* በሠርፀ ድንግል የተሠራው ቤ/ክ ራሳቸውን አንሳር(አሸናፊዎች) በሚሉና የሱፊ እስልምና ተከታይ በሆኑት የሱዳን መሐዲስት ደርቡሾች በተደጋጋሚ 3ት ጊዜ ጥፋትን አደረሱበት፤ እነዚሁም
-ከ1659-1674ዓ.ም. የመጀመሪያው ጥፋት፤
-በዐፄ ቴዎድሮስና በዐፄ ዮሐንስና ዘመን /በጥር 27 1877ዓ.ም. የጎንደርና የደምቢያውን ዘገረ ገዢ ዳኅና ፈንታን ገደሉ ገዳሙን አቃጠሉ፥ መነኰሳቱን ፈጁ/
-በ1880ዓ.ም. ጎንደር አካባቢ ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት አቃጠሉ
-ጥር 10 1880ዓ.ም. ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተዋጉ፤ ልጃቸው ምንትዋብ ተማረከች አልሰልምም ብላ በረሃብ ሞተች፤ ባለቤቷ ደጃች ጀምበሬ ሞቱ፡፡
-ነሐሴ 23 1880ዓ.ም. ጎንደር ገብተው ከ44ቱ ደብራት 40ውን አቃጠሉ፤
-መስከረም 25 1881ዓ.ም. ጎንደርን አቃጠሉ፤ ቀሪዎቹን 3ት ደብራት ሠለስቱ ምዕትን ግምጃ ቤት ማርያምን አቃጠሉ፤ የግምጃ ቤት 9ኝ የመጻሕፍት መምህራንን (ዛሬ የምንገለገልበትን አንድምታ ከመምህር ኤስድሮስ በኋላ ያቀኑትን እነ መምህር ወልደ ሚካኤልን) በቤተክርስቲያኑ መውጫ በርላይ ከነተማሪዎቻቸው ሰየፏቸው፡፡ ጩጊ ማርያምንም አቃጠሉ፡፡ ….. ዐፄ ዮሐንስ እየመጡ መኾኑን ሲሰሙ ወደ መተማ ሸሹ፡፡
**ዐፄ ዮሐንስም ወደ ማኅበረ ሥላሴ በመግባት ገዳማውያኑን በማጽናናት፤ የብራና ተዓምረ ማርያምና ሌላም መብዓ በመስጠት በየካቲት 27/1881ዓ.ም ወደ መተማ ወርደው ተዋጉ፤ በውጊያው ግን ንጉሣችን ተመትተው ቆሰሉ፤ ጦሩም ንጉሡን ይዞ ወደ ማጠቢያ (ጻድቁ ልብስ ያጠቡበት በመሆኑ ይህን ስም አግኝቷል) ሸሸ፤ ጠላት ኃይሉን አጠናክሮ በመጋቢት 3/1881ዓ.ም. ደርሶ ንጉሣችንን ገደለ፤ ንጉሣችንን አናስነካም ያሉ በርካታ ካህናትና ምዕመናንም በሰማዕትነት አለፉ፡፡
**ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ /1929-1922ዓ.ም./ የተቃጠለውን ቤ.ክ. አሳነፁ፥ የውኃ ታንከር ከምድር በታች አስቆፍረው በደንጊያና በኖሩ አሠሩ፡፡ ከ8ት ዓመታት በኋላ ከሚያዝያ 13-15/ 1928ዓ.ም. ግን ጠላት ጣሊያን በጦር አውሮፕላን ሁኖ ገዳሙንና የውኃ ገንዳውን በቦንብ ደበደበ፥ 28 መነኰሳትንም ፈጀ (የቦንቡ ቀለሃ አሁንም በገዳሙ ወፍጮ ቤት ይገኛል)፡፡ ነገር ግን አውሮፕላኖቹ ጥቃቱን አድርሰው ሲመለሱ በአበው ጸሎት፥ በጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ተዓምር አድራጊነት 2ቱን አውሮፕላኖች አንዱን ዋለንታ ላይ፤ ሁለተኛውን ማርዘነብ ላይ ከስክሰዋቸዋል፤ ስብርሪያቸው አሁንም ድረስ አለ፡፡
/#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

👍1
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

👍6

❤8🙏5👍1
ምኵራብ፤
ሦስተኛ ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡
በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡
በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡
በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡
በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡
በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡
፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16
፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52
፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1
፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍7❤3
፨ መንፈሳዊ ጉዞ ፨
ወደ ደብረ ከርቤ ዳግማዊ ጎልጎታ ገዳም
መጋቢት 07/ 2017 ዓ.ም
ትኬት ለማግኘት እንዲሁም ለበለጠ መረጃ
0941495975 / 0924866375 / 0911087991

🥰5👍2
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡
እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓለ_ዕረፍት_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ ላሊበላ፥ ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)
፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/
( ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ተመልሰው ወደ ምድረ ከብድ በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፤ በግብፅ 300ዓመታት፥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ 262ዓመታት (በዋነኛነት በምድረ ከብድና በዝቋላ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን ገዘዛ አቦን መጥቀስ ይቻላል) ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባትም ምድረ ከብድ ገዳም ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከባድ/ ትብለሽ ተጠሪ አላት የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡
አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡
(ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡)

👍9🙏2