#ጥምቀት_በኢትዮጵያ፤
፠ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀው የንግሥት ሕንደኬ በጅሮንድ አቤላክ(ባኮስ) ‹‹እነሆ ውኃ አለ፣ ታድያ መጠመቅን ማን ይከለክለኛል?›› /የሐዋ. ፷፥፳፱-፴፮/ ብሎ በሐዋርያው ፊልጶስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ሥርዐት ግን ተስፋፍቶ የቀጠለው በነገሥታቱ በአብርሃ ወአጽብሐ (315-351ዓ.ም.) የቤተ መንግሥቱ ጃንደረባ በነበረውና ኋላ ጳጳስ በሆነው በፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ) ዘመን ነው፡፡ በዓሉ ግን አሁን በምናከብረው ዓይነት ስዕላዊ በሆነ መልኩ መከበር የጀመረው ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ዜማ መስፋፋት ጋራ በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (530-544ዓ.ም.) እንደሆነ ይነገራል፡፡
፠ ገዳማቱና አድባራቱም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የውኃ ምንጮች በተናጥል በመውረድ በዓለ ጥምቀትን ያከብሩ ነበር፡፡ ተቀራርበው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያሳድሩ ዐዋጅ የታወጀው፥ ትእዛዝ የተላለፈው በጻድቁና በጠቢቡ ንጉሥ ላልይብላ(1140-1180ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በዚሁ ዘመን የነበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአኵሱም በመቀለና በመርጡለ ማርያም ያሉ ጥምቀተ ባሕሮችን ባርከዋል፤ በአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን ደግሞ በአቡነ ተክለሃይማኖት አሳሳቢነት ሥርዐተ ጥምቀቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዐዋጅ ታውጇል፡፡ እስከ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስም ታቦታቱ ዕለቱን ጠዋት ወጥተው ማታ መለሱ ነበር፤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ታቦታቱ በዋዜማው ጥር 10 ከሰዐት በኋላ ወደ ትምቀተ ባሕር ወርደው እንዲያድሩ፤ አገሩንም በኪደተ እግር እንዲባርኩ፤ በሄዱበት መንገድም እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ቀጥሎም አፄ ናዖድ ሕዝቡ ታቦታቱን አጅቦ ወደ ጥምቀተ ባሕር እንዲሄድ በዐዋጅ አስነገሩ፡፡ ይህ ሥርዐትም እስካሁን ከኛ ዘንድ ደርሷል፡፡ በዘመናት ውስጥም የጥምቀት በዓል ሲከበርባቸው ከነበሩ ቦታዎች ዐበይቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤
#በአኵሱም_የንግሥተ_ሳባ_መዋኛ_ ‹‹#ማይ_ሹም››
#በጎንደር_የአፄ_ፋሲል_መዋኛ_ገንዳ
#በቅዱስ_ላሊበላ_የዮርዳኖስ_ወንዝ
#በሸዋ_የአፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_ፍርድ_መስጫ_አደባባይ
#44ት #ታቦታት_የሚያድሩበት_የሸንኮራ_ሜዳ ‹‹#ኢራንቡቴ_ጥምቀተ_ባሕር››
#በአዲስ_አበባ_የጃንሆይ_ሜዳ_ (ጃንሜዳ)
#በአዲስ_አበባ_የእንጦጦ_ማርያምና_ቅዱስ_ራጕኤል_ታቦት_ማደሪያ #ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ ዐበይቶቹ ናቸው፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤2👍2