Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት በዐቢይ ጾም ሰንበታት በ54 አብያተ ክርስቲያናት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላይ ለተሳተፉና በጎ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት የምስጋና እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠ።

በየክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነቱ በአንደኛነት ከተመሰገኑ አድባራት መካከል ደብራችን #ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ቤተክርስቲያን
በዐብይ ጾም በተዘጋጀው ልዩ ጉባኤ ከ54 አድባራት እና ገዳማት መካከል የላቀ ዝግጅት እና አመርቂ ጉባኤ በማዘጋጀት በአንደኛነት ከተመሰገኑ አድባራት መካከል ተሸላሚ ሆኗል።

ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሀገረ ስብከቱ  የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል አዘጋጅነት በዐቢይ ጾም ሰንበታት የተሰጠውን የወንጌል አገልግሎት  በእጅጉ አድንቀው አገልግሎቱን የመሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍልና የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት እንዲሁም እስከ ታች ባለው የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር የተቀመጡትን አገልጋዮች አመስግነዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለው የቤተ ክርስቲያናች መግቢያ  ፣ መኖሪያውና  መድረሻው የሆነው የቅዱስ ወንጌል አግልግሎትን ዓላማውን በተረዳና  ዘመኑን ባነበበ መልኩ መሰጠት እንዳለበት  ለነገ የማንለው ተልእኮ ነው ብለዋል።

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍114👏4
፻፴፪ ኛው መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ አዲስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ  ምደባ አካሔደ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

፩. ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ 

፪. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ፤

፫. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐድያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

፬. ብፁዕ አብነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤

፭. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሜኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤

፮. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤

፯. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤

፰. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
😢282👍2