Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በሃገራችንና በዓለማችን ደረጃ የሚዘከርባቸውን መርሐ ግብሮች እናስተዋውቃችሁ፡፡
http://t.me/finotehiwott
17👍4🥰2
ግንቦት 12፤ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም ።
በድጋሚም
ግንቦት 12 ፤ የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ፦።
✤ ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራ ሰይጣንን ልታስታርቅ በሄደች ጊዜ ከሲኦል ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳት ብዙ እልፍ ነፍሳትን ያወጣችበት ዕለት ነው።ራሷ ባነጸችው በጣና ገዳሟ ይከበራል።
--------
፠ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ፤ በፍልሰቴ ቀን በገዳሜ ይገኝ እኔም ልጄ እለዋለው ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጄ ፊልጶስ ጋር እባርከዋለው።›› /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/

፠ አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡

፠ ግንቦት 12 በደብረ ሊባኖስ ትልቁ በዓል ነው፡፡ ጥንተ መሠረቱም፤ 12ቱ እጨጌዎች ከያሉበት ቦታ እየመጡ 1ድ 1ድ ወር ሙሉ በፈረቃ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቅዱስ አጽም ተራ ገብተው ያጥኑ ነበር፡፡ ግንቦት 12 ግን ሁሉም ከያሉበት ተሰባስበው በአንድነት ያከብራሉ፡፡
#የጻድቁ_ዋና_ዋና_የታሪክ_ሂደቶች
፠ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በእቲሣ ተወለዱ፡፡
፠በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡
፠በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡
፠እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብ ዘንድ እየተማሩ
፠በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከቄርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡
፠በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ቄርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡
፠በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡
፠በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ
፠በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡
፠በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡

፠በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡

፠፠፠አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡

፠የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡
#የጻድቁ_ክብረ_በዓላቶቻቸውም
#ኅዳር 24፤ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት
#ታኅሣሥ 24፤ የአባታችን ልደት
#ጥር 24፤ የአባታችን ስባረ አጽም
#መጋቢት 24፤ የአባታችን ጽንሠት
#ግንቦት 12፤ የአባታችን ፍልሰተ አጽም
#ነሐሴ 24፤ የአባታችን በዓለ እረፍት ናቸው፡፡

፠ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤
እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአጽሙ፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
7👍6🙏1
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት በዐቢይ ጾም ሰንበታት በ54 አብያተ ክርስቲያናት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላይ ለተሳተፉና በጎ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት የምስጋና እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠ።

በየክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነቱ በአንደኛነት ከተመሰገኑ አድባራት መካከል ደብራችን #ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ቤተክርስቲያን
በዐብይ ጾም በተዘጋጀው ልዩ ጉባኤ ከ54 አድባራት እና ገዳማት መካከል የላቀ ዝግጅት እና አመርቂ ጉባኤ በማዘጋጀት በአንደኛነት ከተመሰገኑ አድባራት መካከል ተሸላሚ ሆኗል።

ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሀገረ ስብከቱ  የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል አዘጋጅነት በዐቢይ ጾም ሰንበታት የተሰጠውን የወንጌል አገልግሎት  በእጅጉ አድንቀው አገልግሎቱን የመሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍልና የሰባክያነ ወንጌል ኅብረት እንዲሁም እስከ ታች ባለው የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር የተቀመጡትን አገልጋዮች አመስግነዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለው የቤተ ክርስቲያናች መግቢያ  ፣ መኖሪያውና  መድረሻው የሆነው የቅዱስ ወንጌል አግልግሎትን ዓላማውን በተረዳና  ዘመኑን ባነበበ መልኩ መሰጠት እንዳለበት  ለነገ የማንለው ተልእኮ ነው ብለዋል።

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍114👏4