Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.4K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
እንኳን ለኅዳር ጽዮን ማርያም (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ በሁሉም ቦታ የሚባለውን የኅዳር ፳፩ ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፤ ዚቁንና ወረቡን እንደ የደብራችሁ የአቋቋም ይትበሃል ትቆሙ ዘንድ፤ የላይ ቤት በሚቆባቸው አድባራት ዚቅ ዘግምጃ ቤት የሚለውን ተመልከት፤ የታች ቤት በሚቆባቸው አድባራት ዚቅ ዘበዓታ የሚከለውን ተመልከት፡፡ በተጨማሪ የሸዋ ወረብን (እንደ አዲስ አለም ማርያምና እንጦጦ ማርያም ባሉት) የሚባለውን አብረን አዘጋጅተነዋል፡፡
ኅዳር 21 የታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ) ዓመታዊ ክብረ በዓል የምናከብረው፤
1.በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ የተመለሰችበትን፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)
2. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)
3. በቀዳማዊ ምኒልክ ቀዳማዊ ንጉሥ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት:: (ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …)
4, በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም መካናት በስደት ከልጇጋር ባርካ አኵስም ጽዮን መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ (ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ..)
5.በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ አማካኝነት መስዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵስም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ 12 መቅደሶች ያሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤት የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡
6. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክዕና አምሳል (ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፥ በአምሳለ ብእሲት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት
6.1 እረኛው ሔርማ ጻድቅ ቤተ ክርስቲያንን በአምሳለ ብእሲት በራእይ የተመለከተበት
6.2 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ዘሀገረ ሮሜ የሚዘከርበት
7. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ትሰደድ ነበርና:: ተመልሳ ስትታነጽም (ከዮዲት ወረራ በኋላ፤ ከግራኝ ወረራ በኋካ አፄ ፋሲል፤ በአዲስ መልክ አፄ ኃይለ ሥላሴ ካነጹ በኋላ) ቅዳሴ ቤቷ የተከከበረው ኅዳር 21 ቀን ስለኾነ፡፡
(የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት)
• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 http://tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
13👍9