Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በዓለ ትንሣኤን ነዳያንን በመርዳት በረከት እናግኝ

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍11
ገብርኄር፤ ስድስተኛው ሳምንት

#ገብር ኄር፥ ገብር ምዕመን ፥ ገብር ሀካይ
ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ስለ ስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኄር /ስለታማኝ/ አገልጋይ ያስተማረውን ትምህርት ይነገራል ይህንንም የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ይኸውም ማቴ 25፥14-30 ላይ ይገኛል፡፡ (ይህም ክፍል ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል በምሳሌ ካስተማራቸው ትምህርቶች አንዱ ነው)፡፡
ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፡ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ፡፡ መክሊት የወርቅ መለኪያ /መስፈሪያ/ ነው፡፡ አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ ፡፡ አንድ ተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡
ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቈጣጠራቸው፡፡
*አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክ፤ ‹‹ ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት›› አለ፡፡ ጌታውም፦ ‹‹መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ኄር)፤ በጥቂቱ ታምነሃል በቡዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፡፡›› አለው፡፡
*ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፡፡›› አለ፡፡ ጌታውም፡፡ መልካም፡ ‹‹ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ (ገብር ምዕመን) በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡
*አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ካልዘራህባት የምታጭድ፥ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ሌቦች እንዳይሠርቁኝ አታላዮች እንዳይቀሙኝ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ መክሊትህ እነሆ›› አለው፡፡ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- ‹‹አንተ ክፋና ሃኬተኛ ባሪያ (ገብር ሀካይ) ካልዘራሁበት እንደማጭድ ፥ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር መክሊትም ላለው ስጡት፤ እሱን ደግሞ ወደ ዘለዓለም ሐዘንና መከራ ወዳለብት ወደ ጨለማው አውጥታችሁ ጣሉት›› አላቸው፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወስድበታል፡፡  አገልጋዮችም ይህንን ክፉ አገልጋይ ወደ ጨለማው አውጥተው ጣሉት፡፡ በዚህ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
† መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን፤ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ተሰጥቶናል በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡
† በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፤ የሰማነውን ቃለ እግዚአብሔር ለመተግበር እየበረታን ለሌላው ማሰማት ይገባናል፤ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፤ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚያሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ እኛም በሃይማኖት ጠንክረን በምግባር በርትተን ታማኝ ባርያ ልንሆን ይገባል፡፡
፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍115😢1
🩸 የደም ልገሳ መርሐግብር 🩸
                                          
"ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰውን ሕይወት እንታደግ!"

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
13👍2
በዓለ ንግሥ እና የጉባኤ መርሐግብር

📅 ከመጋቢት 25 - 28 ከ10 ሰዓት ጀምሮ
በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለምና ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያን

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
17👍5
/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍3
፨ የምንናፍቀው ቀን ደረሰ ፨

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
18👍6
እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡

#ጥንተ_ስቀለት
#ክርስቶስ_የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን #ከሆነ _እንደገና_በሌላ_ጊዜ_በዓለ_ስቅለትን_ማክበር_ለምን_አስፈለገ?

      #ጥንተ_ስቀለት
የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ፳፯ ቀን ሰማያዊ አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ ሕማማተ መስቀልን በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው #በገዛ_ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ #በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከበራል ፡፡ የመጋቢት ጽንሰት ( ብሥራት ) ታሕሣስ 22  እንደሚከብረሁ ሁሉ ማለት ነው ፡፡

   ፠#ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ከሆነ እንደገና በሌላ ጊዜ በዓለ ስቅለትን ማክበር ለምን አስፈለገ?
  ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ ሲሆን ከመቃብር የተነሣውም በዕለተ እሑድ በመሆኑ #ስቅለት ከዕለተ ዓርብ፣ #ትንሣኤም  ከዕለተ እሑድ፣ #ዕርገት ደግሞ ከዕለተ ሐሙስ እንዳይወጡ፤ ሌሎቹም በዓላትና አጽዋማት በተወሰነላቸው ቀን እንዲውሉ ማድረግ ይቻል ዘንድ የቀድሞ አባቶችና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሰባት አዕዋዳት አዘጋጅተው እና ቀምረው ሁሉም ሥርዓቱን ጠብቆ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቀን እንዲከበር የወሰኑ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ይፈጻማል::

   #ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን #የጽንሰቱ_በዓል በታላቅ ድምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑ የተነሣ በዓሉን በዓል ተጭኖት ነው እንጂ ፫ኛው ቀን መጋቢት ፳፱ኝም ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት #ጥንተ_ትንሣኤ በመሆኑ እንደ ጥንተ ስቅለቱ ሁሉ ጥንተ ትንሣኤውም ከበዓለ ጽንሰቱ ጋር አብሮ የሚታሰብ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡

#በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤
  
✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤ ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ.
✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም
✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም
✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና
✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ
✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ
✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (ቦሌ የመድኀኔዓለም ታቦት )
✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም
✤9.#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም   ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 110 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡  ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)

10 #መናገሻ_ጋራ_መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡

11.  #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡

12.  #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)

#በዓለም አቀፍ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርባችው ፪ቱ ታላላቅ ገዳማት

፩ኛ. ኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍32
የመጀመሪያ ቀን የጉባኤ ማስታወሻ

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍4