Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
‹‹ሐምሌ 10›› በዚህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል ነው።

ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእስራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው::

ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 14,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር::

ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::

ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::

ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል::

ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እስራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል::

ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::

የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል::

ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል::

የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል በረከቱ ይደርብን🙏
23🥰1
ሐምሌ 15 - ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ስንክሳሩ እንደሚለው ቅዱስ ኤፍሬም ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው፣ አባቱም የጣዖት ካህን ነበር፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው በ306 ዓ.ም ገደማ “በሜሶፖታሚያ” ውስጥ በምትገኝ “ንጽቢን” በተባለች ቦታ ነው፡፡ (ንጽቢን በደቡባዊ ቱርክ እና በምዕራባዊ ሶርያ መካከል የምትገኝ ቦታ ናት፡፡) ይህቺም ቦታ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ የነበረው የቅዱስ ያዕቆብ ሀገረ ሰብከቱ የነበረች ናት፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ተወልዶ ባደገባት ሀገረ ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር፡፡ እርሱም የሰማዕትነት፣ የሐዋርያነት፣ የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ይሄ አባት ሁልጊዜ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማረከ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ አመላክቶት ወደ ቅዱስ ያዕቆብ ሄዶ ትምህርተ ክርስትናን ተምሮ የተጠመቀ ሲሆን ከወላጆቹ ጋር የኖረው እስከ አሥር ዓመቱ ብቻ ነው፡፡ በትምህርተ ክርስትና አምኖ ከተጠመቀ በኋላ ግን በቅዱስ ያዕቆብ ዘንድ በብሕትውና ተወስኖ በመማርና በማስተማር ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት እየተጋደለ ሲኖር የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ አሕዛብንም ተከራክሮና አስተምሮ ይረታቸው ጀመር፡፡
በ325 ዓ.ም 318ቱ ኤጲስቆጶሳት ቢሆንላቸው አርዮስን አስተምረው መክረው ከክህደቱ ለመመለስ እሺ ባይላቸው ግን አውግዘውት ለመመለስ በኒቅያ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ኤፍሬም ከአባ ያዕቆብ ጋር አብሮ በጉባኤው ተገኝቶ ነበር፡፡ አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ፡፡ የዚህንም ራእይ ምሥጢር ይረዳ ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡ ‹‹ይህ የቂሣው ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው›› የሚል ቃል ከሰማይ ወደእርሱ መጣ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወዶ ቂሣርያ ሀገር ተጓዘ፡፡ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ ቅዱስ ባሰልዮስን ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ወንጌልን ሲያነብ አየው፡፡ ሦስት ምልክቶችንም እስኪያይ ድረስ በልቡ ተጠራጠረ፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ ነጭ ርግብ መጥታ በቅዱስ ባስልዮስ ላይ አረፈች፡፡ ቀጥሎም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተሕዋሲያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር፡፡ ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል እየወጣ ምእመናን ላይ ሲያርፍ ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠርቶት ሰላምታ ተሰጣጡና በአስተርጓሚ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ምሥጢር በአስተርጓሚ አይሆንም የአንዳቸው ቋንቋ ለአንዳቸው ይገለጥላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ የአንዳቸው ቋንቋ ለአንዳቸው ተገልጦላቸው ሁለቱም ነገረ እግዚአብሔርን ሲነጋገሩ አደሩ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው፡፡ ከጥቂት ወራትም በኋላ ቅስና ሾመው፡፡ ከዚህም በኋላ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ አበራ፡፡ አንዲት በወገን የከበረች ባለጸጋ ሴት ነበረች፡፡ እርሷም ራሷን ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር፡፡ ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ በዝርዝር ጽፋ በክርስታስ አሽጋ እንዲጸልይላትና ኃጢአቷን ይደመስስላት ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስን ለመነችው፡፡ እርሱም ‹‹ይሁን እንዳልሽው ይሁንልሽ›› ብሎ ጸልዮላት ከአንዲት ኃጢአቷ በቀር ሁሉንም በጸሎቱ ደመሰሰላት፡፡ እርሷም ክርታሱን በገለጠችው ጊዜ ከአንዲቷ ኃጢአት በቀር ሌሎቹ ሁሉም ተደምስሰው ጠፍተው አገኘች፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ስለ አንዲቱም ኃጢአቷ ወደ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲትሄድ አዘዛት፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ‹‹ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሂጂ ነገር ግን ሞቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኚዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይህችን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመስስልሻል›› ብሎ መልሶ ላካት፡፡ በተመለሰችም ጊዜ ቅዱስ ባስልዮስ ዐርፎ ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት አገኘችው፡፡ እርሷም መሪር ልቅሶን ካለቀሰች በኋላ ቅዱስ ኤፍሬም እንዳዘዛት በእምነት ሆና ያንን ክርስታስ በቅዱስ ባስልዮስ አስክሬን ላይ ጣለችው፡፡ ወዲያውኑም ያች የቀረች ኃጢአቷ ተደመሰሰችላት፡፡ ክርታሱም ምንም ጽሕፈት የሌለበት ባዶ ሆነ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሌሎች እጅግ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፣ መናፍቃንን ተከራክሮ እረቷል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመረ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን በሚገባ ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር፡፡ እንደ ዛሬው የእመቤታችን ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበርና ቅዱስ ኤፍሬም ግን ከወንጌለ ከሉቃስ ወንጌል በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ 64 ጊዜ ያመሰግናት ነበር፡፡ እመቤታችንን ከልብ ከመውደዱ የተነሳ ‹‹የእመቤታችን ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባህር ሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው እንደ ውኃ ጠጥቼው ረክቸው›› እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር፡፡ የሻቱትን መስጠት ለመንፈስ ቅዱስ ልማዱ ነውና ቅዱስ ኤፍሬም የፈለገውን ገልጦለታል፡፡ አምላክን የወለደች እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጣለት የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት፡፡ ዛሬ እየጸለይነው ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት፡፡ ውዳሴዋን ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ ቅዱሳን መላእክትን ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ በፊቱ ትቀመጣለች፤ እርሱም ባጭር ታጥቆ በፊቷ ቆሞ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ነው፡፡ ዕለቱ ሰኑይ ነግህ ነው እንዲህም ሆነ፡- የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች፡፡ የብርሃን ምንጻፍ ይነጠፋል፣ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፣ ከዚያ ላይ ሁና ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ወፍቁረ ወልድየ ኤፍሬም›› ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ‹‹ወድሰኒ›› ትለዋለች›› እርሱም ‹‹ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ጻድቃን ሰማዕታት አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል?›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለህ ተናገር›› አለችው፡፡ ‹‹ባርክኒ›› ይላታል፡፡ እርሷም ‹‹በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌክ›› ትለዋለች፡፡ ጥዑመ ልሳን ቅዱስ ኤፍሬምም ተባርኮ መንፈስ ቅዱስ እንዳጸናው ቀለም ሰተት አድርጐ አመስግኗል፤ ስታስደርሰውም በሰባት ከፍላ አስደርሳዋለች፡፡ ምስጋናዋም የሰባቱ ዕለታት ውዳሴ ማርያም ነው፡፡ የእመቤታችንን ውዳሴዋን በ7 ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ከዚህ በኋላ ‹‹አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ›› እስከሚል ድረስ ከእመቤታችን ውዳሴ ሌላ 14 ሺህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደርሷል፡፡ ብዙውን ድርሰቱን መላእክት ደብቀውታል፣ ወስደውም ለምስጋና ተጠቅመውበታል፡፡ መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ጌታችን እመቤታችንንና ቅዱሳንን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ ተገልጦለት ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ ቅድስት ነፍሱን በክብር ተቀብሏታል፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም የደረሳቸውን የእነዚህንም የሰባቱን ዕለታት የውዳሴ ማርያም ዜማቸውን ቅዱስ ያሬድ ደርሶታል፡፡ አክሱም ጽዮን እየተሳለማት ሳለ የብርሃን እናት እመቤታችን ተገልጣለት ቅዱስ ኤፍሬምንና ቅዱስ አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አምጥታ ድርሰታቸውንና ቅዳሴያቸውን ያሰሙታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመልክ በመልኩ እያደረገ ዜማውን ደረሰው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዜማውን ሲጨርስ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ በያዘችው የብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው ዐርጋለች፡፡ ለቅዱስ ኤፍሬም የተለመነች የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ለእኛም ትለመነን!
25
ሐምሌ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን ቅዱስ አባት ወንጌሉ ዘወርቅ የተባለ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ነበር አባቱም አጥራብዮስ የሚባል ባለጠጋ ነው። የእናቱም ስም ብዱራ ይባላል። እንዲማርም ለመምህር ሰጡት ቅዱሳት መጻሕፍትንም ተማረ።
ከዚህም በኋላ ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራለት ዘንድ አባቱን ለመነው አባቱም እንደፈለገው አሠራለት ሁል ጊዜም ያነበው ነበር። በሚያነብ ጊዜም አባቱና እናቱ ደስ ይላቸው ነበር።
በዚያም ወራት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ መነኵሴ ወደ እነርሱ መጣ በእነርሱም ዘንድ አደረ ከቅዱስ ዮሐንስም ጋራ ተነጋግሮ የምኵስናን ሥራ አመሰገነለት ይህን ዓለም እስከ ናቀና እንደ እርሱ መነኰስ ይሆን ዘንድ እስከ ወደደ ድረስ ልቡን ማረከው።
ያን ጊዜም ያ መነኰስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ሁለተኛም ተመልሶ እንደ ልማዱ በእነርሱ ዘንድ አደረ። ቅዱስ ዮሐንስም መነኵሴው ወደ ገዳሙ ይወስደው ዘንድ ፈለገ መነኲሴውም አባትህን እፈራዋለሁ ልወስድህ አይቻለኝም አለው። ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሱ ጋራ እንዲወስደውና ነፍሱን እንዲያድን አማለው።
ከዚህም በኋላ በስውር ወሰደው በመርከብም ተጭነው ያ መነኰስ ወደሚኖርበት ገዳም ደረሱ የገዳሙም አበ ምኔት የወጣቱን ዮሐንስን መልኩን አይቶ አደነቀ። ቅዱስ ዮሐንስም የምንኵስናን ልብስ ያለብሰው ዘንድ አበ ምኔቱን ለመነው አበ ምኔቱም ልጄ ሆይ የምንኵስና ሕግ እጅግ ጭንቅ ናት እኮ አለው። አብዝቶም በለመነውና ግድ ባለው ጊዜ ራሱን ላጭቶ አመነኰሰው።
ከዚህም በኋላ ከጾም ከትጋትና ከኀዘን የተነሣ ሥጋው ደርቆ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ በብዙ ተጋድሎ ተጸመደ። አበ ምኔቱም ልጄ ሆይ ለሰውነትህ እዘን ድካምህንም ቀንስ መነኰሳቱም ሁሉ እንደሚሠሩት ሥራ እያለ ያጽናናውና ይመክረው ነበር።
በዚህ ተጋድሎም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከእነርሱ በረከትን ትቀበል ዘንድ ከመሞትህ በፊት ወደ አባትህና እናትህ ሒድ የሚል ራእይ አየ። ይህንንም ራእይ በሦስት ሌሊቶች ውስጥ አየ ለአበ ምኔቱም እንዴት እንዳየ ነገረው አበ ምኔቱም ይህ ራእይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ ልትሔድ ይገባሃል አለው። ከገዳሙም በወጣ ጊዜ አንድ ምስኪን ሰው ጨርቅ ለብሶ አገኘ። የእርሱንም ልብስ ሰጥቶት ጨርቁን ወሰደ።
ወደ አባቱ ቤትም በደረሰ ጊዜ በትንሽ ጎጆ ውስጥ በአባቱ ደጅ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደለ ባሮች ከአባቱ ማዕድ የሚጥሉለትን ፍርፋሪ እየተመገበ ሰባት ዓመት ኖረ። እናቱም በአንጻሩ ስታልፍ የሚከረፋ ሽታው ያስጨንቃት ነበር። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰባት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ትወጣለህ ብሎ ነገረው።
ያን ጊዜም ወደ እናቱ ልኮ ልመናውን ልትሰማ ወደ እርሱ መጣች ልጅዋም እንደሆነ ፈጥኖ አልነገራትም ነገር ግን በዚያች በታናሽ ማደሪያ ውስጥ በላዩ ባለ ጨርቅ እንድትቀብረው የለበሰውንም ጨርቅ እንዳትለውጥ አማላት። ከዚህም በኋላ ያንን የወርቅ ወንጌል ሰጣት። እንዲህም አላት ይህን መጽሐፍ አንብቡ እኔንም አስቡኝ።
አባቱም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል አሳየችው እርሱም ለልጁ ያሠራለት ወንጌል እንደሆነ አወቀ። አባቱና እናቱም ወደ እርሱ ሔደው ስለ ልጃቸው ጠየቁት እርሱም ከዚህ ጨርቅና ከዚህ ትንሽ ማደሪያዬ ውስጥ በቀር በሌላ እንዳትቀብሩኝ ማሉልኝ አላቸው።
በአማላቸውም ጊዜ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ ነገራቸው ያን ጊዜም ጮኹ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ የሮሜ ከተማ ሽማግሌዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበሰቡ ሰባቱ ቀንም ሲፈጸም ቅዱስ ዮሐንስ አረፈ። እናቱም መሐላዋን ረስታ አስቀድማ ለሠርጉ ያዘጋጀቻቸውን ያማሩ ልብሶች አውጥታ ገነዘችው። በዚያችም ጊዜ ታመመች አባቱ ግን መሐላውን አስታውሶ እነዚያን ያማሩ ልብሶች አስወገደ በጨርቆቹም ገነዙት በዚያ በትንሹ ማድሪያም ውስጥ ቀበሩት ከሥጋውም በሽተኞች የሚፈወሱበት ታላቅ ድኅነት ተገኘ።
ከዚህም በኋላ በስሙ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ። ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፤ ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ
11
#እንኳን አደረሳችሁ

#በመዲናችን_በአዲስ_አበባ__የቅዱስ_ገብርኤል_እና_የቂርቆስ_ኢየሉጣ_በዓል_የሚከበሩባቸው #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩) ፠ (መ.መ.ገ.) መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤ በ1889 ዓ.ም. የተመሠረተ፤
፠ አስኮ ቅዱስ ገብርኤል፤
፠ ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል፤
፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል)
፭) ፠ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል
፠ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በ.ክ.
፠ ደብረ ገነት ፉሪ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት አርሴማና አቡነ አዳም ቤ.ክ.
፲) ፠ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ መካነ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ አለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፠ ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፲፭) ፠ ደብረ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ጋራ ኦዳ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ አንቆርጫ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ጉራራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፠ ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፳፠ አቃቂ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ቦሌ ሃራብሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ቦሌ ቡልቡላ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ.ክ.
፳፭) ፠ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ (የቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. በድርብነት በውስጥ አለ)
፠ ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፠ ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት ይከብራል)
፠ ደብረ ገሊላ አማኑኤል ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፴) ፠ ጀሞ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ.ክ.
፠ አቃቂ ጃቲ መካነ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)
፠ ቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ የካ አባዶ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ገብርኤል
፴፭) ፠ ኮልፌ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ቤ/ክ (በድርብነት ይከብራል)
፠ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ. (አዲሱ ሚካኤል) (በድርብነት ይከብራል)
፠ ካራ ቆሬ ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ድልበር መካነ ጎልጎታ መድኀኔዓለም (በድርብነት ይከብራል)
፠ አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ (አዲስ ሰፈር)
፵)፠ ደብረ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም ስር የሚገኘው ሙት አንሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ መንበረ ልዑል ገብርኤልና ማርያም ቤ.ክ.፤
፠ አየርጤና ደብረ ብሥራት ገብርኤልና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.
፠ ቱሉ ዲምቱ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.
፠ ቀበና ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅ/ገብርኤል ቤ.ክ.
፵፭) ፠ መጠሊ ደብረ አሮን ፍልፍል ዋሻ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ.ክ.
፠ ቂሊንጦ ደብረ ብሥራት ገብርኤልና ማርያም፤
፠ ደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል)፡፡
፠ አንቀጸ ምሕረት (ራስ ካሣ) ቅዱስ ሚካኤል፤ (በድርብነት ይከብራል)
፠ ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም፤ (በድርብነት ይከብራል)
፶) ፠ ቦሌ ቡልቡላ ድብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም፤ (በድርብነት ይከብራል)
፠ ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ማርያም፤ (በድርብነት ይከብራል)
፠ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በድርብነት ይከብራል)
፠ ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ (በድርብነት ይከብራል)
፶፬) ፠ ብሥራተ ወንጌል ቅድስተ ማርያም ቤ.ክ.፤ (በድርብነት ይከብራል)
#በሃገራችንና_በዓለም_አቀፍ__በዓላቸው_የሚከበሩባቸው_ጥንታውያን #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩) ዘብር ቅዱስ ገብርኤል (መንዝ ሰ ሸዋ)
፪) ወይቅን ቅዱስ ገብርኤል (ቆላ ተንቤን)
፫) ክብራን ገብርኤል (ጣና ጎጃም)
፬) ቦሎ ገብርኤል (መርሐ ቤቴ)
፭) ጎንደር አቡን ቤት ገብርኤል
፭) ደሴ ገብርኤል
፮) ናዝሬት ገብርኤል
፯) ቁልቢ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል
፰) ባሕር ዳር ዐባይ ማዶ ገብርኤል
፱) ሐዋሳ ገብርኤል
፲) ድሬደዋ ሳባ ገብርኤል

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
7👏1
እንኳን አደረሳችሁ

የ2016 ዓ.ም ሐምሌ ገብርኤል እና ቂርቆስ ኢየሉጣ በዓል ፎቶ ማስታወሻ ፣

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
1