የአንጾኪያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኤፍሬም ፪ኛ እና በዱሊያ የማር ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ፲ኛ በደማስቆ ዱሊያ አካባቢ በሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን ላይ በደረሰው የሽብር ጥቃት ያረፉ ሰማዕታት ነፍስ በማሰብ ጸሎተ ፍትሐት አድርገዋል።
ከጸሎት በኋላ በሆስፒታል ውስጥ ተገኝተው የቆሰሉት እና የተጎዱት በፍጥነት እንዲያገግሙ ጸሎት አድርገዋል።
የቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በደማስቆ እና በአካባቢዋ ከሚገኙት ታዋቂ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው። ከነቢዩ ኤልያስ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በጥንታዊ እና ታሪካዊነቱ ይታወቃል።
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤20🥰3
#ደብር_ቅዱስ_ደብረ_ጽጌ_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን፡፡
ፎቶውን የምታዩት ቤተ ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በ90 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት የመሠረቱትና ኋላ ግራኝ አፍርሶት ቆይቶ በ1951 ዓ.ም. በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ድጋሜ የታነጸው ደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም ነው፡፡ ይህ ገዳም፤
✜ አቡነ ተክለሃይማኖት በአቅራቢያው ካለው ደብረ ከርቤ ከሚባል ገዳም ጋር የመሠረቱትና ይቀድሱበት የነበረ ታላቅ ገዳም ነው፡፡
✜ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የጋራ መናገሻ መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ባርከው ሲመለሱ ዓረፍተ ዘመናቸው ደርሶ ያረፉበት ሲኾን፤ ኋላ ደቀ መዛሙርቶቻቸው ወደ መሠረቱት ታላቁ ገዳም ወደ ጋሥጫ ይዘው ወስደው በሰላም አሳርፈዋቸዋል፡፡
✜ አፄ ዮሐንስና አፄ ምኒልክ ተጣልተው ቆይተው ኋላ እርቅ ያወረዱት በዚሁ ገዳም ነው፡፡
✜ በግራኝ ወረራ ጠፍቶ ቆይቶ፤ ድጋሜ ደግሞ በጣሊያን ብዙ መከራ ደርሶበት ከቆየ በኋላ፤ በመጀሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በ1951ዓ.ም. በራሳቸው ገንዘብ በድጋሚ በሚደንቅ የሕንፃ አሠራር አስፋፍተው ያሠሩትና የገደሙት ገዳም ነው፡፡ ዳግመኛ ሲያሳንጹትም ከታላላቅ ቅዱሳን ገዳማት አፈር አስመጥተው ያስነሰነሱበት፣ የከበሩ ንዋያትን ከመሠረቱ በታች ያኖሩለት ታላቅ ገዳም ነው፡፡
✜ ገዳሙን ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ ህልውናው ተጠብቆ እንዲቀጥል፤ በበላይነት ኀላፊነቱን የቤተ ክህነት መንፈሳዊ ጕባኤ ተረክቦ እንዲያስተዳድር አደራ የሰጡት ገዳም ነው፡፡
✜ አቡነ ባስልዮስ በድጋሜ ሲገድሙት በኢትዮጵያ የሚሰጡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ኹሉ እንዲሰጡበት አድርገው ነበር፤ ምንም እንኳን አሁን በተወሰነ መልኩ ቢደበዝዝም ንከባብ እስከ ትርጓሜ ቤት ያሉ ጕባኤያት አሁንም እየተካሄዱበት የሚገኝ የቤተ ክርስቲያናቸው ማገር የኾነ የትምህርት ማዕከል ነው፡፡
✜ ጳጳሳትን (ከ17 በላይ)፣ ሊቃውንትንና መምህራንን ያፈለቀና እያፈለቀ የሚገኝ ዐዘቅተ ጥበብ ገዳም ነው፡፡
✜ ከአምስት በላይ ፈዋሽ ጸበል ያለበት ገዳም ነው፡፡
✜ 3 መቅደሶች (መቅደሰ ማርያም መቅደሰ ሚካኤልና መቅደሰ ተክለ ሀይማኖት ያሉበት፤ (በአዘቦት ቀን በ7 ደናግል መነኰሳት የሚቀደስባት፤ በትንዓኤና በዘመነ ጽጌ በ21 ደናግል መነኰሳት በ3ቱም መቅደሶች የሚቀደስበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡)
✜ ከዓመት እስከ ዓመት ሌሊትና ቀን ስብሐትና ጸሎት የማይታጎልበት (በዐቢይ ጾም ዳዊት ሲስተዛዘል ዳዊት የሚያስተዛዛለው /የሚደግመው ከመብዛቱ የተነሣ/ እንኳን አንድ አንድ ንጉሥ (10 ምዕራፍ) ይቅርና አንድ አንድ ምዕራፍ እንኳን ማዳረስ ባለመቻሉ በሦስት ፈረቃ ዳዊት የሚተዛዘልባት ታላቅ የመምህራንና የተማሪዎእ መሰባሰቢያ ገዳም ነው፡፡
✜ በአካባቢው የሚገኘው ‹‹ደብረ ጽጌ›› ከተማ ስያሜውን ያገኘው ከዚሁ ደብረ ነው፡፡
#ኢየሩሳሌም_ደብረ_ገነት_ኪዳነ_ምሕረት_
በመምህር ወልደ ሰማዕት አማካኝነት፤ አፄ ዮሐንስ ፬ኛ አስጀምረውት አፄ ምኒሊክ ያስፈጸሙት እስራኤል ከሚገኙ አፅመ ርስታችን አንዱና ዋነኛው፡፡

❤7
ሰኔ 21 ሰኔ ጐልጐታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
‹‹ሰኔ ጐልጐታ ፤
ችግር የምትፈታታ፡፡››
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህች ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ሰኔ ጐልጐታን ተመልከት
✤✤ ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን፤
ሰኔ 21 ከእመቤታችን #33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው በዚሁ እለት በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡
አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፤ ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ፤
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::
የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን››ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ #ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱመኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ::
በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡
በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡
ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
✜ በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹ ‹‹አክስዮስ››(አክዮስ)እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው::
ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ::
✤✤ ሥርዐተ ማኅሌቱ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠሙበበት ዘንድ የሁለቱንም (የላይ ቤት የግምጃ ቤትና የታች ቤት የበአታን) አብነት አስቀምጠንላችኋል፤ በቢጫ የተቀለመው የላይ ቤት (የግምጃ ቤት) አብነትን ለምትከተሉ አድባራት ሲኾን፤ ሰማያዊ የተቀለመው ደግሞ የታች ቤትን (የበዓታን) የአቋቋም ይትበሃል ለምትጠቀሙ ሲኾን፤ ሁለቱም የላይ ቤቱና ያየታች ቤቱ የሚተባበሩበት ላይ ደግሞ ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ ብለን በፈዛዛ ጥቁር አስቀምጠንላችኋል፡፡ መልካም ማኅሌት፨
ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡
✼ የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን::

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤20
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቀ ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ ተዘጋጅቶ የሚተላለፉ ማንኛቸውም ትምህርቶች ፣ መዝሙራት ፣ ቪዲዮዎች ፣ ቃለ መጠይቆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ መሆናቸው ሙሉ የአርትኦት / ኦዲቶርያል ስራዎች/ ከገዳማችንና ከሰንበት ትምህት ቤታችን በተመደቡ አባቶች እና መምህራን አማካኝነት ሲረጋገጥ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በዚህ መሠረት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፣ ትምህርቶችን እና መዝሙራትን በማቅረብ ምዕመናን ወደ ንስሀና ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀርቡ ለማድረግ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና መምህራንን የህይወት ተሞክሮ ለትውልዱ በማስተዋወቅ አሰረ ፍኖታቸውን እንዲከተሉ ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የጻድቃን ሰማዕታት ተጋድሎ እና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጸጋ ለማስተዋወቅ ብቻ እንዲተላለፉ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን ፣የቤተክርስትያንን ስርዓቶች ለትዉልዱ ለማስተዋወቅ፣ ትዉልዱ ምንነታቸዉን ተረድቶ እንዲጠቀምባቸዉ እና እንዲጠብቃቸው ፣መስማት ለተሳናቸዉ የቤተክርስትያኒቱ ልጆች በቋንቋቸዉ ተከታታይ ትምህርቶችን እንዲማሩ ለማድረግ፤ የቤተክርስትያናችንን፤ የገዳማችንን እና የሰንበት ት/ቤታችንን መንፈሳዊ እና የልማት ስራዎችን ለምዕመና ይህንን ለትዉልዱ እና ለቤተክርስትያን ጠቃሚነቱ የታመነበትን (ዘመናዊ ስቱዱዮ ) ገንብተን ስራ ለማስጀመር፣ ለዚህ የምረቃ ቀን እንድንበቃ ለረዳን ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ይሁን በማለት ብፁዕነታቸውን እና የገዳሙን አስተዳደር ጽ/ቤት አመስግነዋል ።

❤19