❤23👍6
እንኳን አደረሳቹሁ !
ጾመ ፍልሰታ
#ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡
በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ) 5. ✣ ጾመ ነነዌ
2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ) 6. ✣ጾመ ጋድ
3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 7. ✣ #ጾመ #ፍልሰታ
4. ✣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
#ጾመ_ፍልሰታ
ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።
ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።
ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

👍8❤7
በአጠቃላይ #የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ #የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

Telegram
ፍኖተ ሕይወት ሚድያ
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት
👍10❤5
#ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ #ለማርያም_ድንግል
#ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ:: ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡
✣ ✣
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሐይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
✣ ✣ ✣
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡
✣ ✣ ✣
ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ #ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና #ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት #ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፤ #ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ# ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን #ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ #ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ #እያቄም ጋር አጋቧት::
✣ ✣ ✣
እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
✣ ✣ ✣
ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡
✣ ✣ ✣
ሃናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
✣ ✣ ✣
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህ ብሎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ዕለት #ነሐሴ_7 ቀን ተፀነሰች፡:
✣ ✣ ✣
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::

❤15👍4
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን አሜን ፡፡/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/Finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram... https://t.me/Finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
Telegram
ፍኖተ ሕይወት ሚድያ
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት
❤8
👍3
#ዜና_እረፍት
በደብራችን ቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለምቤተ ክርስቲያን በትሩፋት ሲያገለግሉ የነበሩት መምህር ወልደሚካኤል በዛሬው እለት ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም አርፈዋል።
ስርዓተ ቀብራቸዉም ነሀሴ 9/2016 ዓ.ም 9:00-10:00 በደብራችን ይፈፀማል።
መምህር ወልደ ሚካኤል ከ40 ዓመታት በላይ
ደብሩን ያለምንም ደመወዝ በትሩፋት ያገለገሉ ታላቅ አባት ነበሩ።
"እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ መምህርነ ወልደሚካኤል"

😢57❤10👍10
#የየኔታ_ወልደሚካኤል_አጭር_የሕይወት_ታሪክ
#የኔታ_ወልደሚካኤል_ተወልደ_ብርሃን ልዩ ስሙ ፅልማ ስራዬ አዲለጎ በ1920ዓ.ም ሚያዝያ 29 ተወለዱ በአያታቸው ቤትም መምህር ትርፉ ክፍሉ ከተባሉት ፊደል ንባብ መልክዐ ማርያም መልክዐ ኢየሱስ ሰዓታት እና ግብረዲቁና ተማሩ በ1939 መጋቢት ወር ወደ ላስታ ገለሶት ሃዋ ሚካኤል ቄስ ተስፋዬ ከሚባሉ ጋር አባ ኪሮስ ወደ ሚባሉ የድጓ መምህር በመምጣት የቃል ትምህርት አጠናቀዋል በ1940 ዓ.ም መስከረም 21 ከአራት ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው ወደ #ግሸን_ማርያም በመሄድ የአቋቋም የድጓ የዝማሬ እና የቅዳሴ መምህር ወደ ሆኑት የኔታ መንግስቱ የሚባሉ ስመጥር መምህር ጋር የሄዱ ሲሆን ክብረ በዓሉን አክብረው የኔታ መንግስቱ ወደ ደሴ የኔታ አፈወርቅ ወደ ሚባሉ 150አካባቢ ተማሪ ወደነበራቸው የቅኔ መምህር ደሴ መድኃኔዓለም ላኳቸው።
ደሴ መድኃኔዓለም ቅኔ መማር የጀመሩ ሲሆን በ10ወር ቅኔ ተቀኝተው ወደ ግሸን ማርያም በመመለስ ምርቃት በመቀበል ተመልሰው ደሴ መድኃኔዓለም ቅኔውን ማስፋፋት ያዙ። በ1941 ዓ.ም መምህሩ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲሄዱ እዛው ደሴ የኔታ ኤልያስ እና የኔታ ወልደማርያም ከሚባሉ መምህራን እየተማሩ ቆዩ ታህሳስ 22 በ1941 ዓ.ም ከሁለት ተማሪዎች ጋር ሆነው ወደ ደብረሊባኖስ በመሄድ የኔታ አፈወርቅ ጋር ገብተው የቅኔ ትምህርታቸውም ማስፋፋት ቀጠሉ በመሃል የኔታ አፈወርቅ ወደ አዲስዓለም ማርያም ሲሄዱ የኔታ ወልደሚካኤል ደብረፅጌ የኔታ ይትባረክ (የሩፋኤል አስተዳዳሪ የነበሩት ጋር) አንድ ወር ከግማሽ አሁን የቅኔ ትምህርታቸውን ሲያስፋፉ የቆዩ ሲሆን ሰኔ 21,1941 ዓ.ም ወደ ቀድሞ መምህራቸው የኔታ አፈወርቅ ዘንድ ወደ አዲስ ዓለም ማርያም በመሄድ የቅኔ ትምህርታቸውን እያስፋፉ ተማሪዎችንም ያስቀፅሉ ነበር።
የኔታ ወልደ ሚካኤል በትምህርት ቤት በነበሩበት ጊዜያት ሁሉ ከስራቸው ያሉ ተማሪዎችን በማስቀፀል ይታወቃሉ በ1944 ዓ.ም በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ማርያም ከመምራቸው የኔታ አፈወርቅ በቅኔ መምህርነት ተመርቀው እዚሁ ደብር በቅኔ መምህርነት እንዲያስተምሩ የተቀጠሩ ሲሆን #ማስተማር_እንጂ_ደመወዝ_አልወስድም በማለት አንድ ዓመት ቅኔ አስተምረዋል።
ተስፋሚካኤል የሚባለው ወንድማቸው በ1946 ዓ.ም መጥቶ ከአዲስ አለም ወደ አስመራ የወሰዳቸው ሲሆን እዛም የተለያዩ አድባራት እያገለገሉ ቆይተው በ1947 ዓ.ም ወደ መቀሌ በመምጣት መቀሌ ኪዳነምህረት እና መድኃኔዓለም የኔታ ኃይለሥላሴ ከሚባሉት እውቅ መምህር በድጋሚ ፀዋትወ ዜማ እየቀፀሉ ቅኔ ማስተማር ጀመሩ በወቅቱም የዜማ መምህራቸው የኔታ ኃይለሥላሴም የኔታ ወልደ ሚካኤል ዘንድ ቅኔ ይማሩ ነበር መስከረም 1950 ዓ.ም የቅኔ መምህራን ተመርጠው ለፈተና ቅድስት ሥላሴ ተፈትነው የኔታ ወልደሚካኤል ፈተናውን አልፈው አንድ ዓመት የመምህርነት ስልጠና በመውሰድ በዕጣ ጋሞጎፋ ተመድበው ግብረ ገብ እና አማረኛ መምህር ሆነው 3 ዓመት አስተምረዋል።
በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመዛወር አምሃደስታ ት/ቤት ተመድበው እስከ 1959 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት አምሃ ደስታ ትምህርት ቤት ሲያስተምሩ ቆይተው በ1960 ዓ.ም ቀለመ ወርቅ ት/ቤት ተመድበው የመጡ ሲሆን ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ #ቀጨኔ_ደብረሰላም_መድኃኔዓለም_እና_ደብረ_ትጉሃን_ቅዱስ_ገብርኤል_ቤ/ክ በማህሌት በመቆም እና ቅኔ በመቀኘት አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን በ1966 ዓ.ም ድጋሚ ወደ አምሃ ደስታ ት/ቤት በመመለስ እስከ 1981 ዓ.ም በማስተማር በዛን ጊዜ በነበረው ሕግ መሠረት በ55ዓመታቸው ጡረታቸውን አስከብረዋል።
በ1987 ዓ.ም ከጡረታ በኋላ በሚያውቋቸው መምህራን ጠቋሚነት ምስካየ ኅዙናን ገዳም ዘመናዊ ት/ቤቱ ውስጥ ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር ግዕዝ አስተምረዋል በተያያዥም ቀን ቀን በገዳሙ የተመደቡ የቅኔ መምህር ስለነበሩ #በበጎ_ፈቃደኝነት ማታ ማታ ደግሞ የኔታ ወልደሚካኤል መነኮሳቱን ግስ ያስተምሩ ነበር።
በ1989 ዓ.ም ዘመናዊ ትምህርት ማስተማሩን በማቆም #ቀጨኔ_ደብረሰላም_መድኃኔዓለም_እና_ደብረ_ትጉሃን_ቅዱስ_ገብርኤል_ቤ/ክ ልክ እንደ አንድ መደበኛ ሠራተኛ #በእለተ_ሰንበት #በወርሃዊ_በዓላት እና #በዓበይት_በዓላት #በገረገራው_ውስጥ_በማደር በሕመም ቤት እስከዋሉበት ጊዜ ድረስ መድኃኔዓለምን በቅንነት ያገለገሉ አባት ነበሩ ።
የአገልግሎት ዋጋቸውን የሚከፍለው ያገለገሉት አምላክ ቢሆንም #በፍኖተ_ሕይወት_ሰንበት_ት/ቤት እና #ማኅበረ_አሃው የአጥቢያው ማኅበር በሚዘጋጀው "#ዝክረ_አበው" በተሰኘው አባቶች በሕይወተ ሥጋ ባሉበት ወቅት ፀሎታቸው እና ምርቃታቸውን እንዲሁም በአገልግሎት አርአያ በመሆናቸው ለመታሰቢያ በሚዘጋጀው መርሐ ግብር #የሙካሽ_ካባ ተበርክቶላቸዋል የኔታ ወልደሚካኤል በአገልግሎት በቆዩባቸው ዘመናት #ምንም_ድካም_የማይታይባቸው_ብርቱ_አባት_ነበሩ የኔታ ወልደሚካኤል ባለትዳር እና የ3ሴት ልጆች አባት ነበሩ ነፍሳቸውን ከደጋግ አባቶች ዘንድ ያሳርፍልን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመድም መፅናናትን ያድልልን ለቤተክርስቲያንም እንዲህ ያሉ መምህራንን መድኃኔዓለም ይተካልን።
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/Finotehiwott
www.Finotehiwotsundayschool.com

👍17😢10
መዝሙር ዘሰንበት ነሐሴ ፲፪

👍1
#ደብረ_ታቦር
ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “#ታቦርና #አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው /መሳ. 4፥6/፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ #አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም #ሙሴና #ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ #ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ እንስራ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምፅም ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡
፠፠፠
#አዕማደ_ሐዋርያት_ለምን_ተመረጡ
"አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት #ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ #ሰማያዊ #ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ #ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡
ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት ሲል፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡
“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡
፠፠፠
#Share #like
#The_feast_of_the_transfiguration_of_our_lord_on_mount_tabor #Nehhasee 13

❤5👍5