#በአዲስ_አበባ_በብቸኝነት_እንደ_ደብረ_ሊባኖስ_ገዳም_በየቀኑ_ውዳሴ_ማርያም_በዜማ፥#ክስተተ_አርያም_በዜማ፤#መስተጋብዕ_በዜማ_የሚያደርሰው_ደብራችን_ደብረ_ሰላም_የዜማ_ትምህርት_የተጀመረበትን_ ፴፪ኛ #ዓመት_ጥር_18 (24) 2017 ዓ.ም. አክብሯል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን የምታስምራቸውን ትምህርቶች በዘርፍ በዘርፍ ከፍላ ነው የምታስተምረው፤ እነዚህም የፊደል ቤት፣ የንባብ ቤት፣ የዜማ ቤት (ከሰላም ለኪ ዜማ ጀምሮ ውዳሴ ማርያም፣ ሰዐታት፣ ቅዳሴያት፣ ምዕራፍ፣ ድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋስዕት፣ አቋቋም፣….)፣ የቅኔ ቤት፣ የትርጓሜ ቤት፣ የቊጥር (የአቡሻኽር) ቤት ብላ በመክፈል ነው፤ ከእነዚህ ትምህርቶችም አብዛኞቹ በደብራችን የሚሰጡ ቢኾንም፤ የዓለማዊ (የአስኳላ) ትምህርት በእጅጉ እየተስፋፋ በመጣባቸው ዘመናት (ከ1960-1980 ተማሪዎች በቀኑ መርሐ ግብር የዓለማዊ (የአስኳላ) ትምህርት ስለሚማሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የሚማሩበት ጊዜ አጥተው፤ ደብራችንም በአዲስ አበባ ከሚገኙ አድባራትና ገዳማት ሰፊ አጥቢያን የሚያቅፍና የብዙ ሊቃውንት መኖሪያ እንደመኾኑ መጠን ከአጥቢያው የሚወለዱ ተተኪ እንደሚፈለገው መጠን ሳይኾን እስከ 1985ዓ.ም. ዘልቆ ነበር፡፡
ይህንን ችግር በውል የተረዱት ቄሰ ገበዝ መርሐ ጽድቅ ኃ/ጊዮርጊስ በቀኑ መርሐ ግብር የአስኳላ ትምህርታቸውን ለሚማሩ ተማሪዎች በማታው መርሐ ግብር የንባብና የዜማ ትምህርትን በራሳቸው ተነሳሽነት ‹‹ዘነሳእክሙ በጸጋ፥ ሀቡ በጸጋ›› የሚለውን ሲማሩ ያደጉትን የወንጌል ቃልና፤ ቀደሞውንም የተማሩት ከታላቁ ሊቅ አለቃ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል በመኾኑ፤ የወንጌልን ቃልና የመመህራቸውን አሠረ ፍኖት ተከትለው ያለምንም ደመወዝ በመቃብር ቤት ማስተማር ጀመሩ፤ እነኾ ዘንድሮም ማስተማር ከጀመሩ 26 ዓመታትን አስቈጠሩ፤ በእነዚህ ዓመታትም ከ850 በላይ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ አብዛኞችንም እስከ ዲቁናና ቅስና ማዕርግ ያበቁ ትጉህና ታታሪ መምህር ናቸው፤ ማታ ማታ ከ12፡30-3፡00 ለ32 ዓመታትም ተማሪዎቼን ማስተማር ይበልጥብኛል ብለው ብዙ ነገሮችን (ማኅበራዊ ጉዳዮችን ሳይቀር) ትተው እያስተማሩ ያሉ ታላቅ መምህራችንም አባታችንም ናቸው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤታችንም ላፈራቻቸው ዲያቆናትና ቀሳውስት ትልቁን አስተዋጽዖ ያደረጉት እኒሁ መምህር ናቸው፡፡ ስለ መምህራችንም የቱን ተናግረን እንዘልቀዋለን!! ወደፊት የእርሳቸውን የሕይወት ልምድ፣ ምክር ይዘን የምንቀርብ መኾኑን እንገለጽን፤
የዜማ ትምህርቱ ከዛሬ ከ32 ዓመታት በፊት በ1985ዓ.ም. በመቃብር ቤት በመመህራችን በቄሰ ገበዝ መርሐጽድቅ ኃ/ጊዮርጊስ (ከ10-15 በሚጠጉ ተማሪዎች /ለአብነትም ሸዋረጋ አዳነ፣ ሚሊዮን ከበደ፣ አዲስ ወርቅ ደበበ፣ ደረጀ ተክሌ፣ በላይ አዳነ፣ መሳፍንት አለማየሁ፣ …./ ተነሳሽነት የተጀመረ ነው፡፡
በመቀጠልም ተማሪው እየበዛ በመምጣቱ የዜማ መማሪያ ቦታው (መቃብር ቤቱ) ባለመቻሉ ወደ ደወል ቤት መጣ በቅቱም ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በግምት 120-125 ይጠጉ ነበር (በወቅቱ ይማሩ ከነበሩት ውስጥም ለአብነት ያህል ቴዎድሮስ አዳነ፣ ዮሐንስ ደምሴ፣ ወንድይፍራው ጌታቸው፣ ፍስሐ አዱኛ፣ ተፈሪ ተስፋዬ፣ ሰብስቤ ተክለማርያም፣ ዘለዓለም ተረፈ፣ ዘካርያስ አለማየሁ፣ መልአኩ ገብረሥላሴ፣ (አቡሽ) ገብረሥላሴ፣ ቃልአብ አለማየሁ፣ ሔኖክ አለማየሁ፣ ሚሊዮን እሸቱ፣ ዐሥራት ለይኩን፣ ሚሊዮን ለይኩን፣ ተክሉ ተዋበ፣ ፣ ተስፋዬ ገብረሥላሴ፣ ደሳለኝ ገብረ ሥላሴ፣ ምሕረቱ አዳነ፣ በልሁ ሰሎሞን፣ ጥበቡ መኮንን፣ ከተማ ወርቅአለማሁ፣ ቡሩክ አድማሱ፣ ደርብ ወርቁ፣ ዐሥራት ማሙዬ፣ ዐቢይ አለማየሁ፣ ግሩም መልአኩ፣ አበባየሁ ዕንቈ፣ ጌትዬ ዕንቈ፣ ዳንኤል ገብረ ሥላሴ፣ ካሣ ፍቅሩ፣ አፈወርቅ ማሞ፣ ጸጋ ዘአብ ማሞ፣ ስንሻው ውብአየሁ፣ ይስሐቅ ውብአየሁ፣ ስዩም አስቻለው፣ ናርዶስ ንጉሤ፣ አቡሽ ጌታቸው፣ ………… ይገኙበታል፤ አብዛኛው ተማሪዎችም የማርገጃ አካባቢ ልጆች ነበሩ፤ በአብዛኛው የአካባቢ ተወላጆች ዲያቆናትን ደብሩ ያፈራበት ዘመን ነበር፤ ለዚህም የዜማ ትምህርቱ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡
ከደወል ቤት ቀጥሎ የመማሪያ ቦታው ወደ ወንዶች መጠለያ (ገረገራ)ና በመሃል ላይ ወደ ደብሩ የአብነት ትምህርት ቤት እየተዘዋወረ ትምህርቱ ሲሰጥ ቆይቷል፤ በዚህ ወቅትም ከ105-110 የሚጠጉ ተማሪዎች ሲኾኑ፤ በወቅቱ ከተማሩ ተማሪዎች መካከልም መስፍን ለገሠ፣ ስመኘው ጌትዬ፣ ዮሐንስ ጌትዬ፣ ዘካርያስ ጌትዬ፣ ሱራፌል አውግቸው፣ ወንድወሰን ሺፈራው፣ ኢሳይያስ ቦጋለ፣ ያሬድ እንደሻው፣ ….. ይገኙበታል፤ በዚህ ወቅትም ከማርገጃ አካባቢ በተጨማሪ ከሌሎች የደብሩ አጥቢያዎች (ከቀጨኔ፣ ከሰሜን፣ ከችሎት፣ ከ20ቀበሌና ከመነን) መጥተው ተማሪዎች መማር የጀምሩበት ነበር፡፡
አሁን ባለንበት ጊዜ ደግሞ በቋሚነት በወንዶች መጠለያ (ገረገራ) ትምህርቱ እየተሰጠ ይገኛል፤ በአሁኑ ወቅትም በፊት ወንድሞች ይማሩ የነበረው ይህ የማታ የዜማ ትምህርት እኅቶችንም ያካተተ ሁኗል፡፡ አሁን ባለበት የዜማ ትምህርት ሒደት ከምሽቱ 12፡30 ላይ ውዳሴ ማርያም በዜማ፥ ክስተተ አርያም በዜማ፤ እንዲሁም መስተጋብዕ በዜማ ከደረሰ በኋላ የትምህርቱ መርሐ ግብር እስከ ምሽቱ 2፡30 ድረስ ይካሔዳል፤ ከ32 ዓመታት በፊት የዜማ ትምህርቱ በተጀመረበት ወቅት ግን መርሐ ግብሩ ላይ ይደርሱ የነበሩት የዜማ ይዘቶች አሁን የሚደርሱት እንዳሉ ሁኖ ሌሎች የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶችም የሚጨምር ነበር፡፡
ይህ የዜማ ትምህርት ከቀድሞ የወረሰውን የፍልሰታ ልዩ የሱባኤ የጸሎት መርሐ ግብር እና የደብረ ታቦር ዝክርን፤ አሁንም ሳይቋረጥ አሁን በመማር ላይ ያሉ፣ ከዚህ በፊት የተማሩና የደብሩ ማኅበረ ካህናትና ዲያቆናት በአንድነት በመኾን ሱባኤውንና የደብረ ታቦር ዝክሩን አጠናክረው የቀጠሉበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤11👍1😢1
❤26😢12👍7🥰2
#ጥር_29_ጻድቁና_ሰማዕቱ_አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽና_አቡነ_ማትያስ_በውቢት_ገደል_/ጽላልሽ፥ ከሰም ወንዝ ቆላ ውስጥ የሚገኝ/ #ተወርውረው_ሰማዕትነት_የተቀበሉበት_ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ለብዙ ዓመታት ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2005ዓ.ም. የመቃኞ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶለታል፡፡
#አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፤ አባታቸው ካህኑ ሮማንዮስ /የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት/ እናታቸው ማርታ ይባላሉ፡፡ የትልድ ቦታቸው ጽላልሽ ዞረሬ ነው፡፡ ሲወለዱ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ የታየ ሲሆን እርሳቸውም በብርሃን ልብስ ተጠቅልለው ታይተዋል፡፡ ትምህርታቸውን ከሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ በጽዮን በሚገባ ተምረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት ተሻግረው ሞተሎሚን አስተምረው ካሳመኑት በኋላ አቡነ ታዴዮስን ወደ እርሳቸው እንዲመጡ ልከውባቸው ሄደው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ ዘጠኝ ዓመት ተቀመጡ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ግን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ አቡነ ታዴዎስም ወደ ጽላልሽ ተመልሰዋል፡፡ ሁለቱም ከ32 ዓመት በኋላ ተመልሰው በጽላልሽ ተገናኘተው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአቡነ ታዴዎስ ማዕረገ ምንኵስናን ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚያም አቡነ ታዴዎስም በሥጋ ዕድሜ ታላቅ ቢሆኑም እንደታናሽ ብላቴና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ በደብረ ሊባኖስ ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ታዴዎስን ወደ ጽጋጋ እንዲሄዱ ነገሯቸው ምክንያቱም አቡነ አኖሬዎስ በዚያ ሲያስተምሩ ከሃዲያን ደብድበው አስረዋቸው ነበርና አቡነ ታዴዎስን ሕዝቡን ከኃጢአት ግዞት፥ አኖሬዎስን ከእስራት እንዲያስፈቱ ላኳቸው፡፡
አቡነ ታዴዎስም በነፋስ ሠረገላ ተጭነው መዩጥ ከተባለውና አኖርዮስን ካሰራቸው ንጉሥ ፊት ቢደርሱ ንጉሡ በግንጋጤ መልአክ የመጣበት መስሎት ሲፈራ ከሰው ወገን መሆናቸውን ነግረው ክርስትናን አስተማሩት፡፡ ጋኔን ከእሳት ጥሎት ሲሠቃይ የሚኖርና ሊሞት የደረሰ ልጁን ቢፈውሱለት በትምህርታቸውና በተአምራታቸው አምኖ ሕዝቡ ክርስትናን እንዲቀበል በአዋጅ አስነገረ፡፡ አፍጃል የሚባለው ባለጸጋ ወደ አቡነ ታዴዎስ ቀርቦ ሲማር ‹‹ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል›› (ማቴ 19፡24፣ ማር 10፡25፣ ሉቃ 18፡25) የሚለውን የወንጌል ቃል ሲሰማ ለአእምሮው ረቆበት ‹‹እስቲ አድርገህ አሳየኝ?›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም እናቲቱን ግመል ከነጇ ቀጥሎም 28 ግመሎችን በየተራ በመርፌ ቀዳዳ እያሾለኩ አሳይተውታል፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በእጅጉ ሲገረምና ‹‹በአምላከ ታዴዎስ ስም አምናለሁ›› ሲል የባለጸጋው ልጅ ሙሳ ግን ‹‹በምትሃት አሳይቶን ነው እንጂ የእውነት አይደለም›› በማለት አባቱንም እንዳያምን ይናገር ጀመር፡፡ ይህንንም ሲናገር በመጀመሪያ ያለፈችው እናቲቱ ግመል ረግጣ ገደለችው፡፡
አቡነ ታዴዎስም ንጉሡን፣ አባቱን አፍጃልንና ሕዝቡን የሞተ እንደሚነሣ ሲያስተምራቸው ‹‹የሞተ ይነሣልን? እስኪ ይህ የሞተው ልጅ ይነሳና ሁሉም አይቶ ይመን›› አሏቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ዛሬ ተቀብሮ ይዋልና ነገ በሦስተኛው ይነሣል›› ብለዋቸው ተቀብሮ ዋለ፡፡ በማግሥቱም አፍጃልን ጠርተው ‹‹‹አልዓዛርን ከሞት ባስነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ሆይ ና ውጣ› ብለህ ከልጅህ መቃብር ላይ አኑረው› ብለው ዘንጋቸውን ሰጡት፡፡ ሄዶም እንዳሉት ቢያደርግ ልጁ አፈፍ ብሎ ተነሥቷል፡፡ ይህንን ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እሳቸውም 12 አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸው ሞቶ የተነሳውን ሙሳን ሙሴ ብለው ሰይመው አስተምረው ሊቀ ካህናት አድርገው ሾመውት አቡነ አኖሬዮስን ይዘው ወደ ጽላልሽ ዞረሬ ተመልሰዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ አባ ያዕቆብ የተባሉ ጳጳስ ከግብፅ መጡ፡፡ የአቡነ ታዴዎስን ዜና ሲሰሙ ተደስተው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ሆነው አስጠርተዋቸው ‹‹የአባታችሁን ዜና ገድል ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም ‹‹ጨዋታ በአስተርጓሚ አይሰምርም›› ብለው ወደ ጌታችን ቢጸልዩ የጳጳሱ ቋንቋ ለታዴዎስ፣ የታዴዎስም ቋንቋ ለጳጳሱ ተገልጦላቸው የመሸ የነጋ ሳይመስላቸው 40 ጾምን ሲጨዋወቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጳጳሱ ከንጉሡ ተማክረው ‹‹ሊቀ ካህናት ዘጽላልሽ›› ብለው ሾመዋቸዋል፡፡
በነግህና በሰርክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ፣ ቀን ወንጌልን እየሰበኩ፣ ሌሊት ከባሕር ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ ሳለ ከ10 ዓመት በኋላ ሰይጣን በንጉሡ በዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አሳድሮበት በክፉዎችም ምክር አታሎት የአባቱን ቅምጥ አገባ፡፡ አቡነ ታዴዎስም ይህን ሲሰሙ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ገሥጸው አወገዙት፡፡ ገሥጸውና አውግዘው አቡነ ማትያስን አስከትለው ሲመለሱ ቅምጧ የንጉሡ ሚስት በፈረስ ተከትላ ደርሳ የኋሊት አሳስራ ዛሬ ‹‹ማርያም ገዳም›› ከሚባለው ቦታ ፊት ለፊት ካለውና ‹‹ውቢት ገደል›› ከሚባለው ትልቅ ገደል ውስጥ ሁለቱንም ጣለቻቸውና ጥር 29 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው ‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005 ዓ.ም ከኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያናቸው በታላቅ ክብር ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
(ዋቢ፤ ገድለ ታዴዎስ፣ በ2009ዓ.ም. የዋሊ ተጓዦች የቦታው አባቶች በቃል የነገሩን፣ በቦታው የተዘጋጀች በራሪ ጽሑፍ፣ ከገድላት አንደበት)

❤8👍2
#አቡነ_ገብረ_ናዝራዊ_ዘደብረ_ኀረይክዋ_ዘጥሙጋ)፤ #ጥር_29
ጻድቅሰ በአሚን የሐዩ (ጻድቅ ግን በሃይማኖቱ በሕይወት ይኖራል) /ዕን. 2፥4፤ ሮሜ 1፥17/ ጻድቃን ምንም እንኳን በሥጋ ቢሞቱም የነፍስ ሞት የለባቸውምና ነው፡፡
*አቡነ ገብረ ናዝራዊ ዘደብረ ኀረይክዋ(ዘጥሙጋ)፤ አባታቸው ስቡሐ አምላክ እናታቸው ክርስቶስ ክብራ የሚባሉና ከነገሥታት ወገን የነበሩ ናቸው፤ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ሰሜን ሸዋ ይፋትና ጥሙጋ ደብረ ሲና ተወለዱ፡፡ ስማቸውን ያወጡላቸው ወላጆቻቸው ናቸው ገብረ ናዝራዊ ማለት በስዕለት ለእግዚአብሔር የተሰጠ ልዩና የተቀደሰ ማለት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማሩ አድገው በ15 ዓመታቸው ከአቡነ ዮሐንስ ዘንድ ዲቁናና ተቀበሉ፡፡
*ኋላ ሥርዐተ ምንኵስናን ደግሞ ከአቡነ ጎርጎሬዎስ (የደብረ ጽጋጋው የታላቁ አኖሬዎስ ልጅ) ከተቀበሉ በኋላ የተወለዱበትን ደብር ሲያገለግሉና በምደረ ሸዋና አካባቢዋ ሲያስተምሩ ቆዩ፤ ንጉሡ ዐምደ ጽዮን የአባታቸውን ሚስት በማግባታቸው ጻድቁ አቡነ ገብረ ናዝራዊ፣ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብና ሌሎች ካህናት ይህንን ተግባር በመቃወማቸው ለጥቂት ሳምንታት በእስር ቤት ቆዩ፤ ጻድቁ ከእስር እንደተፈቱም በላስታ ላሊበላ ለ12 ዓመታት፣ በሐይቅ እስጢፋኖስ ደግሞ ለጥቂት ወራት ሰንብተው፤ ወደ ትግራይ ተጕዘው ከአባ የዕቆብ ዘንድ የመጻሕፍት ትርጓሜን ሲማሩ ቆዩ፤ ዛሬ በስማቸው ወደ ሚጠራው ታላቁ ገዳም እምባ ላም ደብረ ኀረይክዋ ለምናኔ ከመግባታቸው በፊትም በትግራይ ሃገር እየተዘዋወሩ ሦስት ገዳማትን መሥርተዋል፤ እነርሱም፤
#አጋዝና_ተራራ /#መበቊል_ቋጥኝ/ (ምዕራብ አዲግራት)
#ከቋጥኝ_ድንጋይ_ፈልፍለው_ያነጿት_ቂዓት_ማርያም፤ /ጻድቁ ለ8ዓመት ቆይተውባታል/
#ባለ_2ት_ዐምድና_ባለ_1_በር_አድርገው_ያነጹት_ማይ_ኢየሱስ_/#ቀበሌ_አዘባ_ቤት_ሓባ_ተራራ/
እነዚህን ገዳማት ከሠሩ በኋላ በዘንዶ እንደ አቡነ አገረጋዊ ወደ ደብረ ኀረይክዋ ተራራ ለምናኔ ወጥተዋል፤ ቦታውን ‹‹ደብረ ኀረይክዋ›› ብለው ራሳቸው ሲሆን የሰየሙት፤ ምክንያቱም ቦታው በተራራማና በተፈጥሮ የተዋበ ቦታ በመሆኑ፤ በተፈጥሮ ቅርጽነቱ ባለ ሦስት ማዕዝን ክብና በገመድ የሚወጣ ገዳም ነው፡፡
#ጻድቁ_ከሚታወቁባቸው_ነገሮች_ዋነኞቹም፤
**በተሰጠቻው ሀብተ ፈውስ ብዙ ሕሙማንን ይፈውሱ ነበር፤
**ፍጹም ተሐራሚ በመሆናቸው(የበሰለ ነገር ወደ አፋቸው ሳያስገቡ ሃያ አራት ሰዓት በዳዊት መዝሙር ይደሰቱና ላባቸው እስኪንጠፈጠፍም ይሰግዱ ነበር) ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ከአንድ ማዕድ ውጪ አይቀምሱም ነበር፤
**ይስሐቅ የተባለው ደቀ መዝሙራቸው ሩቅ ሃገር ሄዶ ሲያርፍ ተገልጾላቸው ጸሎት እንዲደረግ ለደቀ መዛሙርቶቻቸው ተናገረዋል፡፡
*ከ44ት በላይ የውኃ ጕድጓዶችን ፈልፍለዋል /ለአብነትም ማይ መስቀል፥ ማይ ዮርዳኖስ፥ ማይ መቅደስ፥ ማይ ጠላዕ፥ ማይ ፀላእ ሰዋ የሚሉት ይገኙበታል/
**ሰንብታት እንዲከበሩ /በተለይ አብዛኛው ትቷት የነበረችውን ቀዳሚት ሰንበት እንድትከበር ታግለዋል/ በዚህም ከታላቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቀጥሎም ሰንበትን አክብሮ በማስከበር ጻድቁ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ፡፡
**በየሃገራቱ እየተዘዋወሩ ወንጌልን የሚሰብኩና ወንጌል የሚያዘውን ያለቻቸውን ነገር ይመጸውቱ ነበር
**ለደቀ መዛሙርቶቻቸውም ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተምሩ፤ ሃይማኖታቸው በጸና ዓለት ላይ የተመሠረተ እንዲሆንና ሃይማኖትን ከሚያስቱ ሐሰተኞች እንዲጠበቁና ዓለምና ክብሩ እንዳያታልሏቸው ይመክሯቸው ነበር፡፡
**በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡፡
#ላህም_አምባ_ደብረ_ኀረይክዋ
#እንደነ #ደብረ_ዳሞ፥ #ደብር_ማርያም #አቤር #አቡነ_ሰላማ ገዳም በገመድ የሚወጣበት ገዳም ነው፤
#በተራራማና በተፈጥሮ የተዋበና በተፈጥሮ ቅርጽነቱ ባለ ሦስት ማዕዝን ክብ ተራራ ነው፤
#የተራራው ርዝመትም 28ሜትር ነው፡፡
#ገዳሙ ከአዲግራት ደቡብ ምዕራብ በ27ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
#በወቅቱ ከገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ቀጥሎ ጥብቅ ሥርዓት የነበረበት ታላቅ ገዳምም ሆኖ ነበር፡፡
#ጻድቁ በአንዶ አማካይነት ተራራውን ሲወጡ የረገጡበት የእግር ጣታቸው ምልክት ያለበት ዐለት ይገኛል፤
#እናቶች ምጥ ሲይዛቸው፥ ሰዎች ሲታመሙ የሚፈውስ፥ ድርቅና ችግር ሲፈጠር ምሕረት የሚያወርድ፥ የተጣሉ ሰዎች የሚታረቁበት #ነባኢ_መስቀል (አልቃሽ መስቀል) የሚገኝበት ነው፤
#ክረምት ከበጋ የማይደርቁና ፈውስን የሚሰጥ ጠበል ያለበት ቦታ ነው፡፡
ጻድቁ #ጥር_29_ዕረፍታቸው_ሲሆን፤ የከበረ አጽማቸው በገዳመ ደብረ ኀረይክዋ ከአንድ ቋጥኝ በተጠረበ ሦስት መዓዝን ባለው ድንጋይ ታትሞ ይገኛል፡፡
**ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘተሰብሐ ወተወደሰ፤
በአፈ አምላክ አሚነ ወዕበየ ስብሐት ዘለብሰ፡፡
ገብረ ናዝራዊ እትናበብ ማኅሌተከ ሐዲሰ፤
አፉየ ምላእ እግዚኦ ማኅሌታዌ መንፈሰ፤
ወተናብቦትየ ረሲ ንባበ ቅዱሰ፡፡
/#ዋልድባ_ዋሊ/

❤5👍4
#ማኅበረ_ዴጎ (ዶጌ) /#ማኅበረ_ጻድቃናት)፤ #ጥር_29_ቃል_ኪዳን_የተቀበሉበት፤ #ጥር_30_ምስዋሮን_በተባለ_ቦታ_የተሰወሩበት_ዕለት_ነው፡፡
ማኅበረ ዴጎ ማለት የደጋጎች ሀገር ማለት ሲሆን የተባለበት ምክንያትም ቅዱሳን ስላሉበት ነው፡፡ በ365 ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ‹‹ ሮምያ›› ከምትባል መንደር የቅዱስ መጽሐፍ ቃል የሆነውን መሠረት አድርገው፤ 1ኛ ‹‹ ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የነርሱ ናትና›› ያለውን 2ኛ ‹‹ አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ብሎ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን አንብበው የዚህን ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው ሃገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡
እነዚህም በአኵሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጢን በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው ለዚሁ ለዚሁማ ከሀገራችን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በጾም በጸሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት ብለው ሱባዔ ገቡ ጾም ያዙ፡፡
ከሱባዔው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልፃ ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው በዚያም በጾምና በጸሎት ፀንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡
ሦስት ሺህ/3000/ ያህሉ ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሄዱ፡፡ ከነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር፣ ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡
ተጨማሪ ሦስት ሺ ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋርም ተደመሩ፡፡ ከዚያም የቅዱስ ጳውሎስና የቅዱስ ዮሐንስ መመሪያ ተከትለው ማለት ‹‹ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል›› የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ፀንተው በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማኅበር መጠጣት ጀመሩ፡፡ የማኅበረ ዴጎ ታሪክም ተቀየረ ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ነዳይ ድሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ፡፡ ከእነርሱ ጋርም አንድ ማኅበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃችው፣ እነርሱም ፈቀዱለት እና አንዱ የማኅበሩ አባል ሆነ፤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ፡፡ በዚሁ ጊዜ ‹‹እስቲ ለኔም ተራ ስጡኝ እንደአቅሜ ዝክር ላውጣ፡፡›› አላቸው፡፡ በዚህ ግዜ ግን ድህነቱን አይተው ‹‹አይሆንም አንተ ድሀ ነህ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህና ነው የምትደግሰው ይቅርብህ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹አይሆንም ስጡኝ እንጂ›› አላቸው እነርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡
ከማኅበርተኞቹ መካከል አሳላፊ ወይም ሙሴ ‹‹ሣይዳ ›› የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው እንግዳና ድሀ ሰው ፈጽሞ አይወድም ነበርና ጌታችንም ከማኅበርተኞቹ መካከል ሲገኝ ደሀ መስሎ ስለነበር በጣም ይጠላው ነበር፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከነርሱ ጋር ሲቀመጥም አንድ ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፡፡ የሆኖ ሆኖ የጌታችን ማኅበር መድረሱ አልቀረም ደረሰ፡፡ እንደማኅበሩ ሥርዐት የወይን ጠጅ የሚጠመቅባቸውን ጋኖች የሚያጥበው ሙሴው /አሳላፊው/ ነው፡፡ ስለሆነም በሥርዐቱ መሠረት ጌታችን ሙሴውን ጠርቶ ጋኖችን እጠብልኝ አለው፡፡ አሳላፊውም በቁጣ ‹‹አንተ ቤትህ የማይታወቅ፤ ከየት አምጥተህ ማኅበር ልታደርግ ነው አንተ ብሎ›› በማለት አናንቆ አልታዘዝህም ብሎ ሄደ፡፡ ይህን የተመለከተው ጌታም አንድ እረኛ ጠርቶ ‹‹አንተ ልጅ ከብቶችህን እኔ እጠብቅልሃለሁና በዚህ ውሀ አምጣልኝ›› አለው፡፡ ትንሹ እረኛ ልጅ ገምቦውን ይዞ ትንሽ ወጣ እንዳለ ጌታ ዘወትር በሚቀመጥበት ድንጋይ ላይ ሆኖ ዘንጉን ወደ ልጁ አቅጣጫ ወረወረው፣ ዘንጉንም ከልጁ ፊት ሂዶ ተተከለ፡፡ ልጁንም ጠርቶ ዘንጉንም እንዲነቅለው አዘዘው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ዘንጉንም ቢነቅለው ውሀ ፈለቀ፡፡ ከርሱ ቀድተህ አምጣልኝ አለው፡፡ ልጁም ከዚህ ውሀ ቀድቶ አመጣለት ጋኖቹን አጠባቸው፡፡
በበዓሉ ቀን ማህበርተኞቹ ምን ሊያበላን ነው፣ ምን ሊያጠጣን ነው ሳይሉ ኹሉም ተሰበሰቡ፡፡ ጌታችንም በፊታቸው ጋኖቹን ቢባርካቸው የወይን ጠጅ ሞልተው ተገኙ፡፡
ቀድቶ ቢሰጣቸውና ቢቀምሱትም በጣም ግሩም ጣፋጭ ስለነበር እጅግ አደነቁ፡፡ እነርሱም ጌታን ከጻድቃን አንዱ ስለመሰላቸው ከእግሩ ላይ ወድቀው እስካሁን ድረስ ሳንበድልህ አልቀረንምና ይቅር በለን ብለው ለመኑት፡፡ ተነሱ ብሎ ካስነሳቸው በኋላ እናንተ ምንም አልበደላችሁም የጠየኳችን እድርጋችኋል የበደለኝ ግን አሳላፊው ነው በማለትና አንድም ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ አልሰጠኝምና አፈራርዱኝ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሙሴው/አሳላፊው/ የማያፍር ደፋርና ርጉም ስለነበር ‹‹ይህ ሰው ጌታችን በልቶ አልበላሁም ፣ ጠጥቶ አልጠጣሁም የሚል ስለሆነና ስለማይጠግብ ነው እንጂ እንዲያውም ለናንተ አንድ አንድ ዋንጫ ሲሰጣችሁ ለእርሱ ሁለት ሁለት ነበር የሚሰጠው ብሎ የሐሰት ቃል መለሰ፡፡
ጌታችንም እንግድያስ እኔ የጠጣሁበት ዋንጫ ትቅረብና ትመስክርብኝ አለው፡፡ በዚሁ ተስማምተው አሳላፊው/ሙሴው/ ሄዶ አንድ ሸራፋ ዋንጫ አምጥቶ በዚህ ነበር የሚሰጠውና የሚጠጣው ብሎ አቀረበ፡፡ ዋንጫዋም ከተቀመጠችበት አንድ ክንድ ከስንዝር ተነስታ ጽዋይቱን ስትመሰክር ‹‹ዓለማትን የፈጠረ አምላክ ምስክሬ ነው እኔ የያዝኩትን የወይን ጠጅ ዕቃ ሙሴም በእጆቹ አልያዝኩትም በከንፈሩ አልነካኝም በሌሎቹ ሰዎች እጅ ግን ተይዤ ያየን ነበር›› አለች ያን ጊዜ እንደ ዳታን እና አቤሮን ምድር ተከፈተችና ሙሴውን ከነልጁ ዋጠቻቸው፡፡
ማኅበረ ፃድቃንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ተረድተው እንደገና ከእግሩ ወድቀው ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ለመኑት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታ ካደረገላቸው በኋላ ስማችሁ የጠራ በስማችሁ ተዝካር ያወጣ በስማችሁ ድሆችን የረዳ፣ ያለበሰ፣ ያጎረሰ፣ የሰጠ፣ የመጸወተ፣ ቤተ ክርስትያናችሁን የሠራ፥ ያሠራ፣ እሰከ 14 ትውልድ ደረስ ምሬላችኋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይህችን ቦታችሁ መጥቶ የሳመ እየሩሳሌም እንደሳመ አድርጌላችኋሁ አላቸው፡፡
በኦሪት ሔኖክ፣ ዕዝራ፣ ኤልያስ፤ በሐዲስ ኪዳንም እነ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና በየጊዜውም እንደሚሰወሩ ቅዱሳን እንደዚሁም ጌታችን እነዚህን የማኀበረ ዴጎ ጻድቃንንም ከሞት ተሰወሩ ብሎ በበነጋታው ጥር 30 ቀን ሠውሯቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ይህ ታላቅ በዓል ሆኖ ዛሬም በየዓመቱ ጥር 30 ቀን በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ይኖራል፣ ይከበራልም፡፡
በገዳመ ዴጎ በዓይን የሚታዩ፥ በእጅ የሚዳሰሱ ተአምራት የታየባቸውና የተደረገባቸው ንዋያት እስካሁንም አሉ፡፡ ወደ አኵሱም ስትሄዱ ታዩት ዘንድ እንጠቁማችሁ፡፡
1. ጌታችን የተቀመጠበትንና የቆመበትን ድንጋይ ከነምልክቱ
2. ምስዋሮም የሚባል ጻድቃኑ የተሰወሩበትን ስፍራ

👍7❤3
3. ከድንጋይ ላይ ሁኖ ወርቅ ዘንግ ወርውሮ ያፈለቀው ማየ ጸሎት ማየ ዮርዳኖስ ብሎ የሰየመው
4. ቁመት ጨምራ ከመሬት ተነስታ እንደ ሰው አፍ አውጥታ የመሰከረችው ዋንጫ
5. ጻድቃኑ ይወቅጡበት የነበረ የድንጋይ ሙቀጫ
6. በማኅበራቸው ጊዜ ሲደግሱባቸው የነበሩ የድንጋይ ገበታዎች
7. ከሀገራቸው ከሮም ያመጡት ባለመስታወት ቋሚ ዕፀ መስቀል፡፡
8. ርዕሰ ዮሐንስ የሚባል ነገሥታት ከነዘውዳቸው፥ ጳጳሳት ከነአክሊላቸውና ከነመስቀላቸው በዚያን ጊዜ የተሳሉበት ስዕል፡፡
9. ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በማህበረ ፃድቃን ዴጌውን ሆኖ ያስተማረበትና የጠመቀበትን በስዕል የሚያሳይ፡፡
10. ይህ ገዳም በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት እንደተገደመና ገዳሙ ራሳቸው የገደሙት የራሳቸው መሆኑን በአክሱም መጽሐፍ ክብረ ነገሥት ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡
መልክኦሙ ለጻድቃን ዘዴጎ፤
ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘሐዋዝ ጥቀ፤
ለዘይሰምእ በእዝኑ ወበኅሊናሁ ጥንቁቀ::
ጻድቃን ዘዴጎ እበይክሙ ተአውቀ፤
እመ በትህትና ማእከሌክሙ ረፈቀ፤
ሊቀ ጠቢባን ክርስቶስ ዘይሜህር ጽድቀ፡፡
(ምንጭ፤ በዋሊ ጉዞ ላይ የገዳሙ አባቶች በቃል ያስረዱን፣ የብሥራት ዕይታ፣ ማኅበረ ዴጎ የምትል ትንሽ መጽሔት)

❤6👍4