Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑራኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡
በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤
1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል
2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል
3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/
4ኛ) አዲስ አበባ አዲስ ሰፈር አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቁ ዮሐንስና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ.ክ. (ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ
5ኛ) ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን)
6ኛ) ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን)

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
👍147🥰1
#ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25
፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ#በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡
፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡

፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡
፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡
፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡
፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡

#ሰላም_ለዝክረ_ስምከ_ዘይትበደር እምብሩር፤
ወይጥዕም እም ሶከር፡፡
ሰባስትያኖስ ንጹሕ ትሩፈ ምግባር፤
በዝክረ ስምከ ተማኅጸንኩ ኢትኅድገኒ ለገብር፤
አመ ትወፅዕ ነፍስየ እምሥጋ በግብር፡፡

#ሰላም_ዕብል_ለፍጽምከ_መአድም
በስመ ሥላሴ ኅቱም፡፡
ሰባስትያኖስ አቡየ ሰላም ሰላም፡፡
በፍጽምከ ተማኅጸንኩ ኢይቅርበኒ ሕማም፤
ማዕተበ ፍጽምከ በፍጽምየ ሢም፡፡

#ሰላም_ለመልክዕከ_ዝብጠታተ ኀጺን ዘተወክፋ፤
ወትዕግስታተ አዝለፋ፡፡
ሰባስትያኖስ ጻማዊ ሱታፌ ሕማሙ ለዘልፋ፤
መልክዐ ገጽከ ኀበ ተጽሕፋ፥ ለመለክዕየ ጸሐፋ፤
ውስተ ምዕራፍከ ረሲ ምዕራፋ፡፡

**ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡
#ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡
#ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡

(የስብስትያኖስ ቤተ ክርስቲያን ከአዴት በተጨማሪ ያለበትን ጠቁሙን ቢቻል በፎቶ ጭምር፤ አዴት አካባቢ የምትገኙ የፈትለ ሥላሴን ገዳም ፎቶ ላኩልን)
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
6👍4🤝1
#በአዲስ_አበባ_በብቸኝነት_እንደ_ደብረ_ሊባኖስ_ገዳም_በየቀኑ_ውዳሴ_ማርያም_በዜማ#ክስተተ_አርያም_በዜማ#መስተጋብዕ_በዜማ_የሚያደርሰው_ደብራችን_ደብረ_ሰላም_የዜማ_ትምህርት_የተጀመረበትን_ ፴፪ኛ #ዓመት_ጥር_18 (24) 2017 ዓ.ም. አክብሯል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን የምታስምራቸውን ትምህርቶች በዘርፍ በዘርፍ ከፍላ ነው የምታስተምረው፤ እነዚህም የፊደል ቤት፣ የንባብ ቤት፣ የዜማ ቤት (ከሰላም ለኪ ዜማ ጀምሮ ውዳሴ ማርያም፣ ሰዐታት፣ ቅዳሴያት፣ ምዕራፍ፣ ድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋስዕት፣ አቋቋም፣….)፣ የቅኔ ቤት፣ የትርጓሜ ቤት፣ የቊጥር (የአቡሻኽር) ቤት ብላ በመክፈል ነው፤ ከእነዚህ ትምህርቶችም አብዛኞቹ በደብራችን የሚሰጡ ቢኾንም፤ የዓለማዊ (የአስኳላ) ትምህርት በእጅጉ እየተስፋፋ በመጣባቸው ዘመናት (ከ1960-1980 ተማሪዎች በቀኑ መርሐ ግብር የዓለማዊ (የአስኳላ) ትምህርት ስለሚማሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የሚማሩበት ጊዜ አጥተው፤ ደብራችንም በአዲስ አበባ ከሚገኙ አድባራትና ገዳማት ሰፊ አጥቢያን የሚያቅፍና የብዙ ሊቃውንት መኖሪያ እንደመኾኑ መጠን ከአጥቢያው የሚወለዱ ተተኪ እንደሚፈለገው መጠን ሳይኾን እስከ 1985ዓ.ም. ዘልቆ ነበር፡፡
ይህንን ችግር በውል የተረዱት ቄሰ ገበዝ መርሐ ጽድቅ ኃ/ጊዮርጊስ በቀኑ መርሐ ግብር የአስኳላ ትምህርታቸውን ለሚማሩ ተማሪዎች በማታው መርሐ ግብር የንባብና የዜማ ትምህርትን በራሳቸው ተነሳሽነት ‹‹ዘነሳእክሙ በጸጋ፥ ሀቡ በጸጋ›› የሚለውን ሲማሩ ያደጉትን የወንጌል ቃልና፤ ቀደሞውንም የተማሩት ከታላቁ ሊቅ አለቃ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል በመኾኑ፤ የወንጌልን ቃልና የመመህራቸውን አሠረ ፍኖት ተከትለው ያለምንም ደመወዝ በመቃብር ቤት ማስተማር ጀመሩ፤ እነኾ ዘንድሮም ማስተማር ከጀመሩ 26 ዓመታትን አስቈጠሩ፤ በእነዚህ ዓመታትም ከ850 በላይ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ አብዛኞችንም እስከ ዲቁናና ቅስና ማዕርግ ያበቁ ትጉህና ታታሪ መምህር ናቸው፤ ማታ ማታ ከ12፡30-3፡00 ለ32 ዓመታትም ተማሪዎቼን ማስተማር ይበልጥብኛል ብለው ብዙ ነገሮችን (ማኅበራዊ ጉዳዮችን ሳይቀር) ትተው እያስተማሩ ያሉ ታላቅ መምህራችንም አባታችንም ናቸው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤታችንም ላፈራቻቸው ዲያቆናትና ቀሳውስት ትልቁን አስተዋጽዖ ያደረጉት እኒሁ መምህር ናቸው፡፡ ስለ መምህራችንም የቱን ተናግረን እንዘልቀዋለን!! ወደፊት የእርሳቸውን የሕይወት ልምድ፣ ምክር ይዘን የምንቀርብ መኾኑን እንገለጽን፤
የዜማ ትምህርቱ ከዛሬ ከ32 ዓመታት በፊት በ1985ዓ.ም. በመቃብር ቤት በመመህራችን በቄሰ ገበዝ መርሐጽድቅ ኃ/ጊዮርጊስ (ከ10-15 በሚጠጉ ተማሪዎች /ለአብነትም ሸዋረጋ አዳነ፣ ሚሊዮን ከበደ፣ አዲስ ወርቅ ደበበ፣ ደረጀ ተክሌ፣ በላይ አዳነ፣ መሳፍንት አለማየሁ፣ …./ ተነሳሽነት የተጀመረ ነው፡፡
በመቀጠልም ተማሪው እየበዛ በመምጣቱ የዜማ መማሪያ ቦታው (መቃብር ቤቱ) ባለመቻሉ ወደ ደወል ቤት መጣ በቅቱም ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በግምት 120-125 ይጠጉ ነበር (በወቅቱ ይማሩ ከነበሩት ውስጥም ለአብነት ያህል ቴዎድሮስ አዳነ፣ ዮሐንስ ደምሴ፣ ወንድይፍራው ጌታቸው፣ ፍስሐ አዱኛ፣ ተፈሪ ተስፋዬ፣ ሰብስቤ ተክለማርያም፣ ዘለዓለም ተረፈ፣ ዘካርያስ አለማየሁ፣ መልአኩ ገብረሥላሴ፣ (አቡሽ) ገብረሥላሴ፣ ቃልአብ አለማየሁ፣ ሔኖክ አለማየሁ፣ ሚሊዮን እሸቱ፣ ዐሥራት ለይኩን፣ ሚሊዮን ለይኩን፣ ተክሉ ተዋበ፣ ፣ ተስፋዬ ገብረሥላሴ፣ ደሳለኝ ገብረ ሥላሴ፣ ምሕረቱ አዳነ፣ በልሁ ሰሎሞን፣ ጥበቡ መኮንን፣ ከተማ ወርቅአለማሁ፣ ቡሩክ አድማሱ፣ ደርብ ወርቁ፣ ዐሥራት ማሙዬ፣ ዐቢይ አለማየሁ፣ ግሩም መልአኩ፣ አበባየሁ ዕንቈ፣ ጌትዬ ዕንቈ፣ ዳንኤል ገብረ ሥላሴ፣ ካሣ ፍቅሩ፣ አፈወርቅ ማሞ፣ ጸጋ ዘአብ ማሞ፣ ስንሻው ውብአየሁ፣ ይስሐቅ ውብአየሁ፣ ስዩም አስቻለው፣ ናርዶስ ንጉሤ፣ አቡሽ ጌታቸው፣ ………… ይገኙበታል፤ አብዛኛው ተማሪዎችም የማርገጃ አካባቢ ልጆች ነበሩ፤ በአብዛኛው የአካባቢ ተወላጆች ዲያቆናትን ደብሩ ያፈራበት ዘመን ነበር፤ ለዚህም የዜማ ትምህርቱ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡
ከደወል ቤት ቀጥሎ የመማሪያ ቦታው ወደ ወንዶች መጠለያ (ገረገራ)ና በመሃል ላይ ወደ ደብሩ የአብነት ትምህርት ቤት እየተዘዋወረ ትምህርቱ ሲሰጥ ቆይቷል፤ በዚህ ወቅትም ከ105-110 የሚጠጉ ተማሪዎች ሲኾኑ፤ በወቅቱ ከተማሩ ተማሪዎች መካከልም መስፍን ለገሠ፣ ስመኘው ጌትዬ፣ ዮሐንስ ጌትዬ፣ ዘካርያስ ጌትዬ፣ ሱራፌል አውግቸው፣ ወንድወሰን ሺፈራው፣ ኢሳይያስ ቦጋለ፣ ያሬድ እንደሻው፣ ….. ይገኙበታል፤ በዚህ ወቅትም ከማርገጃ አካባቢ በተጨማሪ ከሌሎች የደብሩ አጥቢያዎች (ከቀጨኔ፣ ከሰሜን፣ ከችሎት፣ ከ20ቀበሌና ከመነን) መጥተው ተማሪዎች መማር የጀምሩበት ነበር፡፡
አሁን ባለንበት ጊዜ ደግሞ በቋሚነት በወንዶች መጠለያ (ገረገራ) ትምህርቱ እየተሰጠ ይገኛል፤  በአሁኑ ወቅትም በፊት ወንድሞች ይማሩ የነበረው ይህ የማታ የዜማ ትምህርት እኅቶችንም ያካተተ ሁኗል፡፡ አሁን ባለበት የዜማ ትምህርት ሒደት ከምሽቱ 12፡30 ላይ ውዳሴ ማርያም በዜማ፥ ክስተተ አርያም በዜማ፤ እንዲሁም መስተጋብዕ በዜማ ከደረሰ በኋላ የትምህርቱ መርሐ ግብር እስከ ምሽቱ 2፡30 ድረስ ይካሔዳል፤ ከ32 ዓመታት በፊት የዜማ ትምህርቱ በተጀመረበት ወቅት ግን መርሐ ግብሩ ላይ ይደርሱ የነበሩት የዜማ ይዘቶች አሁን የሚደርሱት እንዳሉ ሁኖ ሌሎች የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶችም የሚጨምር ነበር፡፡
ይህ የዜማ ትምህርት ከቀድሞ የወረሰውን የፍልሰታ ልዩ የሱባኤ የጸሎት መርሐ ግብር እና የደብረ ታቦር ዝክርን፤ አሁንም ሳይቋረጥ አሁን በመማር ላይ ያሉ፣ ከዚህ በፊት የተማሩና የደብሩ ማኅበረ ካህናትና ዲያቆናት በአንድነት በመኾን ሱባኤውንና የደብረ ታቦር ዝክሩን አጠናክረው የቀጠሉበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
11👍1😢1