የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቀ ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ ተዘጋጅቶ የሚተላለፉ ማንኛቸውም ትምህርቶች ፣ መዝሙራት ፣ ቪዲዮዎች ፣ ቃለ መጠይቆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ መሆናቸው ሙሉ የአርትኦት / ኦዲቶርያል ስራዎች/ ከገዳማችንና ከሰንበት ትምህት ቤታችን በተመደቡ አባቶች እና መምህራን አማካኝነት ሲረጋገጥ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በዚህ መሠረት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፣ ትምህርቶችን እና መዝሙራትን በማቅረብ ምዕመናን ወደ ንስሀና ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀርቡ ለማድረግ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና መምህራንን የህይወት ተሞክሮ ለትውልዱ በማስተዋወቅ አሰረ ፍኖታቸውን እንዲከተሉ ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የጻድቃን ሰማዕታት ተጋድሎ እና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጸጋ ለማስተዋወቅ ብቻ እንዲተላለፉ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን ፣የቤተክርስትያንን ስርዓቶች ለትዉልዱ ለማስተዋወቅ፣ ትዉልዱ ምንነታቸዉን ተረድቶ እንዲጠቀምባቸዉ እና እንዲጠብቃቸው ፣መስማት ለተሳናቸዉ የቤተክርስትያኒቱ ልጆች በቋንቋቸዉ ተከታታይ ትምህርቶችን እንዲማሩ ለማድረግ፤ የቤተክርስትያናችንን፤ የገዳማችንን እና የሰንበት ት/ቤታችንን መንፈሳዊ እና የልማት ስራዎችን ለምዕመና ይህንን ለትዉልዱ እና ለቤተክርስትያን ጠቃሚነቱ የታመነበትን (ዘመናዊ ስቱዱዮ ) ገንብተን ስራ ለማስጀመር፣ ለዚህ የምረቃ ቀን እንድንበቃ ለረዳን ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ይሁን በማለት ብፁዕነታቸውን እና የገዳሙን አስተዳደር ጽ/ቤት አመስግነዋል ።

❤19
ሰኔ ፳፬ #አባ_ሙሴ_ጸሊም በሰማዕትነት አረፈ
ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር።
አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ቀን ወይን ጠጅ እንደ ሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል።
እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር።
ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው።
ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው።
እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተ ማረው እንዲህም አለው ታግሰህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ።
ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ።
ሰይጣንም አስቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብልና በመጠጡ በዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር።
ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእነርሱ ሩቅ ነበረና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ።
ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ።
እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበምኔት ሆነ።
ከዚህ በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ ባቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር፤ አረጋውያኑንም ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት አላቸው፤ #እርሱም "መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ፣ መልካም አደረጉብህ" በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ።
በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህ በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጒድጓዶችን ሁሉ ሞላ።
አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም እግዚ አብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገ ልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር፤ በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን አላቸው።
በአንዲትም ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋራ ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ አላቸው አባ ሙሴም አባቴ ሆይ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና ብሎ መለሰ።
ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ አላቸው እነርሱም አባታችን አንተስ አትሸሽምን አሉት እርሱም #በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለሚለው የእግዚእብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ አላቸው።
ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስላአልፈለጉ ከእርሱ ጋራ ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መልአክ እየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም ባየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ፤ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕትነ ትንም እክሊል ተቀበለ።
ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርሰቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው #የንስሐን_ኃይሏን_ተመልከቱ።
ሥጋውም በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
#ሰኔ #፳፬ ፤ #በዓለ_ዕረፍቱ_ለአቡነ_ሙሴ_ጸሊም_፡፡
#በአገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የአቡነ_ሙሴ_ጸሊም_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን #፪
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ ጨምሩበት፡፡)
፩. ግብጽ ሰሜን ምዕራብ ኒትሪያን በረሐ ባራሞስ እመቤታችን ገዳም፤ (የቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊምና የመምህሩ የቅዱስ አባ ኤስድሮስ የከበረ ዐፅማቸው በክብር ያረፈበት)
አድራሻ፤ ግብጽ ሃገር፥ ሰሜን ምዕራብ ኒትሪያን በረሐ፥ ባራሞስ እመቤታችን ገዳም፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብጽ → ሰሜን ምዕራብ ኒትሪያን በረሐ፡፡
፪. ሐመር ቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሙሴ ገዳም፤
አድራሻው፤ ደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት፥ ሐመር፥ ቡስካ ተራራ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → አርባ ምንጭ → ሐመር → ቡስካ፤
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤15