*በጥንታዊው ደብረ ኃይል እንጦጦ ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ፤
*በደብረ ኤልያስ ጎጃም፤
*በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት አለ)
*መካነ ሕያዋን ቅዱስ ኤልያስ ኋላ መካነ ሕያዋን ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል
የተባለ ፤
*በሻሸመኔ ልደታና በሌሎችም የቅዱስ ኤልያስ አድባራትና ገዳማት ይከበራል፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤6👍2👏2
እንኳን አደረሳቹህ | ታኅሣስ 3
#✤ በአታ ለማርያም፤ ✤ በዓለ ሢመቱ ለቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት፤ ዕረፍቱ ለአቡነ ዜና ማርቆስ
እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት(ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው።
**ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች።
ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥ መጠቃቸው፡፡
**ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡
***ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
**ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡
***ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በአታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤
#መቅደሲቱ_ወደ መቅደስ ገባች፤
#ቅድስቲቱ_ወደ ቅድስት ገባች፤
#ክብርቲቱ_ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤
#ልዩ_የሆነችው_ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤
#ቅድስተ_ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤
#ንጽሕተ_ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤
#ቤተ_መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡
**እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
***ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/።
***ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/
***እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡
ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/።
✤#በዓለ_ሢመቱ_ለቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መላእክት፤
#ሰዳዴ አጋንንት ነው፤ /ሄኖክ 10፥8፣ ድርሳን ዘፋኑኤል/
#መጋቤ ድንግል ነው፡፡/ተአምረ ማርያም/
#ማኅሌታዊ ነው፤
#በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ /ሄኖክ 20፥39/
#በአራቱ የዓለም ማዕዘናት ሹም አንዱ ነው፡፡
#ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው /መዝ. 33፥7/
#ካህነ ንስሐ ነው /ሄኖክ 10፥5/
#ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ /2ኛ ነገ. 6፥14/
#ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና፤
#ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና፡፡
✤#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ዜና_ማርቆስ_በዓለ_ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በምድረ ጉራጌ በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም 40 ዓመታትን ሱባኤ የገቡ፤ ምድረ ጉራጌን (ሙሉ ሸዋን ጨምሮ እስከ ደቡብ) እንዲሁም በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ያስተማሩ፤ በርካታ ሊቃውንትን /አባ ጽጌ ድንልንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታን ጨምሮ ሌሎችን ሊቃውንትም/ ያፈሩ ፈርጥ ሲኾኑ፤ በስተመጨረሻ በተአምራት የተሞላውን ታላቁን ገዳም #ደብረ_ብሥራትን (ጅሩ) መሥረተው በክብር አርፈዋል፡፡
#ክብረ_በዓሉ_ከሚከብርባቸው_አድባራትና_ገዳማት
#በአዲስ_አበባ
፩. ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም፤
(ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤

Telegram
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
👍12❤5
፪. ቦሌ አራብሳ ዘንዶ አስራ በዓታ ማርያም፤
መንግሥት (ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤
፫. ቂሊንጦ መካነ ፍስሐ ቅዱስ ሚካኤልና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ.፤
ቂሊንጦ አደባባይ፤
፬. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስትሥላሴ ቤ.ክ፤
ጠሮ፡፡
ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ ሞቢሉ ጋር (4 ኪሎ) → ፈረንሳይ/ኢየሱስ/፤
፮. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
ላፍቶ፡፡
፯. ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል
ለቡ(ፉሪ)፡፡
፰. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤
ሰፈረ ገነት፡፡
፱. ኮተቤ የካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤
(ብረታ ብረት)፡፡
፲. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤
አቃቂ ኬላ፡፡
፲፩. ደብረ ሰሊሆም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና መድኃኔ ዓለም ቤ.ክ.፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → በርታ ሰፈረ ሰላም፡፡
#በመላው_ኢትዮጵያ
፲፫. ደብረ ኤረር በዓታ ወልደታ፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ የተመሠረተ፤ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምድር፤ የምሥጢር ቦታ)
(ዱከም) → ደብረ ኤረር፡፡
፲፬. ባሕር ዳር ጽርሐ አርያም ደብረ ሲና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ. (በ1313 ዓ.ም. በአቡነ ዘዮሐንስ የተመሠረተች)፤
ባሕር ዳር
፲፭. ጎንደር ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም /ወዑራኤል/፤ (የታች ቤት አቋቋም ዋና ምስስከር) (በጎንደር ዘመነ መንግሥት በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተች) ጎንደር
፲፮. ጂንካ በዓታ ለማርያምና ቅድስት አርሴማ ቤ.ክ.፤
ጂንካ
#የመልአኩ_የፋኑኤል_በዓል_ከሚከብርባቸው
፩. ካራ ቆሬ ቅዱስ ፋኑኤል፤
ካራ ቆሬ፡፡
፪. መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤ.ክ.፤
አያት አደባባይ፡፡
፫. ቅዱስ ፋኑኤል
#የአቡነ_ዜና_ማርቆስ በዓል
፩. ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ
ጅሩ → ደብር፡፡
፪. ምሁር አክሊል አቡነ ዜና ማርቆስ
ወልቂጤ → ምሁር፡፡
፫. ጣፎ አቡነ ዜና ማርቆስ
→ ጣፎ፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

👍7