Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.4K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
#እንዃን_ደስ_ያላችኹ

የ2017 የትምህርት ዘመን በቀጨኔ ደብረሰላም ወ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል  ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት  ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ምዝገባ እነኾ ተጀምሯል።

#የምንሰጣቸው_ኮርሶች_:-

- ትምህርተ ሃይማኖት
- ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ወ ህይወት
- የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት
- የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
- ሥርዓተ ወ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
- መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ

#የሚሰጡበት_ቀናት
ሰኖ ረቡዕ አርብ
ማታ ከ12፡00 - 1:45
እንዲሁም
ቅዳሜ 9፡30 - 12፡30
እሁድ 4፡30-6፡00

#መመዝገቢያ_ቦታ

- በፍኖተ ህይወት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ
-ቤተመጻሕፍት
-ፍኖተ ሱቅ (የሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ )

#መመዝገቢያ_ስልኮች

09-33-09-54-12
09-34-11-30-23
09-60-41-25-71



Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram...  https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot 
.YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
                   www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
👏7👍61
እንኳን ለአባታችን #አቡነ_ሀብተማርያም በዓለ ጽንሰት በሰላም አደረሳቹ::

አቡነ ሀብተማርያም

፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤
፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤
፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ ታለቅ አባታችን ናቸው፡፡፡፨

፠ታላቁ ጻድቅ አባታችን #አቡነ_ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በንጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡

የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሐሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡ ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እናታቸውም ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ #7_አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡

፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡

፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡
ለአብነትም፤
ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው ፡፡

፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡
*የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡
፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው::

"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው::

+ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: መላእክትም ዝማሬም ወሰዷት::

 ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
፩ኛ. #መብረቅ
፪ኛ. #ቸነፈር
፫ኛ. #ረሃብ
፬ኛ. #ወረርሽኝ
፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሀብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)

✞✞✞✞✞
#አቡነ #ተክለሃይማኖት አና #አቡነ #ሀብተማርያም


#ያን ጊዜ ክቡር የሆነ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ጠርቶኝ ልጄ #ሀብተ_ማርያም ሆይ ፈጣሪየ እግዚአብሔር ስለ ወደደህ ብዙ ምህርኮ እንደአገኝህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል አለኝ ፤
#ነገር ግን የሞለምንክ አንድ ነገር አለና እሽ በለኝ ቢለኝ አቤቱ ጌታዩ ምንድን ነው ነገሩ አልሁት ፣
#ክቡር አባታችን አባ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀብር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለኝ፤
ይንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትለምነኛለህ ብየ ብመልስለት፣ እነሆ በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስ መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው ፤ እሊሁም አንዱ መብረቅ ነው ፣ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ፤ ሦስተኛው የረኃብ ጦር ነው ፣ አራተኛ ወረርሽኝ ነው ፡፡ አምስተኛ የእሳት ቃጠሎ ነው ፤ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደ ሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገር ከእንዚህ መቅስፍታት ትድናለች፣
#……ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሄር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው አለኝ ፣ ይልቁንስ እንዳልኩክ በተቀበርኩበት ቦታ እንተቀበርልኝ ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ መላልሶ ማለደኝ.
ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም

#አቡነ_ሀብተ_ማርያም በቃል ኪዳናቸው ሀገራችንን ከአምስቱ መቅሰፍታት ይጠብቁልን አሜን !

በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
፠፠፠
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like
👍108
#እንዃን_ደስ_ያላችኹ

የ2017 የትምህርት ዘመን በቀጨኔ ደብረሰላም ወ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል  ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት  ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ምዝገባ እነኾ ተጀምሯል።

#የምንሰጣቸው_ኮርሶች_:-

- ትምህርተ ሃይማኖት
- ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ወ ህይወት
- የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት
- የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
- ሥርዓተ ወ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
- መዝሙርና ምሥጢራዊ ሥርዓቱ

#የሚሰጡበት_ቀናት
ሰኖ ረቡዕ አርብ
ማታ ከ12፡00 - 1:45
እንዲሁም
ቅዳሜ 9፡30 - 12፡30
እሁድ 4፡30-6፡00

#መመዝገቢያ_ቦታ

- በፍኖተ ህይወት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ
-ቤተመጻሕፍት
-ፍኖተ ሱቅ (የሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ )

#መመዝገቢያ_ስልኮች

09-33-09-54-12
09-34-11-30-23
09-60-41-25-71

Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram...  https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot 
.YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
                   www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
👍10