Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ነዳያንን በማስፈሰክ የ56 የዓመታት አገልግሎት ጕዞ፡፡
በአዲስ አበባና በሃገራችን ላሉ ሌሎች ሰንበት ትምህርት ቤቶች ፋና ወጊ የኾነ አገልግሎት፡፡ ወንድማችንና አባታችን አርቲስት ችሮታው በዚህ አገልግሎት ላይ ግንባር ቀደምት ናቸው፡፡
ነዳንንና አቅመ ደካሞችን በትንሣኤ በዓል ላይ አብሮ መፈሰክ ከዛሬ 56 ዓመታት በፊት በ1961 ዓ.ም በትንሽ ነገር ተጀምሮ ዘንድሮም ነዳያንን በደብራችን ምርፋቅ ቤት (ሰንበቴ ቤት /ደጀ ሰላም/)፣ በጸበል ቦታ ያሉትን፣ በገዳም ውስጥ ያሉትን መነኰሳትና የአብነት ተማሪዎች ሰለምናስፈስክ፤ ለመርዳት የሚያስፈልጉትን በየቤታችሁ እንጀራና የወጥ መሥሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ለመሰብሰብ ለሚመጡ አባላቶቻችን እንደተለመደው አዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ እንዲሁም (ገንዘብ፣ ልብስ፥ ሳሙና፥ ንጽሕና መጠበቂያ፣ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፣ የተማሪዎች የመማሪያ ቊሳቊሶችን) ሰ/ት/ቤታችን ድረስ በመምጣት አስተዋጽዖ እንድታደርጉ በመድኀኔዓለም ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል፡፡›› መዝ. 40፥1

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍71
#ሥርዓተ_ጸሎተ_ሐሙስ_ወሕጽበተ_እግር

ሐዋርያቲሁ ከበበ፥
እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤
ኮኖሙ አበ ወእመ፤
ወመሐሮሙ ጥበበ፡፡

(ሐዋርያቱን ሾመ፤
የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤
አባትና እናት ኾናቸው፤
ጥበብንም አስተማራቸው፡፡)
/ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍9🥰21