ዐጤ ኃይለ ሥላሴም ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ በ6 ኪሎ ለሰማዕታቱ ሐውልት ቆመ መጀመሪያ የተሠራው አነስተኛ በመሆኑ ኋላ አሁን ያለው ትልቅ ተደርጎ ተሠርቷል፡፡ ቀኑ እንዳይረሳም ቤተ ሳይዳ ተብሎ ይጠራ የነበረው የካቲት 12 ሆስፒታል ተባለ፡፡ ከ8 ዓመት በኋላም የሰማዕታቱንም ዐፅም ሰብሰብሰበውና አፍልሰው በ4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክብር እንዲያርፍና መቃብር ቤት እንዲሠራለት ተደረገ፡፡ በሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍና ግጥም እንዲህ ይነበባል፤
#‹‹ዝንቱ ውእቱ ምዕራፈ አዕጽምቲሆሙ ለብዙኃን ኢትዮጵያውያን እለ ተቀትሉ በግፍዕ በእደዊሆሙ ለሕዝበ ኢጣሊያ ፋሽስታውያን አመ ፲ወ፪ ለየካቲት በ፲ወ፱፻፳ወ፱ ዓ.ም.፤ ወተቀትሎቶሙኒ ኮኑ በውግረተ አእባን ወበአብትር፥ በመክርይ ወበመስኤ፥ በመሕፄ ወበዕፀው፥ በመብረቀ ሐፂን ወበፀዓዕ፥ ወበውዕየተ እሳት ውስተ ቤቶሙ፡፡ ወበራብዕ ዓመት እምዘኮነ ዝንቱ ነገረ ግፍዕ ተመይጠ እግዚእነ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እም ሀገረ ብሪታንያ በግርማ መዊዕ፤ ወአቲዎ ብሔሮሙ ሠረዎሙ ለጸላእትነ ወአቀመ ትእምርተ ግዕዛንነ፡፡ ወእምድኅረዝ አዘዞሙ ለኅሩያኒሁ ከመ ያስተጋብኡ አዕጽምቲሆሙ ለእሉ እለ ተቀትሉ በግፍዕ ወያንብርዎሙ ውስተ ዝንቱ መካን ቅዱስ ዘሕኑፅ ለዝክረ ነገር ወለዝክረ ስሙ፤ ወኮነ በዓለ ፍልሰቶሙ ወተጋብኦቶሙ ለእሙንቱ አዕጽምተ ምውታን በ፲ወ፬ ዓመተ በዓለ ንግሡ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትየጵያ አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት በዕለተ ኀሙስ በ፲ወ፱፻፴ወ፯ዓ.ም.፡፡››
#ራስን ካንገት ላይ ቈራርጦ እየጣለ፤
በችንካር ቸንክሮ ሰው እየገደለ፤
ሰውን ከነቤቱ አብሮ እያቃጠለ፤
ማነው እንደ ፋሽስት በሰው ግፍ የዋለ?፡፡
ሥጋችንን ገድለው ሳይቀብሩ እየጣሉ፤
ስማችንን ገድለው ሊቀብሩት ከጀሉ፡፡
በዚህ ያልነበሩ ሐሰት እንዳይሉ፤
እሊህ አስከሬኖች ይመሰክራሉ፡፡
ይህን ታላቅ ስቃይ መከራና ግፍ፤
ሲያስታውስ ይኖራል የታሪክ መጽሐፍ፡፡
አትርሱት አንርሳው ያስታውሰው ዘራችን፤
ኢጣሊያ መሆኗን መርዛም ጠላታችን፡፡
እናንት አእጽምቶች ዕድለኞች ናችሁ፤
በኃይለ ሥላሴ ትንሣኤ አገኛችሁ፡፡

👍8
#ጀግናውና_የቅኔው_አዝመራ_አለቃ_መርሻ_ወልደ_ማርያም
ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡
ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤
እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡
ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤
ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡
ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤
አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤
ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤
ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤
በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡
መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤
ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡
/ቢያነቧቸው ስለ የካቲት 12ና ስለ 5ቱ ዓመት የመከራ ዘመን በርካታ ቁም ነገርን ያስጨብትዎታል፤/
#አምስቱ የመከራ ዘመናት፣ ቅጽ 1፤ 44 የተመዘበሩ. የተቃጠሉና የጠፉ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፣ እርቅይሁን በላይ፣ 2007
#“The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937” (“የደብረ ሊባኖስ እልቂት)፣ ኢያን ካምፕቤል፣ # "ሕይወቴ(ግለ ታሪክ)" ተመስገን ገብሬ፤
#የሸንቁጥ ልጆች፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ
#"Yekatit" 12 Revisited: new light on the strike against Graziani Author(s): Ian Campbell Source: Journal of Ethiopian Studies, Vol. 40, No. 1/2, Festschrift Dedicated in Honour of Prof. Richard Pankhurst & Mrs. Rita Pankhurst (June-December 2007), pp. 135-154
/ታሪኩን ከመጻሕፍት አገላብጦና ምሁራንን ጠይቆ ላቀረበልን አምላከ ኢትዮጵያ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በእድሜ በጤና ይጠብቅልን፡፡/

👍8❤2
የእርዳታ ጥሪ
የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት አባል የሆነች እኅታችን በልብ ሕመም ከሁለት ጊዜ በላይ ቀዶ ጥገና አድርጋለች የተደረገላት ህክምና በቂ ባለመሆኑ ሌላ ቀዶ ጥገና ለመደረግ ተወስኗል ለዚህ ህክምና የተጠየቀችው ገንዘብ በቂ ስላልሆነ ይህ ትኬት ተዘጋጅቷል ትኬቱ 100 ብር ነው ሁላችን በመግዛት የልጅቷን ሕይወት እናትርፍ።
ትኬቱን በሰ/ት/ ቤታችን በበጎ አድራጎት ክፍል ያገኙታል
ሄኖክ 0900021866
ሰሎሞን 0933062383 በመደወል ትኬቱን ይውሰዱ።
#Share

👍28❤12🙏9🤝2
እንኳን ለእመቤታችን ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤
ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ፡፡
(ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች የካቲት አሥራ ስድስት ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡
ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም የሚያጠጡ(በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ) ፣ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡
#ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16፤ #በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡
በሃገራችን በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመው፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ነው፡፡ እነዚህም፤
1ኛ) የላይ ቤት፤ የደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት
2ኛ) የታች ቤት አብነት፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ
3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡
እኛም ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ የዐቢየ እግዚእንና የበዓታን ይትበሃል አንድ ላይ በቅደም ተከተል አድረገን አዘጋጅተንላችኋል፤ የደፈጫ ከላይ ከተጠቀሱት ከ2ቱ በጥቂት ቀለም ብቻ የሚለይ በመኾኑ አላካተትነውም፡፡ ስለዚህ እንደ የደብራችሁ ይተበሃል የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ) የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡
መልካም ማኅሌት፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍8❤5
እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሳችሁ!
ጾሙ የካቲት 17 ይገባል
#የዐቢይ_ጾም_ሳምንታት_ስያሜዎች
፩ኛ)የመጀመሪያው እሑድ(ሳምንት)፥ #ዘወረደ (ሙሴኒ፣ ጾመ ሕርቃል) ይባላል፡፡ አምላክ ከሰማይ መውረዱን፣ ሰው መሆኑንና ነገረ መስቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡
፪ኛ. የሁለተኛው እሑድ፥ #ቅድስት ይባላል፤ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው
፫ኛ. የሦስተኛው እሑድ፥ #ምኲራብ ይባላል፤ በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኲራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡
፬ኛ. ዐራተኛው እሑድ፥ #መፃጉዕ ይባላል፤ ድውያንን መፈወሱን፣ ዕውራንን ማብራቱን፣ የሚያነሣ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፭. አምስተኛው እሑድ፥ #ደብረ_ዘይት ይባላል፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሁኖ ያስተማረው ትምህርት፥ የዳግም ምጽአትን ነገር የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፮. ስድስተኛው እሑድ፥ #ገብርኄር ይባላል፡፡ የጌታውን ብር ተቀብሎ ያተረፈበት፣ በጌታውም ፊት ምስጋናን ያገኘው ሰው ታሪክ ይዘመርበታል፡፡
፯. ሰባተኛው እሑድ፥ #ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ እየመጣ ይማር የነበረውን የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
፰. ስምንተኛው እሑድ፥ #ሆሣዕና ነው፡፡ ጌታ በአሕያ ውርንጭላ ሆኖ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡
፨ ከሠርክ ሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ያለው ሰባት ቀን #ሕማማት ይባላል:- የጌታን መከራና ስቃይ እንዲሁም ሞት የምናስታውስበት ሳምንት ነው ፡፡
#የዐቢይ_ጾም_ሌሎች_መጠሪያ_ስያሜዎች
፩. ዐቢይ ጾም ይባላል፤
፪. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤
፫. የካሣ ጾም ይባላል፤
፬. የድል ጾም ይባላል፤
፭. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፤
፮. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፤
፯. የቀድሶተ ገዳም ጾም፤
፰. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፤
፱. የሥራ መጀመሪያ ጾም፤
፲. ጾመ አርብዓ ይባላል፡፡

👍11🥱1