#_ግንቦት_26_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታቸው_ነው፡፡
፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤
፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤
፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ፨
፠በመራ ውዕይ (ሸዋ ፥ ቡልጋ) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መንና ነበር፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡
፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡
፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡ ለአብነትም፤
*ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
*በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
*ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርል፤
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
*በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
*የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
*"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለለት ታላቅ አባት ነው፡፡
፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡
*የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡
፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው::
"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው::
+ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::
ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
1. #_መብረቅ፣ 2. #_ቸነፈር፣ 3. #_ረሃብ፣ 4.#_ወረርሽኝ፣ 5.#_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)
#ሰላም_ለጽንሰትከ_እማኅፀነ_ቅድስት_ዮስቴና፤
#በብሥራተ_ጻድቅ_ባሕታዊ_ሠናየ_ዜና፡፡
#ሀብተማርያም_ጴጥሮስ_ሐዋርያ_ወልደ_ዮና፤
#መሐረኒ_ምግባረ_ጽድቅ_ወጸግወኒ_ልቡና፤
#አፍቅሮ_ቢጽ_እኅሥሥ_ዘምስለ_ፍጽመት_ትሕትና፡፡
ፎቶ ላይ የሚታየው ገዳም፤
፨ ብሔረ ብፁዓን ድበረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም፤ የጻድቁ የተጋድሎ መካን፤ ከደብረ ሊባኖስ ወረድ ብሎ
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤24
እንኳን ለአምላካችንና ፈጣሪያችን ቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡
ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ገዳማትና አድባራት ዐበይቶቹ (እናንተም የምታውቋቸውንና በአቅራቢያችሁ ያሉትንከነፎቷቸው ጨምሩበት)
፠ ኦፍና አማኑኤል፤ መርሐ ቤቴ፥ አለም ከተማ፤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ጥንታዊ ቤ.ክ.
፠ ኤነር አማኑኤል፤ ምድረ ጕራጌ፤ እጅግ በጣም ጥንታዊ ገዳም
፠ ደብረ መንክራት በጎል ሰከበ ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል፤ ከደብረ ብርሃንና አንኮበር መሃል ላይ የሚገኝ፤ በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የተመሠረተ፤ እጅጉን በጣም ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበትና የቅዱሳን መናኸሪያ የኾነ፡፡
፠ ጫገል ቅዱስ አማኑኤል /በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ/
፠ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል፣ አዲስ አበባ፤ መርካቶ መሳለሚያ
፠ ባሶ ወረዳ ጣፎ ደብረ ሰላም ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን፤ ከጢያ ከተማ ወደ አጠገብ የሚገኝ፡፡

❤10