አብነቶቻችን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ ለመንጋው የተሾሙ እስከ ሞትም የታመኑ እውነተኛ እረኞች ናቸው። ሥልጣናቸውም የሚመነጨው ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ ነው። ቸር ጠባቂያችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም እረኝነት የባሕርዩ ነው፡፡ ‹‹አነ ውእቱ ኖላዊ ኄር ዘበአማን፤ እውነተኛ ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤›› በማለት እንደ ተናገረው (ዮሐ. ፲፥፲፩)፡፡ ጌታችን ይህን መለኮታዊ ሥልጣኑን ለቅዱሳን በጸጋ አድሏቸዋል፡፡ ‹‹… ግልገሎቼን አሰማራ፤ ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ በጎቼን አሰማራ›› በማለት ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠው ሥልጣን ለዚህ ማሳያ ነው (ዮሐ. ፳፩፥፲፭-፲፯)፡፡
ስለ መልካም እረኛ ሲነሣ በአብነት ከሚጠቀሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል በረከታቸው ይደርብንና ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አንደኛው ናቸው፡፡ ጠላት አገራችንን በወረረበት፣ በመንጋው ላይ መከራ እና ችግር በጸናበት፣ እንደዚሁም የንጹሐን ደም በግፍ በፈሰሰበት በዚያ በፈተና ወቅት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለቤተ ክርስቲያንም ለአገርም የሚያስቡ መልካም እረኛ እንደ ነበሩ የታሪክ መዛግብት ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ከዐርበኞች ጋር ኾነው ሕዝቡ ለጠላት እጁን እንዳይሰጥና ሃይማኖቱን እንዳይለውጥ ከማስተማራቸው፣ ከማጽናናታቸው ባሻገር በጠላት ፊት ለፍርድ በቀረቡበት ጊዜም መልካም እረኝታቸውን በዐደባባይ መስክረው፣ ለሕዝብ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለአገር በመቆርቆራቸው በጥይት ተደብድበው በሰማዕትነት አልፈዋል፡፡
ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኩል የሚገባ ሌባ፥ ወንበዴም ነው፡፡ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው፡፡ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እርሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል፡፡ ምንደኛ (ቅጥረኛ) እረኛ ግን ለበጎቹ አይጨነቅም፤ በጎቹም አያውቁትም (ዘካ. ፲፩፥፬-፭፤ ዮሐ. ፲፥፩-፲፪)፡፡ ዛሬም በእናት ቤተ ክርስቲያናችን የተሾሙ አባቶች እንደነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለቤተ ክርስቲያንም ለአገርም የሚጨነቁ ሊኾኑ ይገባል፡፡
ጳጳሳት የህዝብን አንድነት የሚጠብቁ። በበጎቻቸው የማያደሉ ስለ በመንጋው አንድነት የሚገዳቸው ሊሆኑ ይገባል። እኛ ምእመናንም እግዚአብሔር አምላካችን መልካም እረኞችን እንዳያሳጣን መለመን ይኖርብናል፡፡ እንደዚሁም ራሳችንን ለሃይማኖታችን ማስገዛት፣ መልካም እረኞችንም አብነት ማድረግና መከተል ይጠበቅብናል፡፡

❤9👍3
«ልጆቼ ዓላማዬን ተከተሉ!»
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (1932 ዓ.ም— 1982 ዓ.ም)
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከአቶ ገበየሁ እሰዬና ከወ/ሮ አሰለፈች ካሣ በ1933 ዓ.ም በስእለት የተወለዱ ሲሆን ወደ ተቀደሰው የእግዚአብሔር ጎዳና ያመሩት ገና በሕፃንነታቸው ነበር። ዝናቸው ከታወቀው የተለያዩ ኢትዮጵያ ገዳማትና ብቃታቸው ከተመሰከረላቸው ሊቃውንት ዘንድ ዜማ፣ትርጓሜ መጻሕፍት፣ባሕረ ሐሳብ እና ቅኔ ተምረው ተመርቀዋል።
በዘመናዊ ትምህርታቸውም በየደረጃው ከአቴና ዩኒቨርስቲ በቲኦሎጂ (ነገረ መለኮት ) በማስትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል እንዲሁም ፈረንሳይኛና ዐረብኛ ቋንቋ አጥንተዋል።
በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው፣በትምህርታቸው፣በምርምር፣በሥነ ጽሑፍ እና በማስተማር ዘዴያቸው ባለተሰጥኦ እንደነበሩ ይነገራል።
የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንብሮተ እድ በ1971 ዓ.ም ጳጳስ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ሕይወታቸው በመኪና አደጋ እስካለፈበት ቀን ድረስ በጣም ድንቅና በርከታ ሥራዎችን አከናውነዋል።
በተለይም የዝዋይን የከህናት ማሠልጠኛ በገዳም ሥርዓት እንዲተዳደር አስወስነው በሺህ የሚቆጠሩ ካህናት እንዲሠለጥኑ፣ አባትና እናት የሌላቸው ሕፃናት እንዲያድጉበት ከማድረጋቸውም በላይ፣ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽና በዚሁ ሥፍራ የተለያዩ የልማት አውታሮችን በመዘርጋት አርአያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል።
ትምህርታቸው ልቡናን ሰብሮ የሚገባ፣በምሳሌዎች የተደገፈ እና ጥልቀት ያለው ነበር በአጠቃላይ «ትምህርታቸው እንደ ዐባይ ውኃ የሚፈስ ነበር» ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በአስተሳሰበቸው ሀገራቸውን፣ሕዝባቸውን የሚወዱ፣ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ፣እናት ለልጅዋ እንደምታስብ ሀገራቸውን የሚወዱ፣ሥጋዊ ጥቅም የማያታልላቸው፣በሃይማኖትም ሆነ በሀገራቸው ጉዳይ አድርባይነት የሌለበቸው፣ፍርሀት የሌለባቸው፣ እውነት የሚናገሩ እንደነበሩ ብዙዎች ይመስክራሉ፡፡
ለወጣቶች የተለየ ፍቅርና እንክብካቤ ያደርጉ የነበሩ፣በአቀራረባቸው የሚወደዱ እና ወጣቶችን “እናንተ የቤተ ክርስቲያን የስስት ልጆች ናችሁ፣የሰንበት ተማሪዎች የቤ ተክርስቲያን ችግኞች ናችሁ» በማለት በሃይማኖታዊ ፍቅር ይኮተኩቱ ነበር፡፡
ብፁዕነታቸው በዓለም መድረክ የቤተ ክርስቲያን መልእክተኛ የነበሩ ሲሆን ሦስት ጃማይካውያንን በዝዋይ አስተማረው ለማዕረገ ቅስና አብቅተዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራብዕ፣ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ካልዕ፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሣልስ፣ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ከብፁዕነታቸው ፍሬዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
አቡነ ጎርጎርዮስ የሃይማኖትና የታሪክ ተመራማሪም የነበሩ ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ስምንት መጻሕፍት ጽፈዋል። እነርሱም፡- መሠረተ እምነት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ)፣የስብከት ዘዴ( ኦርቶዶክሳዊ)፣ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ፣ሥርዓተ ኖሎት እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሲሆኑ እነዚህም መጻሕፍቶቻቸው በምርምር ላይ የተመረኮዙ፣ጥልቅ ምሥጢር ያካተቱ እና በውብ አገላለጽ የተሞሉ ናቸው።
በጻፉት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው ኢትዮጵያ በዘመነ ኦሪት፣ኋላም የክርስትናን እምነት ከተቀበለችበት ወቅት አንስቶ እስከ አሁን የተጓዘችባቸውን የታሪክ ሂደቶች የሚያሳይ፣በሥዕላዊ ቃላትና ጥልቅ ሐሳቦችን የሚገልጽ ድንቅ መጽሐፍ ነው።
በተጨማሪም መጽሐፉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት(ዶግማ)፣የታበት፣የሥዕልና የመስቀልን ክብር፣የአማላጅነት ምስጢር፣የቤተ ክርስቲያን ትውፊት እና ሥሪትን የሚያብራራ ነው።
ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡
ብፁዑነታቸው ከተናገሯቸው ድንቅ አባባሎች ውስጥ ስለ እመቤታችን መናገር የምንችለው ስለሰውና ስለ እግዚአብሔር ስናውቅ ብቻ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ነውና ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠናክሩ፣ሰው ፍላጎቱን ካላሸነፈ የእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፣ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው፣ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገር ናት፡፡
ለሠሩት እና ላበረከቱተት አስተዋጽኦዎች ትምህርት ቤቶች፣አዳራሾች፣ቤተ መጻሕፍት እና ሐውልት በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ

❤13🙏2👍1