እንኳን ለአምላካችንና ፈጣሪያችን ቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡
ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ገዳማትና አድባራት ዐበይቶቹ (እናንተም የምታውቋቸውንና በአቅራቢያችሁ ያሉትንከነፎቷቸው ጨምሩበት)
፠ ኦፍና አማኑኤል፤ መርሐ ቤቴ፥ አለም ከተማ፤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ጥንታዊ ቤ.ክ.
፠ ኤነር አማኑኤል፤ ምድረ ጕራጌ፤ እጅግ በጣም ጥንታዊ ገዳም
፠ ደብረ መንክራት በጎል ሰከበ ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል፤ ከደብረ ብርሃንና አንኮበር መሃል ላይ የሚገኝ፤ በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የተመሠረተ፤ እጅጉን በጣም ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበትና የቅዱሳን መናኸሪያ የኾነ፡፡
፠ ጫገል ቅዱስ አማኑኤል /በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ/
፠ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል፣ አዲስ አበባ፤ መርካቶ መሳለሚያ
፠ ባሶ ወረዳ ጣፎ ደብረ ሰላም ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን፤ ከጢያ ከተማ ወደ አጠገብ የሚገኝ፡፡

❤10
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ
ሥርዐተ ማኅሌቱ በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ በኹሉም ገዳማትና አድባራት ይከበራል፤ ነገር ግን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ይልቁንም በአዲስ አበባ ብቸኛ በኾነው #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስና_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገብ) ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል (መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡
#በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ
እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡
ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤
፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡
፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡
፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡
ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡
***አማናዊ ትርጓሜ - በሐዲስ
ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡ በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡
የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፡- “ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን” በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
#ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ
ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው: /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው
ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡
#መንፈስ_ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ የሚቀደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፤ አይወልድም፤ አይወለድም፡፡
በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_የሚከብርበት_ #፫_ብቸኛው_ደብር፡፡
፩ኛ). #ጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያትና_ጎላ_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ኢምግሬሽን አጠገብ፥ ጎላ፤
፪ኛ). #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት ት/ቤት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት (አስኮ በሚለው ታክሲ)፤
፫ኛ). #መንበረ_ልዑል_ቅዱስ_ማርቆስ_ቤ/ክ
አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ፤

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤24
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፩ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩ኛ). #ደብረ_ሕይወት_ማይዳዕሮ_ጰራቅሊጦስ_ገዳም፤ (እመቤታችን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት፤ ጃንደረባው ባኮስ አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ዓዲ አቡን (ኤርትራ ጠረፍ)፤
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤3
#ጾመ_ሐዋርያት (ሰኔ 02 - ሐምሌ 5)
(የ2017 ዓ.ም)
በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚጀምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መካከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2017 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 01 ይገባል ፡፡
ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይህ ታላቅ ጾም በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይህ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርየት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡
‹‹#ሙሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲሆን ይህን ጾም ከዕረገት በኃላ የምንጀምረው ፤ ይህን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ አስር ቀን ዘግይቶ መጀመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡
ይህ ጾም በአላዋቂዎች እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ትንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይህንን አውቀን ሁላችንም ልንጾመው ይገባል ፡፡

❤16🙏5