#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት
✤✤ #ፀሐይ_ማር_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_(#ዘገዳመ_ዋሊ_) ✤✤
፠ በሃገራችን በኢትዮጵያ በብቸኝነት በጌታችን የተመሠረተው ገዳመ ዋልድባ፤ ኋላ በአሕዛብ ጠፍቶ ነበርና በ13ኛው ክፍል ዘመን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው በ4ቱም አቅጣጭ በ4 ወንዞች (በሰሜን ተከዜ፥ በምስራቅ እንስያ፥ በምዕራብ ዛሪማ ፥ በደቡብ እንዞና ወይቦ) ዙሪያውን ከልለውና አጥረው ያስባረኩ አባት ናቸው፡፡
፠ አዲስ አበባና አካባቢውን ከ700ዓመታት በፊት በአንበሳ እየተጓጓዙ በስብከተ ወንጌል እርሻነት፥ በሥነ ምግባር ማለስለሻነት ያረሱ አባት ናቸው፡፡
፠ ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፣ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት የኾኑ ናቸው፤ ይህንንም ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ40ቀን ዕረፍታቸው በመካነ መቃብራቸው ተገኝተው መልክዓቸውን ደርሰውላቸዋ፤ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው አውስተዋቸዋል፤ እንዲሁም በርካታ ቅዱሳን ደራስያን በየድርሰታቸው አንስተዋቸዋል፡፡
#ክቡር_መምህር፥ #የከበረ_መምህር፤
#መልአክ_ዘበምድር፥ #የምድር_መልአክ፤
#ካህን_ወድንግል፥ #ካህንና_ድንግል፤
#ፍጹም_ንጹሕ_ወልዑል፥ #ፍጹም_ንጹሕና_ልዑል፤
#ትጉህ_ወኅሩይ፥ #ትጉህና_ኅሩይ_የተመረጠ)፤
#ብእሴ_እግዚአብሔር፥ #የእግዚአብሔር_ሰው፤
#ለባሴ_ንጽሕና፥ #ንጽሕናን_የተላበሰ፤
#ወለብሰ_ብርሃናዌ፥ #ብርሃንን_የለበሰ፤
#ዘፈጸመ_ገድሎ_በሠናይ፨ #ገድሉን_በመልካም_ተጋድሎ የፈጸመ፨/ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ/
፠ ከረድአቸው አባ ብንያሚና፤ ከጓደኞቻቸው ከአባ አንበስ ዘሐዘሎና ከአቡነ ዘርዐ ቡሩክ ጋር በመኾን በወቅቱ ከነበሩት ርዕሰ አበው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ለመባረክ ወደ ዝቋላና ምድረ ከብድ የመጡና በረከትን የተቀበሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያስተማሩ ናቸው፡፡
፠ አናታቸው በሥጋ ሞት በሕፃንንታቸው ቢለይዋቸውም፤ በሕፃንነታቸው ጌታችን አውራ ጣቱን አትብቷቸዋል፡፡
‹‹እንዘ ይተግህ ለጸልዮ ወያስተበርክ ለስኢል፤
መንኰብያቲሁ አጠበዎ ወልደ ማርያም ድንግል፡፡
ሳሙኤል፥ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ዘዋልድባ መነኮስ ኀያል፡፡›› /እንዲል ነግሥ/
፠ የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትዕምርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ ፥ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ወደ ወንዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉም ሳይበላሽ ተሸግረዋል፡፡
፠ ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ፤
ⴲ ዝናብ በኾነ ጊዜ ዝሆኖች መጥተው እንደ ጥላ የሚያስጠልሉት፤
‹‹ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤
ጊዜ ርደቶሙ ለዝናማት፤
ዘከለሉከ ነጌያት፡፡›› እንዳለ መጽሐፈ ሰዐታት፤
ⴲ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ (ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት) ጋር መንበረ ጸባዖትን ለ12 ዓመታት አጥነዋል፤ በዚህም በጎንደር ደባርቅ አካባቢ የመሠረቱት ገዳማቸው አብ ጠራ(ህ) በሚል ተሰይሟል፡፡
......................................የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት
‹‹ሳሙኤል አቡነ ትሩፈ ምግባር፤
ዐምድ ጽኑዕ ፀወነ ሃገር፤
ወመልአክ ዘበምድር፡፡›› እንዲል መጽሐፈ ሰዐታት፣
ⴲ በዋልድባ ምድር ላይ ቀድሞ ውኃ የለም ነበርና፤ ፸ የሚጠጉ ምንጮችን በተለያዩ ቦታዎች አፍልቀዋል፡፡
ⴲ ቅዳሴ ማርያምን ወደ መሃል ሃገር ያመጡ፤
ⴲ ቅዳሴ ወውዳሴ ማርያምን ሲደግሙ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ያህል ከፍ የሚሉ፡፡
ⴲ በአናብስት ዘባን ላይ የሚጫኑ፤ መጻሕፍቶቻችውንም በአናብስት ላይ የሚጭኑ፡፡
ⴲ እመቤታችን ነጭ ዕጣን (ስለ ምዑዝ ክህነታቸው) እንዲሁም ዕንቊ (ስለ ንጽህናቸው፣ ቅድስናቸውና ድንግልናቸው) የሰጠቻቸው።
ⴲ በሰኔ 21 ቀን በቀደሱበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆሞ የታየላቸው፡፡
ⴲ ውኃውን ወደ ኀብስት የቀየሩና ከነ ደቀመዛሙርቶቻቸው የተመገቡ፤
‹‹ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፤
ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፡፡
ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ፤
ሥረዪ ኀጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ፤
አስመ ኵሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/
‹‹ …አርአዮሙ ለመምህራን ዐበይተ ኀይላተ፤
እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በኀበ ተአኵተ፥
ወለማይኒ ረሰዮ ኅብስተ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/
የምንኵስና ተወረዱም፤ አባት አባትን ሲወልድ፤ መምህር መምህርን ሲተካ፥ ቅዱስ ቅዱስን ሲያፈራ፥ ገዳም ገዳምን ሲወልድ ነውና ቅሉ፤ የምንኵስና ተዋረዱም፤
፠ ….. ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን፤
፠ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7ቱን ከዋክብት /ፀሐይ አቡነ ሳሙኤልንና ሌሎች ቅዱሳንን/፤
፠ ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ ፀሐይ አቡነ ሳሙኤል ደግሞ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን (አባ ተሥፋ ሐዋርያትን፥ አባ ዘሩፋኤልን፥ አባ ብንያሚን፥ አባ በኪሞስን፥ …… ሌሎች እልፍ አእላፋት መነኰሳትን አምንኵሰዋል፣ ሊቃውንትን አስተምረዋል፤ መምህራንና ደራስያንን ተክተዋል ….፤ በዚህም ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ፥ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት አባ ሳሙኤል በመባልም ይታወቃሉ፡፡
#አቡነ_ሳሙኤል_፤ በአኵስም ከተማ አካባቢ በ1295 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው ዓመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በአኵስም ጽዮን ከነበሩት መምህራን ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ተምረዋል፡፡ ወላጆቻቸው በልጅነታቸው በሞት ተለይተዋቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ሞት በኋላ ወደ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘንድ ሔደው ደብረ በንኰል ገዳም ገቡ፡፡ በዚህም ገዳም እያገለገሉ በወቅቱ ከነበሩት ሊቃውንት የብሉያትና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ሥርዐተ ምንኵስናን ተምረው ከገዳሙ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ከሌሎች 11ድ ወንድሞቻቸው ጋር አብረው መነኰሱ፤ ቆባቸውም እንደ አቡነ አረጋዊ የድንጋይ ቆብ ነበር፡፡ በዚህም ገዳም እህል ሳይበሉ ቅጠል ብቻ እየተመገቡ ይኖሩ ነበር፡፡ እግራቸው እስኪያብጥም ድረስ ይሰግዱ ነበር፡፡
**ኋላ ወደ ጣና ገብተው ከቆብ ወንድማቸው ከአቡነ ያሳይ ጋር ለ12 ዓመታት በሱባኤ ቆዩ፤
**በስተመጨረሻም ጌታችን ወደ መሠረተውና በመሃልም ጠፍ ሆኖ ወደ ነበረው ብዙ ቅዱንን፣ መምህራንን፣ ሊቃውንትንና መናንያንን ወደ ወለዱበት ዋልድባ ገዳም ገብተው ለ70 ዓመታት ያህል ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው፣ ግርማ ሌሊቱን፥ ፀብአ አጋንንቱን ፥ ድምፀ አራዊቱን፥ የሌሊቱን ቊር፥ የቀኑን ሐሩር ታግሠው፣ ረሃቡንና ጽሙን ችለው፣ መላ ዘመናቸውን በጽድቅ ጎዳና ተጕዘው በ1395ዓ.ም ታኅሣሥ 12 ቀን በዋልድባ አቴና ገዳም ዐርፈዋል፡፡
#ባርከኒ አባ እንሣእ ጸሎተከ፤
በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤
አባ ሳሙኤል ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፨ /ጸሎተ መሐረነ አብ/
#በታኅሣሥ ፲፪ በበዓለ ዕረፍታቸው ጊዜም፤ ሮም በጴጥሮስና በጳውሎስ ዕረፍት እንዳለቀሰች፤ ቅድስት ገዳማቸው ገዳመ ዋልድባ (ዋሊ) አልቅሳለች፨
‹‹በከየት ወለሀወት ገዳምከ በሞትከ ዮም፤
ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤
ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ፤
እንዘ አንተ ሰብእ ምድራዊ ወመልአክ ተሠመይከ፤
ካህነ አርያም ሳሙኤል መንበረ ሥላሴ ዘአጠንከ፤
አንበሳ ወነምር ይሰግዱ ለከ፤
ወይልህሱ ጸበለ እግርከ፤
ዕንቈ ወዕጣነ ማርያም አምጽአት ለከ፤
በቅዳሴሃ ሶበ ጸለይከ፤
በከየት ወለሐወት ገዳምከ።>> እንዲል ዚቅ፨
#ታኅሣሥ #፲፪ ፤ #በዓለ_ዕረፍቱ_ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍14❤6
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w