ልደታ ለማርያምና ሥርዐተ ማሕሌት ዘግንቦት ልደታ ለማርያም፡፡
፨ ልደቷ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከሌለ ተቀባይነት እንዴት ይኖረዋል?
፨ የእመቤታችን ታሪክ
፨ እመቤታችን የት ተወለደች?
፨ የልደታ ለማርያም በዓል መቸ ነዉ?
፨ የድንግል ማርያም ልደት ለምን ይከበራል?
፨ የግንቦት ልደታ በዓል አከባበር
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ነበሩና የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች፡፡ ከዛም ፀንሳ በ9 ወሯ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት፡፡ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት፡፡ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፤ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፡፡ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት፡፡ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች::
ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በሥርዓት በቅጣት አደገች፤ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው (መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት:: እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፤ እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ፤ አትናቀኝ፤ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፡፡ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፡፡ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው፡፡
ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት፡፡ ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ፤ የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩ፣ መንግስቱ ናቸው፡፡ ሃናም እኔም አየሁ አለችው፡፡ ምን አየሽ ቢላት፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ ነጭነቷ፤ ንጽህናዋ፣ ቅድስናዋና ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷ ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን፡፡ ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፡፡ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፤ ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሏችኅል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች (በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና)፡፡ እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት:፡፡ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፡፡ አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን፤ እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ፡፡ "እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች፡፡"

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍6❤3
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቷ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ፤ እነሆ በዚህ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው፤ በገነትም በሕይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ "ማርያም" ብለው አወጡላት:: የእመቤታችን ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና:-""ማ"" ማለት ማህደረ መለኮት: ""ር"" ማለት ርግብየ ይቤላ: ""ያ"" ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት:""ም"" ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስትሥራየ ኃጥያት ማለት ነው:: አንድም "ማርያም" ማለት ልዩ ከጣዖት፣ ክብርት እምፍጥረታት፣ ንጽህት እምሃጥያት፣ መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ተፈስሂ ቤተ ይሁዳ ወተሃሠዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው:: አንድም "ማርያም" ማለት መርሕ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ ይህስ እንዴት ነው ቢሉ ፡- እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሷም በጣዕመ ፍቅሯ የሰውን ሁሉ ኃጥያት ክፋት ፍቃ ከልጇ ከወዳጇ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ስለዚህ መርሕ ለመንግስተ ሰማያት አሏት:: አንድም ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው፤ አንድም ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ማለት ነው፤ አንድም ማርያም ማለት ውብህት (ስጥውት) ማለት ነው:: በዚህ በግንቦት አንድ ቀን እመቤታችን አለምን ልታስምር ከቅድስት ሃና እና ከቅዱስ እያቄም በብዙ ልመና ተገኘች:: የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ ጣዕሟ በረከቷ ረድኤቷ አማላጅነቷ በእውነት በኛ በምናምን ልጆቿ ላይ ይደርብን:: ፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
የእመቤታችን በዓላት
በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል››ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ (ዮሐ 10-22) በሐዲስ ኪዳን እዉነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ 111-7
በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሠላሳ ሦስት በዓላት አሏት ፡፡ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘዉ ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡
ልደቷ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከሌለ ተቀባይነት እንዴት ይኖረዋል?
በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› 1ኛ ዜና 29-29
የእመቤታችን ታሪክ
የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ‹‹ሀና››እና ኢያቄም/ዮአኪን በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሀና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሀና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ እርግብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡
ስለ ሃና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡
እመቤታችን የት ተወለደች?
እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሀሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሀሳቦች የሚያነሱ ሲሆን አንደኛዉ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች››የሚል ነዉ፡፡ሁለተኛዉ ሀሳብ ደግሞ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሀና የክሩሲድ ቤተ ክርስቲያን በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡
የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፍንቄ በስተ ምስራቅ ይገኛል፡፡‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ››የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምስጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡መኃ 4-7
የልደታ ለማርያም በዓል መቸ ነዉ?
እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ ና7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅ/ ዮሐንስ፤በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡
የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬ.ክ በመጋገር፡የአመቤታችን ትንሽ ሀዉልት በማቆም ዐስር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡
የድንግል ማርያም ልደት ለምን ይከበራል?
ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል››በማለት ተነግሯል(ሉቃ 1-14)ምክንያቱም ቅ/ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን፡፡ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡
የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ህንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል

❤9👍4
እመቤታችን ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፡በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ህልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡
ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት‹‹መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ›.ብለዉ ተናገሩላት ቅ/ድ/ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ነዉ፡፡(መዝ86-1 ኢሳ 11-1)
በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን!
የግንቦት ልደታ በዓል አከባበር
በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ቡና የሚረጩ፣ቂቤ የሚቀቡ፣የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደዚ ዓይነቶቹ አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ የ እመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ ሐመር 20ኛ ዓመት ቁጥር 1
/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤10👍4
ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን፤
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አስገኘችልን።
እንኳን አደረሳችሁ

❤28👍12🥰1
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ
#፩)#የቅዱስ_ያሬድ_ልደትና_የስሙ_ትርጓሜ
ꔰ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ፤ እንዲሁም አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ /መመህሩ/ ነው ይላሉ፡፡)
ꔰ የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡
፨ አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡
፨ አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤
፨ አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡
-ዐፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በዓፄ ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡
#፪)#የቅዱስ_ያሬድ_አስደናቂ_ነገሮች
#፠ከጌዴዎን ዘንድ ትምህርቱን አቋርጦ ሄደ ስንል፤ በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ በትል አማካይነት ትዕግስትንና ማስተዋልን ቀስሞ፤ ወደ አጎቱ ተመልሶ ተምሮና ትምህርትን አምላክ ገልጾለት መምህረ መምህራን ሁኖ እንገኘዋለን፤ /እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱስ ያሬድ ያንን ኹሉ ጥበብ ቶሎ ያልገለጸለት በቀላሉ ቢያገኘው ኋላ እንዳይታበይ ብሎ ነው፤ የሐዊራ ብስድር እስክንድራን ታሪክ ልብ ይሏል)
#፠መምህር ነው ስንል፤ መናኝ ባሕታዊ ኾኖ እናገኘዋለን፤ /በደብረ ሐዊ ለ22ዓመታት መመኑን ልብ ይሏል/
#፠መናኝ ነው ስንል የተለያዩ የሃገራችንን ክፍሎች ገዳማትና አድባራት ሲጎበኝ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሲጓዝ እንገኘዋለን፤ /ጣና ቂርቆስ፤ ዙር አባ አቡነ አረጋዊ፣ …. ሌላውንም ልብ ይሏል)
#፠ወደ ገዳማትና አድባራት ይጓዛል ስንል፤ ወደ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ በደመና ተጭኖ ሂዶ ምሽቱን ወደ በዓቱ ሲመለስ እንገኘዋለን፡፡
#፠በሃገራችን በዋና ከተማ አኵሱም ተወልዶ ያደገ ነው ስንል፤ ሰው ሊኖርበት በማይችለው፥ በረድ በሚፈላበት፥ የነፋስ እሩምታ በሚያይልበት፥ ቅዝቃዜው አጥንት በሚሰነጥቅበት፥ ውርጩ እጅጉን በሚቀዘቅዝበት፥ ደመና በሚፈስስበት በራስ ደጀን ተራራ አጠገብ በደብረ ሐዊ መንኖ እናገኘዋለን፡፡
#፠ከሰዎች ጋር አብሮ ኑሯል ስንል፤ ከሰው የማይቀርቡና በዐለማችን ላይ ብርቅዬ ኾነው በሃገራችን የሚገኙ ከሃገራችን ኢትዮጵያም በሰሜን ተራሮች በአብዛኛው ከሚገኙት ዋልያ ጋር አብሮ ሲኖር፤ ዋልያዎችንም እንደ መጓጓዣና እንደ መጫኛ ሲያገለግሉት እንገኛለን፡፡
#፠በሙራደ ቃል የመላእክት ዜማ ተገልጾለት ተማረ ስንል፤ የግእዝ ቋንቋ ምሁርና ጠበብት ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ለተሰዓቱ ቅዱሳን መምህር መሆኑን ልብ ይሏል)
#፠የዜማ ጀማሪ አባት ነው ስንል ባለቅኔ ኾኖ እንገኘዋለን (ሕንፄሃ ወሡራሬሃ …. የሚለው ቅኔውን ልብ ይሏል)፤
#፠ባለቅኔ ነው ስንል መተርጕም ኾኖ እንገኘዋለን፤ (ድጓው የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መሆኑን ልብ ይሏል)
#፠መተርጕም ነው ስንል ባለታሪክ፥ የታሪክ ምሁር ኹኖ እናገኘዋለን፤
#፠የታሪክ ምሁር ነው ስንል፤ የመርሐ አዝማን ሊቅ ኹኖ እናገኘዋለን፤ (ዓመቱን በሚገርም ሁኔታ ከወቅታቱ ጋራ አገናዝቦ መሠየሙን ልብ ይሏል)
#፠የመርሐ አዝማን ሊቅ ነው ስንል ቅዱስ ኾኖ እንገኘዋለን፤ የቅዱሳንም ጓደኛ ኹኖ እንገኘዋለን፡፡ /የአቡነ አረጋዊ፣ የአጼ ገብረ መስቀልን ታሪክ ልብ ይሏል፡፡/
#፠ነቢይ ነው ሰንል ሐዋርያ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ስለ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትና …. ሌሎችንም ልብ ይሏል)
#፠ሐዋርያ ነው ስንል ሰማዕት ኹኖ እናገኘዋለን፡፡ (እግሩን በጦር መወጋቱን ልብ ይሏል)፤ ሌላም ሌላም ….
፠#፠በአጠቃላይ ምድራዊ ነው ስንል ሰማያዊ፤ ሰማያዊ ነው ስንል ምድራዊ (ብእሲ ሰማያዊ ወመልአክ ምድራዊ) ሁኖ እናገኘዋለን፡፡
#ዜማውን በግዕዝ ዕዝል አራራይ የዜማ ስልት የደረሰ፤
#በዓለም ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ፤
#የዜማ ሥርዓትን በመንደፍ የዓመቱን ቀለም ያዘጋጀ፤
#ዜማውን በ4ት ዘመናት ከፋፍሎ፤ ዘመናቱን በንዑሳን ዘመናት ከፋፍሎ ለወራቱና ለሰሙኑ ለእለቱ የሚገባውን ቀምሮ የደረሰ፤
#እንኳን በእርሱ ዘመን ዛሬ እንኳን ብዙ ነገሮች ተሰባስበዋል በተባለበት ዘመን ሊሠራ አይደለም ሊታሠብ በማይችሉ መልኩ መጽሕፍትን እንደ ንብ እየቀሰመ፤ እንደ ወይን እየጨመቀ፤ እንደ አረቂ እያጣራ፤ እየተረጐመ ላሰበው ድርሠት ያዋለ፤ … ስለ ቅዱሱ ምኑን ተናግረን እንጨርሰዋለን፡፡ …
##.. ይኼማ ኢትዮጵያዊ ሊኾን አይችልም ብለው ብዙ የውጭ ሃገራት ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚዳዳቸው፡፡
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/
#፫#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤
#1ኛ) ምዕራፍ (ውዳሴ ማርያም በዜማን፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠለስት፣ ክስተተ አርያምን) ያጠቃልላል፡፡
፠የውዳሴ ማርያም ዜማ ቅዱስ ኤፍሬም ሦርያዊ የደረሰውን ለቅዱስ ያሬድ እየነገረው ልብን የሚመስጥ ዜማ ደርሶለታል፡፡
፠መስተጋብዕ፤ ስብስብ ማለት ሲኾን፡፡ ከዳዊት መዝሙር (ከ180ው የመስተጋብእ ድርሰት 1ድ ድርሰት በስተቀር) ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የኾነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የኾነው የተቀመረ ነው፡፡ መስተጋብዕ ሲጀምር ‹‹ወለቡ ጽራኅየ (ጩኸቴን ልብ አድርግ›› ብሎ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ጠዋት ይዘመራል፤ የቀድሞ መምህራን በፍልሠታም ይዘምሩት ነበር፤ ዜማው በዋነኛነት በግዕዝና በዕዝል ሲኾን በአራራይ ከሐሙስ ‹‹አንተሰ እግዚኦ ለዓለም›› የሚለውና ከቅማዴ ‹‹መንግሠትከሰ መንግሥት›› የሚለው ይገኙበታል፡፡ በየእለቱ እንዲደርስ (ከእሑድ በስተቀር) አድርጎ የደረሰው ነው፤
፠አርባዕት፤ አራት አራተኛ ማለት ሲን በዳዊት መዝሙር በአራተኛው መሥመር ውስጥ እየገባ የሚዘመር ነው፤ ‹‹ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራኅየ፤ ወአጽምአኒ ቃለ ስእለትየ፤ ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ፡፡ ከፈጸመ በኋላ አርባዕት ይገባል፡፡ አርባዕት ሲጀመር ‹‹ቃልየ፤ ከመ ያፈቅርለ ጐሥዓ፤ ዐቢይ፤ ተሣሃለኒ›› ብሎ ነው (በዳዊት መዝሙር ጀምሮ ቀጥሎ በቅዱስ ያሬድ ድርሠት በኾነው በአርባዕት ያጠናቅቃል፡፡አብዛኛው በግጥም መልክ የተቀመረ ሲኾን አልፎ አልፎም በስድ ንባብ መልክ ይገኛል፡፡ ግእዝ ዕዝልና አራራይ ዜማ አለው፡፡ አርያም፤ አርያም ልዑል፥ ከፍተኛ ማለት ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ሰምቶ ‹‹ቀዳሚ ዜማ፤ አንድም ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ስላመጣው ነው፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ የግጥም መል ባለው አእያም በተባለው ይጀምራል፡፡ በግጥም መልክና በስድ ንባብ ሲገኝ የግጠም አገጣጠሙ ከፍ ያለ የግጥም አገጣጠምን የተከተለነው፡፡ የሚባልበት ጊዜ በጾም ጊዜ በጾመ ድጓው እየገባ፣ በተለይ ደግሞ በክብረ በዓል ክሥተተ አርያም ሲደርስ ይዘመራል፡፡

👍6❤5🤝1
ሠለስት፤ ስምዐኒ ብሎ የሚጀምር ባለ ብዙ ሃሌታ ያለው፤ በዳዊት መዝሙር በሦስተኛው መሥመር እየገባ የሚዘመር፤ አንድም 3 መዝሙሮች ብቻ የሚዘመሩለት ብዙውን ጊዜ በግጥም የሚቀርብ ሲኾን፤ ይኽ ዜማ የሚደርሰው በክብረ በዓላት ዋይዜማ፤ በስብሐተ ነግህ፣ በአርያም፣ በጾመ ድጓ ውሎ፣ በአርያም፣ በሰንበት፣ በፍትሐት ጊዜ ነው፡፡
ክስተተ አርያም፤ የሰማይ መከፈት ማለት ሲኾን በታላላቅ በዓል ቀን እንዲሁም ታላላቅ? ሰዎች ሲሞቱ የሚዘመር ነው፤ ክስተትን ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጀው ከዳዊት መዝሙራት፥ ከጸሎተ ነቢያትና ከራሱም ጭምር ኀይለ ቃል ያላቸውን ባለሁለት መስመሮች ሐረግ በመውሰድ ሲኾን ዜማው እጅጉን ነፍስና ሥጋን፥ ልብንና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡
2ኛ) ጾመ ድጓ፤ በዐቢይ ጾም የሚባል ነው፡፡
3ኛ) ድጓ፤ በ4ት ክፍላተ ዘመናት የተቀመረ ነው፡፡
4ኛ) ዝማሬ፤ ቅዱስ ቊርባን ድርገት ሲወርድ ለቅዱስ ቊርባን ክብር የሚዘመር ነው፡፡
5ኛ) መዋሥዕት፤ ሰው ሥጋው ከነፍ ስትለይ ፍትሐት የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡
6ኛ) የ14ቱን ቅዳሴያት ዜማ፤ 14ቱን ቅዳሴያት 14ት አባቶች የደረሷቸው ቢሆንም ዜማ የደረሰላቸው ግን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
7ኛ) አንቀጸ ብርሃንን፤ ድርሰቱ ነው፡፡ /ይቀጥላል……/
በተጨማሪም ደግሞ፤
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ዐይነቶች ግእዝ፣ ዕዝልና ዓራራይ በመባል ይታወቃል፡፡እነዚህ የዜማ ዐይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛው ድምፅ ያልተደባለቀ፣ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ትርጉም ያላቸው
በሆኑ የዜማ ምልክቶች (ድፋት፤ ሂደት፤ ቅናት፤ ይዘት፤ ቁርጥ፤ ጭረት፤ ርክርክና ደረት) ደርሷል፡፡
የቅኔ ጀማሪም ነው፡፡ ‹‹ሕንፄሃ …›› የሚለውን ቤት መምቻ ያለውን ቅኔ ልብ ይሏል፤ አንድ ባለቅኔ ግን ይህን ሳይረዳ ‹‹ተትሕተ ያሬድ …›› የሚል ቅኔን ተቀኝቷል፡፡
#፬#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤#የዜማው_ይዘት_የዜማው_ጠባያት_ከሌሎች_ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይና_የዜማው_ጥቅም
#ሀ_የቅዱስ_ያሬድ_የዜማው_ይዘት
፠ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀው ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንት መጻሕፍት እየመረጠ ለምስጋናና ለጸሎት እንዲኾኑ አድርጎ ነው፡፡
፠ዜማው ምስጢሩ የማይጠገብ፥ቃሉ የሚያረካ፥ አነጋገሩ የተሳካ፥ ጣዕመ ቃሉና ኀይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ፥ ልብን የሚነካ ነው፡፡
፠በይዘቱም የሥነ ፍጥረት ውበትን በማድነቅና የሥነ ፍጥረት አስገኝ የኾነውን እግዚአብሔርን በማመስገን ላይ ያተኮረ ነው፡፡
፠በአጠቃላይ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ጌታ ለሰው ልጆች ሲል በዚህ ዓለም የፈጸመውን የማዳን ሥራ ሁሉ ገልጦ የሚያስረዳ ነው፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳን መላእክትን፣ የነቢያትን፣ የሐዋርያትን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ክብርና ቅድስና በማውሳት በስማቸው መማፀንና መጸለይ የሚያስገኘውን ጥቅም የሚያስረዳ ታላቅ ዜማዊ ሀብት ነው፡፡
፠ከእርሱ በፊት የነበሩና በእርሱ ዘመን የተጻፉ የቅዱሳን ገድላትና ድርሳናትን እንዲሁም የበዓላትን ጥንታዊ አመሠራረት ውስጠ ምሥጢር በማስረዳት በዜማ ድርሰቱ አካቷል፡፡
፠ምስጋናውንም ለአራቱ ክፍላተ ዘመን ለክረምት፣ ለመፀው (ለጥቢ)፣ ለሐጋይ (ለበጋ)፣ ለጸደይ (ለበልግ) እንዲኾን አዘጋጅቶታል፡፡
#ለ_የዜማው_ጠባያት
፨የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ በመኾኑ ኅሊናን የመመሠጥ፣ ሥጋዊ ደስታንና ኀጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ፣ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምስጢር የማሳወቅ ኀይል አለው፡፡
፨ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታም በመኾኑ ብልየት (እርጅና)፣ ውላጤ (መለወጥ) የማይታይበት ዘወትር ሕያው የኾነ ብቸኛ ዜማ ነው፡፡
፨የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም በመኾኑ ዘወትር አዲስና የማያልቅ ጥልቅ ምንጭ ያለው ሕይወትን የሚያለመልም ነው፡፡
፨ዜማውም ሰማያዊና መንፈሳዊ፣ ከእግዚአብሔር የተገኘ ለመኾኑ ማስረጃ የሚኾነን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች ዜማውን ለተለያየ ዐላማ ይመኙታል፤ ነገር ግን ለመያዝም ኾነ ለመወሰን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በምድራዊ ጥበብና ፍልስፍና የሚያዝ የሚወሰን ሳይኾን ታላቅ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ፣ ሌት ተቀን ልቡናን ለሥላሴ ሰጥተው ከእግዚአብሔር የሚያገኙት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያጸኑት፣ የሚማሩትና የሚያዜሙት እንጂ በገንዘብ የማይገዛ ታላቅ ጸጋ መኾኑ ነው፡፡
#ሐ.#የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ከሌሎች _ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይ፤
፨ ዜማው አሳብን የሚገዛ፣ ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር በመኾኑ፤
፨ በአቀራረቡም የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው በመኾኑ፤
፨ ዜማው በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም መኾኑ፤
፨ ማንኛውም ሰው ከተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ውጪ በራሱ ፍላጎት የድምፅ ቅላጼውን ለማሳመር ስለፈለገ የሚያሻሽለው ወይም የሚለውጠው አለመኾኑ፤
፨ ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መኾኑና
፨ የዜማው ምልክቶችና ዐይነቶች ጥልቅ ምሳሌና ምስጢር ያላቸው መኾናቸው ነው፡፡
#መ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ጥቅም
ሀ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በመጠበቅ፤ በየትኛውም አካባቢ የምትኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዐይነት ሥርዐት በአንድ ዓይነት ጊዜ በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡
ለ. በነገረ መለኮት ትምህርት፤ ሊቁ የትርጓሜ መምህር ስለሆነ ከብዙ መጻሕፍት ስለሚጠቅስና የሃይማኖት ትምህርቱትንም በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ ትምህርት እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡
መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

👍4❤2