ104 ዓመቱ ነበር፡፡
የአባታቸን የአረጋዊ ዮሴፍ ምልጃና ጸሎቱ አትለየን
#ሐምሌ 26 የመጀመርያው ጳጳስ የሆኑት አቡነ #ሰላማ /ፍሬምናጦስ / ዕረፍት
3ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ እኚህ አባታችን የትውልድ ሀራቸው ሶርያ ነው: ቀዳሚ ስማቸው ፍሬምናጦስ ይባላል የመጀመሪው ጳጳስና በትምህርታቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያሸጋገሩ አባት ናቸው፡፡
ውደ የግብጽ ሄደው እለ እስክንድሮስም ጳጳስ እንዲሾምላቸው ከሄደበት ከኒቅያ ጉባኤ ድርስ ሄድው ቢጠየቁት ባህላቸውን የለመደ ቋንቋቸውን ያወቀ ካንተ ሌላ ወዴት ይገኛል ደግሞም ያንተ ዕጻ ናት ብሎ አምስት ዓመት ሐዲስ ኣስተምሮ አባ ሰላማ ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኵላ ኢትዮጵያ ብሎ ሾሞ ልኳቸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሰረተው ወንጌልን ተግተው እያስተማሩ አገልግለው ብዙ መጻሕፍትን ተርጉመው በክብር ዐርፈዋል::
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በደስታዋም በኀዘናም ጊዜ አልተለያትም። እመቤታቸን በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ።ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። ልጇን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማዳን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሀቡን ጽሙን ሐሩረ መዓልቱን ቁረ ሌሊቱን በተንከራተተችበትም ወቅት አልተለያትም። ከዛም በኃላ ጌታን እንደ አባት ሆነ አገልግሏል፡፡
ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ'ወንዶችና ሴቶችልጆቹን ጠርቶ ተሰ ናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን ለእግዚአብሔር 'እጅ ሰጠ " የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ።
በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃብር አኖሩት። ያረፈውም በ104 ዓመቱ ነበር፡፡
የአባታቸን የአረጋዊ ዮሴፍ ምልጃና ጸሎቱ አትለየን
#ሐምሌ 26 የመጀመርያው ጳጳስ የሆኑት አቡነ #ሰላማ /ፍሬምናጦስ / ዕረፍት
3ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ እኚህ አባታችን የትውልድ ሀራቸው ሶርያ ነው: ቀዳሚ ስማቸው ፍሬምናጦስ ይባላል የመጀመሪው ጳጳስና በትምህርታቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያሸጋገሩ አባት ናቸው፡፡
ውደ የግብጽ ሄደው እለ እስክንድሮስም ጳጳስ እንዲሾምላቸው ከሄደበት ከኒቅያ ጉባኤ ድርስ ሄድው ቢጠየቁት ባህላቸውን የለመደ ቋንቋቸውን ያወቀ ካንተ ሌላ ወዴት ይገኛል ደግሞም ያንተ ዕጻ ናት ብሎ አምስት ዓመት ሐዲስ ኣስተምሮ አባ ሰላማ ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኵላ ኢትዮጵያ ብሎ ሾሞ ልኳቸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሰረተው ወንጌልን ተግተው እያስተማሩ አገልግለው ብዙ መጻሕፍትን ተርጉመው በክብር ዐርፈዋል::
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤17
ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት::
ሐምሌ 27 ፤ የልጅ ኢያሱ (ክፍለ ያዕቆብ ደብረ የሚሆነው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቅዳሴ ቤት መታሰቢያ መሆኑም እንዳይዘነጋ::
#ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ጥንታዊ የአቤቶ ልጅ ኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ››
ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)
….. የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤ የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡
✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡

❤15