Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
፨ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡

፨ ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤

፨የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ #መናገሻ_ገነተ_ጽጌ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍3👌1
መዝሙር ዘቅድስት

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
🙏9👍41
ቅድስት፤ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡

‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡

ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡

፨ የዕለተ ሰንበት ክብር፤
በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8
በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡
ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡

  ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡

   ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና››
  ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍11
፨ ቅዱስነትዎ እንኳን አደረስዎ ፨

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
31👍9
#ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳምና_ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ

፨ ታቦቱ_ሥላሴ፥ ፨ ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ፥
፨ የገዳሙ ስም ማኅበረ ሥላሴ፡፡
፨ በየቀኑ በሁሉም ቤክ በቅዳሴ ላይ ስሙ የሚነሳው ገናናው ገዳም (ብዙዎች ግን የማያውቁት)፡፡
፨ እንኳን ሰዉ ከብቱ ሥርዐት ያለው ድንቅናዕፁብ ገዳም፡፡
፨ ገዳሙን ያጠፉ አውሮፕላኖችን በጸሎት የከሰከሱ አባቶች የሚገኙበት የበርካታ ትምህቶችና የጥበብ ማዕክል፤ …. ኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢያንስ አንዴ ሊያዩት የሚገባ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ገዳም!!!፡፡

፨ በዚህች በየካቲት 27 እለት ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወመነኰሳት (ለአቡነ ክፍለ ማርያም፥ ለአቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘቋራ፥ ለ፯ቱ ዘሥላሴ በመባል ለሚጠሩ ቅዱሳን፣ ለዐርከ ሥሉስ /የአርኬና የመልክአ ቊርባን ደራሲ/፤ ….) የኾኑትና ፤ ጽድቃቸውና ቃልኪዳናቸው እንደ ምድር አሸዋ የበዛው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት ለመቊጠር የሚያስቸግረው ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ ልደታቸውም እረፍታቸውም ነው፡፡

- እኒህ ጻድቅ የተወለዱት በጎጃም(ሸዋም የሚሉ አሉ) ሲኾን፤ የተወለዱትም ሆነ 104ዓመታት ከኖሩ በኋላ ያረፉበት ቀን በመድኀኔ ዓለም ወርኀዊ በዓል በየካቲት 27 ነው፡፡
- ጻድቁ በተለያዩ ገዳማት በአርድእትነትና ሥርዐተ አበው በማጥናትና በመተግበር ከቆዩ በኋላ፤ ምንኩስናን ከአቡነ ተንሥአ ክርስቶስ ዘትግራይ ተቀብለዋል፤ ኋላም ወደ ታላቁ ገዳም ገዳመ ዋሊ (ገዳመ ዋልድባ) ገብተው ከቆዩ በኋላ ወደ ገዳመ አስቄጥስ በመሄድ ለ18 ዓመታት ከቆዩ በኋላ በስተመጨረሻ ምናኔያቸውን በማኅበረ ሥላሴ አድርገዋል፡፡

* በ1616ዓ.ም. ሱስንዮስ 8,000 ክርስቲያኖችን የካቶሊክን ካልተቀበላችሁ ብሎ ጠዳ ላይ በሰየፈ ጊዜ ሳይፈሩና ሳይፍሩ ለሃይማኖታቸው ከተከራከሩና ጠበቃ ከኾኑት መካከል ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ (ሌሎችም ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ እኅተ ጴጥሮስ፣ ፍቅርተ ጴጥሮስ፣ ሐራ ድንግል ምዕመነ ድንግል አብረው ይጠቀሳሉ)፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ሐዘናቸውን ወደ ፈጣሪያቸው በማድረሳቸው ሱስንዮስ ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ (ተቀሰፈ)፡፡
-  የሱስንዮስ ልጅ ፋሲልም አባቴን ይፈውሱልኝ ብሎ መልእክትን ላከ፤ ጻድቁ ዐምደ ሥላሴና አባ ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ ማርያም ተገኝተው ካቶሊክነቱን ከተወ እሺ ብለው 3ት ሱባኤ ጸልየው ፈወሱት፤ ሱስንዮስም ንሥሐ ገብቶ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበለ፡፡ በሰኔ 21 1624ዓ.ም.
‹‹የእስክንድርያ ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ይመለስ፥
የሮም ካቶሊክ ሃይማኖት ይፍለስ፥
ልጄ ፋሲል ይንገሥ›› ብለው አዋጅ ነገሩ፤ ልጃቸው ፋሲልንም ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ቅብዓ መንግሥት (አፈዋተ መንግሥት) ቀብተው አነገሡት፤ ንጉሡም ለገዳሙ የእርሻ መሬት የሚሆን ጣቁሳ ላይ 44ት ጉልት ጐለተ፥ የገዳሙንም ስም ‹‹ማኅበረ ሥላሴ›› ብሎ ሰየመው፡፡
- ታላቁ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ቀድሞም ከእርሳቸው በፊት የነበረ ቢኾንም፤ በተለያዩ ዘመናት በጠላት የጠፋ ስለነበረ ዳግመኛ ያስፋፉትና እንደ መሶብ ያስባረኩት ናቸው፤
- ከወለዷቸው አንዱ ዐርከ ሥሉስ ከደረሳቸው አንዱ በኾነው በመልክአ ቊርባን ላይ፤

‹‹ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፤
ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ፡፡
ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ፤
ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፤
ተማኅጸነ ለክርስቶስ ሥጋሁ ወደሙ፡፡
በማለት የደረሱለት ሲኾን፤ በዚህም በየቀኑ በቅዳሴ ላይ ከቊርባን በፊት የማኅበሩን ስም የማይጠራ ቤተ ክርስቲያን የለም፡፡

፨ ብፁዕ አባ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ንብረቱ ገዳም ውስተ ሀቌሁ ቅንአቱ ዘአዲም ያስተጋብእ ጽድቀ ዘእምኵሎሙ ቅዱሳን በጾም ወበጸሎት ሀለወ በክብር ወበሰላም፡፡ /መሐረነ አብ/
/#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

#የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (#የሺዎች_ማኅበር)፤
፨ ምቅዋመ ሥላሴ፡፡

፨ስለ ገዳሙ አጠቃላይ ሁኔታ፤
*ገዳሙ የሚገኘው በሀገራችን በመተማ በረሃ ደቡባዊ ክፍል፥ ከጎንደር በስተምዕራብ አቅጣጫ (132 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ) ሲሆን፤ ከአ.አ. 901ኪ.ሜ. ርቀት ላይ፤ ከደረቅ ዐባይ ቀበሌ በ4ት ሰዓት የእግር ጕዞ ይገኛል፡፡ የጣቁሳ የቋራና የሱዳን በረሓማው አከባቢዎችም ያዋስኑታል፡፡

*ከፀሐዩ ሐሩር ማየልና ከቆላነቱ የተነሣ ‹‹በደንጊያው ላይ ተልባ ያስቆላል›› እየተባለ የሚነገርለት ነው፡፡ የተለያዩ ዕፅዋትና አራዊት የሚገኙበትም ሲሆን ቦታው በብሔራዊ ደረጃ ጥብቅ ደን ነው፡፡
* የገዳሙ ይዞታ ከ19ሺህ 186 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቦታ ስፋት የሚመስለው ዋልድባ (ዋሊ) ብቻ ነው፡፡ በዚህም ከሃገራችን ገዳማት 2ቱ ታላላቅ ገዳማት እጅግ በጣም ሰፋፊ ይዞታ ያላቸው ገዳማት ናቸው፡፡
* ገዳሙ በ፪ት ትላልቅ ወንዞች (በገንዳ ውኃና ሸንፋ ወንዝ) የተከበበ ነው፡፡
*ገዳሙ በሚገኝበት በረሃ ውስጥ 4ት ተራሮች(አምባዎች) ይገኛሉ፡፡ እነርሱም፤ ድባ(የማኅበረ ሥላሴ ገዳም ያለበት)፣ ከርከመች፣ ኩክቢና ጎርማስ ይባላሉ፡፡
*ገዳሙን በርቀት ሆነው የሚያዋስኑት ታላላቅ ገዳማትም፤ በሰሜን አቅጣጫ ደምጫ፥ በደቡብ ጋንጫ(ዋታሆ አቦ) ናቸው፡፡
*በገዳሙና በአካባቢው ከሚገኙት የተለያዩ ዕጽዋት መካከል (ሰርኪን፥ ሲና፥ የዕጣን ዛፍ/ዋልያ/፥ መቀር፥ ወርካ፥ ክርክራ፥ ሽመል) እና ሌሎችም ልዩ ልዩ ዕጽዋት የሚገኙበት ሲኾን፤ ከዱር አራዊት መካከልም (አንበሳ፥ ነብር፥ አጋዘን፥ ቶራ/ሚዳቋ/፥ ድኩላ፥ አሳማ፥ ጉሬዛ፥ ዝንጀሮ፥ ቀይ ጦጣ፥ የተለያዩ የእባብና የዘንዶ ዝርያዎች) ይገኙበታል፡፡
👍12