Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት  ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት  የተለያዩ መመሪያዎች  መተላለፋቸው ተገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ  የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ  የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም  ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ  ለማወቅ ተችሏል።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት  ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው።

በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና  ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም  ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ  መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።
54👏20👍12🙏3
"ሲሳያ ለነፍስ ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ"

/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍6👏51
"በጣሊያን ወረራ ወቅት አስተዋጽዖ ካደረጉት መካከል ዐበይቶቹ ገዳማትና አድባራት"


"…ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገደልና ዱር አላገኝ ስትል፤ ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤ 300 ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤ 2ሺ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡

"…ይህንን እኩይ ተግባሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማእታት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም መሐል አዲስ አበባ ላይ በ8 ጥይት ያረፉት)ና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት)

፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው ታላቁ ሊቅ አቡነ ክፍሌ፡፡

፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ የደብረ ሊባኖስ መነኰሳት፡፡

፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 የአቡነ ዜና ማርቆስ መነኰሳት፡፡

፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 የዝቋላ መነኰሳት፡፡

፠ በጥቅምት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ 2116 የሆኑ የደብረ ዳሞ መነኰሳት፡፡

፠ በሰኔ 3/1929 ዓ.ም 60 የታረዱ የምድረ ከብድ መነኰሳት፡፡

፠ በሰኔ 15/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ በዚህም አንበሶች ከጫካ ወጥተው ያለቀሱላቸው፤ 91 የሚሆኑ የአሰቦት መነኰሳት፡፡

፠ በኅዳር 25/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ ሲታረዱም ብርሃንም የወረደላቸው፤ 143 የአዲስ ዓለም ካህናትና መነኰሳት፡፡

፠ በየካቲት 12/1929 ዓ.ም ከ30 ሺ በላይ በአካፋ ሳይቀር የተጨፈጨፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፡፡

፠ በመጋቢት 16/1929 ዓ.ም. ከላይ በቦንብ የውሃ ገንዳውን ጭምር፣ ከታች በመትረየስ የተፈጁት 515
የማኅበረ ሥላሴ ገዳም መነኰሳት፡፡ የበቁ አባቶችም በጸሎታቸውም አውሮጵላኗን የከሰከሷት፡፡

፠ በመጋቢት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ ብዛታቸው በውል ያልታወቁ የደብረ ዓባይ ገዳም መነኰሳት፡፡

፠ በሚያዝያ 18 ና ሚያዝያ 20/1929 ዓ.ም የታረዱ 363  የመርጦ ለማርያምና የተድባበ ማርያም ካህናትና መነኰሳት፡፡

፠ በሐምሌ 29/1929 ዓ.ም. እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ግማሾቹ የተሰፉትና ግማሾቹ ደግሞ በግዞት የተወሰዱት ጎንደር ሊቃውንት፡፡

፠ በየካቲት 18/1929 ዓ.ም የተሠዉት የአዲስ አበባ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካህናት አባቶች፡፡

፠ በየካቲት 20/1929 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት ተለቅመው እንዲሰበሰቡ ከተደረገና ከተደበደቡ በኋላ እጅና እግራቸውን አስረው እሳት አጉርሰዋቸዋል፡፡

፠ የትግራይ ጨለቆት ሥላሴ አገልጋዮችና (ርዕሰ ደብር የነበሩትን አስተዳዳሪውን ጨምሮ) አስረው ‹‹በሮማ ካቶሊክ ታምናላችው ወይስ በረሃብ ትሞታላችሁ?›› እያሉ በረሃብ አሠቃይተዋቸዋል፡፡ እምቢ ቢሏቸው ጽኑ ግርፋት ገርፈው ከለቀቋቸው በኋላ በመኪና ገጭተው ገድለዋቸዋል፡፡

፠ ይደመቆ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/

፠ አፈር ባይኔ ተክለ ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/

፠ አክርሚት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/

፠ ጎበጥ አገር ገብርኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ እመ ምሕረት/

፠ አንኮበር ቅድስት ማርያም ቤ.ክ.

፠ ደረፎ ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/

፠ ጎንቻ መድኀኔ ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/

፠  አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።

#ጀግናውና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም
ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡

 ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤
እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡
ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤
ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡

 ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ ደግሞ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤

አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤
ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤
ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤
በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡
መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤
ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡

፠ ከ1927-1934 ዓ.ም ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀገራችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤

*በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤ *ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤

**የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ ከ30,000 በላይ ሰማዕታት፤
*በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤ *በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤ *ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤
*በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤ *ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤
*ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡ *ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣ *350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡

**ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡  (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍91👌1
፨ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡

፨ ኮከበ ክብር፥
*ሊቀ ሰማዕታት፥
*መክብበ ሰማዕታት፥
*የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥
*የልዳ ፀሐይ፥
*የኢትዮጵያ ገበዝ፥
*ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥
*፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥
*በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥
*፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥
*፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤
*እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤

፨የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ #መናገሻ_ገነተ_ጽጌ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍3👌1
መዝሙር ዘቅድስት

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
🙏9👍41
ቅድስት፤ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡

‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡

ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡

፨ የዕለተ ሰንበት ክብር፤
በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8
በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡
ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡

  ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡

   ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና››
  ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍11
፨ ቅዱስነትዎ እንኳን አደረስዎ ፨

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
31👍9
#ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳምና_ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ

፨ ታቦቱ_ሥላሴ፥ ፨ ጻድቁ_ዐምደ_ሥላሴ፥
፨ የገዳሙ ስም ማኅበረ ሥላሴ፡፡
፨ በየቀኑ በሁሉም ቤክ በቅዳሴ ላይ ስሙ የሚነሳው ገናናው ገዳም (ብዙዎች ግን የማያውቁት)፡፡
፨ እንኳን ሰዉ ከብቱ ሥርዐት ያለው ድንቅናዕፁብ ገዳም፡፡
፨ ገዳሙን ያጠፉ አውሮፕላኖችን በጸሎት የከሰከሱ አባቶች የሚገኙበት የበርካታ ትምህቶችና የጥበብ ማዕክል፤ …. ኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢያንስ አንዴ ሊያዩት የሚገባ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ገዳም!!!፡፡

፨ በዚህች በየካቲት 27 እለት ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወመነኰሳት (ለአቡነ ክፍለ ማርያም፥ ለአቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘቋራ፥ ለ፯ቱ ዘሥላሴ በመባል ለሚጠሩ ቅዱሳን፣ ለዐርከ ሥሉስ /የአርኬና የመልክአ ቊርባን ደራሲ/፤ ….) የኾኑትና ፤ ጽድቃቸውና ቃልኪዳናቸው እንደ ምድር አሸዋ የበዛው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት ለመቊጠር የሚያስቸግረው ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ ልደታቸውም እረፍታቸውም ነው፡፡

- እኒህ ጻድቅ የተወለዱት በጎጃም(ሸዋም የሚሉ አሉ) ሲኾን፤ የተወለዱትም ሆነ 104ዓመታት ከኖሩ በኋላ ያረፉበት ቀን በመድኀኔ ዓለም ወርኀዊ በዓል በየካቲት 27 ነው፡፡
- ጻድቁ በተለያዩ ገዳማት በአርድእትነትና ሥርዐተ አበው በማጥናትና በመተግበር ከቆዩ በኋላ፤ ምንኩስናን ከአቡነ ተንሥአ ክርስቶስ ዘትግራይ ተቀብለዋል፤ ኋላም ወደ ታላቁ ገዳም ገዳመ ዋሊ (ገዳመ ዋልድባ) ገብተው ከቆዩ በኋላ ወደ ገዳመ አስቄጥስ በመሄድ ለ18 ዓመታት ከቆዩ በኋላ በስተመጨረሻ ምናኔያቸውን በማኅበረ ሥላሴ አድርገዋል፡፡

* በ1616ዓ.ም. ሱስንዮስ 8,000 ክርስቲያኖችን የካቶሊክን ካልተቀበላችሁ ብሎ ጠዳ ላይ በሰየፈ ጊዜ ሳይፈሩና ሳይፍሩ ለሃይማኖታቸው ከተከራከሩና ጠበቃ ከኾኑት መካከል ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ (ሌሎችም ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ እኅተ ጴጥሮስ፣ ፍቅርተ ጴጥሮስ፣ ሐራ ድንግል ምዕመነ ድንግል አብረው ይጠቀሳሉ)፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ሐዘናቸውን ወደ ፈጣሪያቸው በማድረሳቸው ሱስንዮስ ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ (ተቀሰፈ)፡፡
-  የሱስንዮስ ልጅ ፋሲልም አባቴን ይፈውሱልኝ ብሎ መልእክትን ላከ፤ ጻድቁ ዐምደ ሥላሴና አባ ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ ማርያም ተገኝተው ካቶሊክነቱን ከተወ እሺ ብለው 3ት ሱባኤ ጸልየው ፈወሱት፤ ሱስንዮስም ንሥሐ ገብቶ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበለ፡፡ በሰኔ 21 1624ዓ.ም.
‹‹የእስክንድርያ ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ይመለስ፥
የሮም ካቶሊክ ሃይማኖት ይፍለስ፥
ልጄ ፋሲል ይንገሥ›› ብለው አዋጅ ነገሩ፤ ልጃቸው ፋሲልንም ጻድቁ ዐምደ ሥላሴ ቅብዓ መንግሥት (አፈዋተ መንግሥት) ቀብተው አነገሡት፤ ንጉሡም ለገዳሙ የእርሻ መሬት የሚሆን ጣቁሳ ላይ 44ት ጉልት ጐለተ፥ የገዳሙንም ስም ‹‹ማኅበረ ሥላሴ›› ብሎ ሰየመው፡፡
- ታላቁ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ቀድሞም ከእርሳቸው በፊት የነበረ ቢኾንም፤ በተለያዩ ዘመናት በጠላት የጠፋ ስለነበረ ዳግመኛ ያስፋፉትና እንደ መሶብ ያስባረኩት ናቸው፤
- ከወለዷቸው አንዱ ዐርከ ሥሉስ ከደረሳቸው አንዱ በኾነው በመልክአ ቊርባን ላይ፤

‹‹ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፤
ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ፡፡
ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ፤
ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፤
ተማኅጸነ ለክርስቶስ ሥጋሁ ወደሙ፡፡
በማለት የደረሱለት ሲኾን፤ በዚህም በየቀኑ በቅዳሴ ላይ ከቊርባን በፊት የማኅበሩን ስም የማይጠራ ቤተ ክርስቲያን የለም፡፡

፨ ብፁዕ አባ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ንብረቱ ገዳም ውስተ ሀቌሁ ቅንአቱ ዘአዲም ያስተጋብእ ጽድቀ ዘእምኵሎሙ ቅዱሳን በጾም ወበጸሎት ሀለወ በክብር ወበሰላም፡፡ /መሐረነ አብ/
/#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

#የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (#የሺዎች_ማኅበር)፤
፨ ምቅዋመ ሥላሴ፡፡

፨ስለ ገዳሙ አጠቃላይ ሁኔታ፤
*ገዳሙ የሚገኘው በሀገራችን በመተማ በረሃ ደቡባዊ ክፍል፥ ከጎንደር በስተምዕራብ አቅጣጫ (132 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ) ሲሆን፤ ከአ.አ. 901ኪ.ሜ. ርቀት ላይ፤ ከደረቅ ዐባይ ቀበሌ በ4ት ሰዓት የእግር ጕዞ ይገኛል፡፡ የጣቁሳ የቋራና የሱዳን በረሓማው አከባቢዎችም ያዋስኑታል፡፡

*ከፀሐዩ ሐሩር ማየልና ከቆላነቱ የተነሣ ‹‹በደንጊያው ላይ ተልባ ያስቆላል›› እየተባለ የሚነገርለት ነው፡፡ የተለያዩ ዕፅዋትና አራዊት የሚገኙበትም ሲሆን ቦታው በብሔራዊ ደረጃ ጥብቅ ደን ነው፡፡
* የገዳሙ ይዞታ ከ19ሺህ 186 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቦታ ስፋት የሚመስለው ዋልድባ (ዋሊ) ብቻ ነው፡፡ በዚህም ከሃገራችን ገዳማት 2ቱ ታላላቅ ገዳማት እጅግ በጣም ሰፋፊ ይዞታ ያላቸው ገዳማት ናቸው፡፡
* ገዳሙ በ፪ት ትላልቅ ወንዞች (በገንዳ ውኃና ሸንፋ ወንዝ) የተከበበ ነው፡፡
*ገዳሙ በሚገኝበት በረሃ ውስጥ 4ት ተራሮች(አምባዎች) ይገኛሉ፡፡ እነርሱም፤ ድባ(የማኅበረ ሥላሴ ገዳም ያለበት)፣ ከርከመች፣ ኩክቢና ጎርማስ ይባላሉ፡፡
*ገዳሙን በርቀት ሆነው የሚያዋስኑት ታላላቅ ገዳማትም፤ በሰሜን አቅጣጫ ደምጫ፥ በደቡብ ጋንጫ(ዋታሆ አቦ) ናቸው፡፡
*በገዳሙና በአካባቢው ከሚገኙት የተለያዩ ዕጽዋት መካከል (ሰርኪን፥ ሲና፥ የዕጣን ዛፍ/ዋልያ/፥ መቀር፥ ወርካ፥ ክርክራ፥ ሽመል) እና ሌሎችም ልዩ ልዩ ዕጽዋት የሚገኙበት ሲኾን፤ ከዱር አራዊት መካከልም (አንበሳ፥ ነብር፥ አጋዘን፥ ቶራ/ሚዳቋ/፥ ድኩላ፥ አሳማ፥ ጉሬዛ፥ ዝንጀሮ፥ ቀይ ጦጣ፥ የተለያዩ የእባብና የዘንዶ ዝርያዎች) ይገኙበታል፡፡
👍12