Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በኢትዮጵያ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርበት ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡

የሕማማትህንና የሞትህን ዜና ስለሰማች ዋልድባ ቅድስት ከዓመት እስከ ዓመት ታለቅሳለች፤
ፈጣሪዋ አምላኳ ስለሆንክ፥ በስደትህ ጊዜ የባረካትና የመሠረትሃት፥ ኋላም እንደ ተሰቀልክ ሆነህ የተገለጽክባትና የቀደስካት በመሆኗ ዓመት እስከ ዓመት በሱባዔ ታስብሃለች፡፡
መጋቢት 27 ግን እንባዋን በቅዳሴ ጭምር የምታብስበት የደስታዋ ቀን ነው፤
ሰብዐ ዓለም ወሰብአ ኢትዮጵያ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ተሰብስበው በኢትዮጵያ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓልህን ያስባሉ፤ ማዕከላዊና ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዋልድባ ገዳም በመራቃቸው ብዙሃን ሕዝብ ለክብረ በዓሉ ወደ ዋልድባ ባይሄድም፤ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በተለይም ከጎንደርና ከትግራይ የ7 ዓመት ሕፃናት ሳይቀር ያን በረሐ አቋርጠው ወደ ገዳሙ ይተማሉ ፤ መነኰሳቱም እንደ አሸን ለበዓሉ የሚመጣውን ምዕመን በቋርፍና በጭልቃ፣ በሰሊጥና በሻይ ይቀበሉታል፡፡ ቅዳሴው እንዳበቃም ነፋስ እንደበተነው አሸዋ ባንዴ ሕዝቡ ወደ መንደሩ ይተምማል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍16🥰53
እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡
*ከዋይዜማ እስከ ማኅሌት፤
*ከሰዐታት እስከ ኪዳን፤
*ከቅዳሴ እስከ ዑደተ ታቦተ ሕግ፤
*ከጠዋት የስብከት ጕባኤ እስከ ሠርክ ጕባኤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የመድኅነ ዓለም ቤተ ከርስቲያን ተገኝታችሁ እንድታከብሩ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ሥርዐተ ማኅሌት በግእዝና በአማርኛ ትርጕሙን ጭምር አቅርበንላችኋል፡፡
(በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ብቻ የሚቆሙትንም ቀለማት ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም ብለን አካተን አስቀምጠናቸዋል፡፡)

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
8👍2