Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
✞ የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

፨ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ሐዋርያ አልነበረም ኋላ ከሔደበት ሲመጣ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት እኔ ሳላይ አላምንም በማለቱ በዚህ ጥያቄው መሠረት በሳምንቱ ጌታችን በድጋሚ ስለተገለጸ ለዚህ መገለጹ መታሰቢያ ሆና ዕለቲቱ «በቶማስ» ተብላ ተሰየመች፡፡ ዮሐ. 20-24-30

፨ ጥንተ ቶማስ  ሚያዝያ አንድ ነው ይህም ጌታ በተሰቀለ 4 ኛው ቀን በተንሣኤው ደግሞ 2ኛ ቀን ነች፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍163🥰3
✞   የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው    #ረቡዕ#አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አላዓዛር መታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየት በጌታችን ብዙ ሕዝብ ስለአመነበት ቀኒቱ «አላዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡ ዮሐ. 11-38-46

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍142
የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው  #ሐሙስ#አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ የአዳም ተስፋው ተፈጽሞለት ከነልጅ ልጆቹ ወደቀደመ የገነት ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ሆና «የአዳም ሐሙስ» ተብላ ይኸው ትከበራለች፡፡ ሉቃ. 24-25-49

በአዲስ አበባ የሚነግሥበት ብቸኛው በስሙ የተሰየመ የአቡነ አዳም ወሔዋን ቤተ ክርስቲያን

፨> ለቡ መርጡለ አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤ/ክ
አድራሻ፦ ከፒያሳ - ሜክሲኮ - ለቡ ጋርመንት መብራት ኀይል

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
1
/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
7👍3
ድንግል ማርያም ሆይ በሚጣፍጠው ስምሽ ደስ ይለናል፤ ጥዑም በሆነው በማኅፀንሽ ፍሬ በክርስቶስ ደምም ሐሴትን እናደርጋለን፤ ፅንዕት ክብርት ንጽሕት ልዩ እመቤታችን ሆይ አንቺ የዓለም ሁሉ ቤዛ ነሽ!!!

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
40👍3👏2🥰1
✞  የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው #ዓርብ#ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዓርብ «ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡  ማቴ. 26 ÷ 26-29 ሐዋ 20-28

በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
22👍9
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በስተቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበይባት «የቁራ ገበያ» የገበያ ጥፊያ ስትባል በቤተ ክርስቲያን ግን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጉልበታቸው ለአገለገሉት በስቅለቱ ዋይ ዋይ እያሉ እስከ ቀራንዮ ለተከተሉት፣ የትንሣኤው ዕለት ገና ከሌሊቱ ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው በመገሥገሣቸው ትንሣኤው ከሁሉ ቀድሞ ለተገለጸላቸው ቅዱሳት አእንስት መልካም መታሰቢያ ሆና «አእንስት» ተብላ ትጠራለች፡፡ ሉቃ. 23-27-33፣ 24-1-01፣ ማቴ. 25-1-11

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
25👍3
✞ እሑድ- ዳግማይ ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ዳግም ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

+ + + መልካም በዓል!!! + + +

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍175
#ሚያዝያ_23_በዓለ_ክላሌሁ_ለሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ፡፡
ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡
#ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ በዕረፍቱ ክርስቶስን የሰበከ፥ ከዕረፍቱ በኋላ ዛሬን ጨምሮ ፈትኖ የሚራዳ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤
#....
የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በዓለ ክላሌ (ሚያዝያ 23) ከዋይዜማው ጀምሮ በመላው ሃገራችን የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡
#አማን በአማን፥ አማን በአማን፤
ኮከበ ልዳ፥ ፀሐየ ፋርስ፡፡
#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤
ዘአንበሩ ብየ አክሊለ ሞገስ፤
መዘምረ እኩን ለጊዮርጊስ፡፡

#ኀያል መስተጋድል
ኀያል ኮከበ ክብር፤
ኀያል ገባሬ ተአምር፤
ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር፡፡

#በእንተ ጊዮርጊስ ፍቁርከ(ሰማዕትከ፥ ምዕመንከ)፤
ምህላነ ስማዕ በዕዝንከ፡፡

#ሥርዐተ ማኅሌቱን ሌሎችም እንዲደርሳቸው ከዚህ በታች የሰፈረውን ገጻችንን LIKE LIKE እንዲያደርጉ ያስተዋውቁ፤ INVITE INVITE INVITE ያድርጉ፡፡

👍115