Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.4K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እና አካባቢው - 1951 ዓ.ም

ኢቲሳ በሰሜን ሸዋ በቀድሞው ቡልጋ አውራጃ የሚገኝ እና ከ800 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ በ1215 ዓ.ም አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ታሪካዊ ቦታ ነው።

University of Monash/Asian Collections/Forsyth, Elliott Christophe Photographs:
https://repository.monash.edu
20👍7🥰3👏3
#ታኅሣሥ ፳፱፤ #ልደተ_እግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_፡፡
#በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_ #የጌታችን_ልደት_የበዓለ_ወልድ_የገና_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፵፯ ገዳማትና አድባራት፡፡
(ያልጠቀስናቸው ካሉ አሳውቁን)
#ዮም_ተወልደ_ መድኀኔ_ዓለም፤ #ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም#ዮም_ተወልደ_ከሣቴ_ብርሃን፡፡
✧ ክብረ በዓሉ የሚከበርበት ምክንያት፤ የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት፤
ልዩ ማስታወሻ፤ ከቅዱሳንም ሆነ ከእመቤታችን በላይ የጌታችን በዓል ከዋለ የጌታችን በዓል በዋነኛነት ስለሚከበር፤ ጾምም ከሆነ ጾሙ ቀርቶ በዓል ስለሚደረግ፤ በዓላቸው በዚህ ቀን የኾኑ ቅዱሳን በዓላቸው በሌላ ቀን ቅያሬ ሲከበር ነገር ግን በቦታቸው ላይ የጌታችን ልደት በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡
✧ ነገር ግን የጌታችን ልደት፤ ከ9ኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት አንዱ በመኾኑ፤ በሁሉም ገዳማትና አድባራት ዋይዜማ ተዚሞ፥ ማኅሌት ተቁሞ፥ ሰዐታት ተቁሞ፥ ኪዳን ተደርሶ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ ይከበራል፡፡

#በመዲናችን_በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_#ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. አዲስ አበባ መካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ (አዲስ አበባ ላይ በ1883 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ነገር ግን ታቦቱ ቀድሞ የነበረና ከ600 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው)
አድራሻ፤ አራዳ ከተማ ክፍለ ከተማ፤ 4ኪሎ
ታክሲ፤ ከፒያሳ → አራት ኪሎ

፪. ለቡ ደብረ ታቦር በዓለ ወልድና አበ ብዙኃን አብርሃም ገዳም
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ለቡ
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ለቡ

፫. ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤ/ክ
አድራሻው፤ ሐና፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሐና፡፡

፬. አንቀፀ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (የቅዱስ ላሊበላ ታቦት በድርብነት ይወጣል)
አድራሻ፤ የካ_ክፍለ_ከተማ፥ ራስ ካሣ
ታክሲ፤ ከ4 ኪሎ → ፈረንሳይ → አንቀጸ ምሕረት (ራሳ ካሣ ሚካአል)

፭. ፊሊዶሮ መድኀኔዓለም ቅዱስ ላሊበላ፡፡
አድራሻው፤ ፊሊዶሮ፡፡
ታክሲ፤ ከመርካቶ → ኮልፌ(ፊሊዶሮ)፡፡

፮. አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕትና ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ገብርኤል
አድራሻው፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ሳሪስ አዲስ ሰፈር፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሳሪስ አዲስ ሰፈር፡፡

፯. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል (ቅዱስ በዓለ ወልድ በድርብነት ይከብራል)
አድራሻው፤ መካኒሳ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → መካኒሳ

፰. ኮልፌ ቀራንዮ (ታቦት ማደርያ) ደብረ ተአምራት ዳግማዊ ጻድቃኔ ማርያም፡፡ (ቅዱስ በዓለ ወልድ በድርብነት ይከብራል)
አድራሻ፤ ዘነበወርቅ ታቦት ማደሪያ ጀርባ፤ ከዘነበወርቅ ወደ ታቦት ማደሪያ በሚወስደው መንገድ ላይ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃይሎች → ዘነበ ወርቅ፡፡

#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_፳፩ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ቤተልሔም፥ እስራኤል፥ ኢየሩሳሌም (ጌተችን የተወለደባት)
አድራሻ፤ እስራኤል፥ ኢየሩሳሌም፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ (በአውሮፕላን) → እስራኤል

፪. ማኅበረ ሥላሴ ገዳም (የሺዎች ገዳም)፤ (ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ በተወለደባት ዕለት የጌታችን መወለድ በኢትዮጵያ የተበሠረባት)
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ቋራና (መተማ)
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ጎንደር → ሸዲ/መተማ/

፫. ደብረ ሮሐ ላስታ ቅዱስ ላሊበላ (ዳግማዊት /አምሳለ/ ኢየሩሳሌም)
አድራሻው፤ ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ላስታ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ

፬. መንበረ ልዑል ደብረ መጕና አቡነ አብሳዲ ወቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወማኅበረ በኵር ገዳም፡፡
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥
ትራንስፖርት፤ ከጎንደር ከተማ → ዳንሻ መስመር ላይ → በበው /አሸሬ/ የምትባል መንደር ላይ ተወርዶ → የእግር ጕዞ

፭. ዞዝ አንባ አቡነ አብሳዲ (ቅዱስ ላሊበላ ከፈለፈላቸው አንዱ)
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ በለሳ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ማክሰኚት → በለሳ (ዞዝ አንባ)

፮. ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አድራሻ፤ ጉራጌ ስልጤ ሃገረ ስብከት፥
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ምደረ ከብድ

፯. ዲጎ ኢየሱስ፡፡
አድራሻ፤ ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ወልድያን አልፎ፥ ዶሮ ግብር፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ወልድያ፡፡

፰. ገሀ ኢየሱስ፤ (ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥)

፱. ኬላ ኢየሱስ፤ (ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥)

፲. ደንቀዝ ኢየሱስ፡፡
አድራሻ፤ ጉራጌ ስልጤ ሃገረ ስብከት፥
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ምደረ ከብድ

፲፩. ርዕሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ ቤ.ክ.፤ /ጽላቱ ከደበቡ ኢትዮጵያ የሄደ፥ እጅግ ጥንታዊ ታሪክ ያለው፥ ኋላ ላይ ቊጥሩ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነ/
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አራዳ፥ ጃንተከል ወርካ ጋር
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር

፲፪. እስቴ መካነ ኢየሱስ
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ እስቴ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እስቴ፡፡

፲፫. ደብረ ታቦር ኢየሱስ
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደቡብ ጎንደር ከተማ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ታቦር፡፡

፲፬. ብራ ኢየሱስ (ብራ ታዴዎስ)፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ወገራ፥ አምባ ጊዮርጊስ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → አምባ ጊዮርጊስ፡፡

፲፭. ደብረ ስብሐት ቀሃ ኢየሱስ፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ፤ የጎንደር ላይ ቤት አቋቋም ትምህርት ቤት ማስመስከርያ)
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ጥምቀተ ባሕሩ አጠገብ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር

፲፮. መንደረ ኢየሱስ
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ አዴት፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር በሞጣ መስመር(አዴት)

፲፯. ጃንገበር ኢየሱስ
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ አዴት አጠገብ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር በሞጣ መስመር(አዴት)

፲፰. ሰንቀኛ በዓለ እግዚአብሔር፤ (ባሕር ዳር በሞጣ መስመር(አዴት)

፲፱. ሺገዢ ኢየሱስ፤ ባሕር ዳር በሞጣ መስመር(አዴት)

፳. አለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ (በድርብነት ይከብራል)፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት ፥ አለም ገና
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → አለም ገና፡፡

፳፩. ገፈርሳ(ታጠቅ) በዓለ ወልድ ወአቡነ ሳሙኤል ወአቡነ ኪሮስ፤
አድራሻው፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ገፈርሳ
ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ታጠቅ ወይም መናገሻ የሚል ትራንስፖርት ይዘው ገፈርሳ ድልድዩ ጋር በዓለ ወልድን ያገኛሉ፡፡

፳፪. አሸዋ ሜዳ ቤሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያን፤
አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት ፥ ወልመራ ወረዳ፥ (አዲስ ዓለም አካባቢ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → አምቦ (አዲስ ዓለም)

፳፫. ቂልጠፋት በዓለ ወልድ
አድራሻ፤ ጉራጌና ስልጤ ሃገረ ስብከት፥ እንደጋይ ወረዳ
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ጉራጌ

፳፬. ጉንችሬ በዓለ ወልድ፤
አድራሻ፤ ጉራጌና ስልጤ ሃገረ ስብከት፥ እነሞር ወረዳ)
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ጉራጌ
👍52
፳፭. ሆሳዕና ደብረ ምሕረት ቅዱስ በዓለ ወልድ፤
አድራሻ፤ ጉራጌ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ሆሳዕና

፳፮. ቡኢ ደብረ ሰላም በዓለ ወልድ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ደቡብ ሃገረ ስብከት፥ ቡኢ፤
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ → ቡኢ

፳፯. ባሕር ዳር በዓለ ወልድ (በዐለ እግዚአብሔር) ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ባሕር ዳር ሃገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፥ ቀበሌ 13፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡

፳፰. ወለንጪቲ ጨመሪ በዓለ ወልድ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ወለንጪቲ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ወለጪቲ፡፡

፳፱. ወንዶ ገነት በዓለ ወልድ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ሳዲማ ሃገረ ስብከት፥ ወንዶ ገነት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ወንዶ ገነት፡፡

፴. ደብረ ምሕረት ዱና በዓለ ወልድ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ዱና፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አውቶቡስ ተራ → ዱና፡፡

፴፩. ደብረ ገነት በዓለ ወልድ ቤ.ክ.፤
አድራሻ፤ ሃገረ ስብከት፥ ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አውቶቡስ ተራ → ደብረ ገነት፡፡

፴፪. ጫንቋ በዓለ እግዚአብሔር፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ደምቢያ ቆላ ድባ አጠገብ፡፡)
፴፫. ባርጫ ኢየሱስ፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ከቆላድባ አጠገብ፡፡)
፴፬. ገምበራ ኢየሱስ፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ በጯሂትና በጣና አጠገብ፡፡)
፴፭. ጉቢያ ኢየሱስ፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ደምቢያ፡፡)
፴፮. ማክሰኚት በዓለ ኢየሱስ፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ፡፡)
፴፯. ዘንተራ ኢየሱስ፤ (ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ፤ ማክሰኚት፤ በግራኝ በርና በጎንድ ገዳም መሃል፡፡)
፴፰. ደባርቅ በዓለ እግዚአብሔር፤ (ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ደባርቅ ከተማ ወረዳ)

#ከኢትዮጵያ_ውጪ_የሚከበርበት_#ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ደብረ ገሊላ ቅዱስ በዓለ ወልድ ወሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን፤
አድራሻ፤ አሜሪካ ሃገረ ስብክት፥ ሲያትል
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ (በአውሮፕላን)→ አሜሪካን (ሲያትል)

/ #ክብረ_በዓላት #Feasts /
/ #ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches /

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
1