Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.4K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
፪ኛው ዙር ፥ ዝክረ አበው ዘደብረሰላም
2015 ዓ.ም
ዓርብ ጠዋት ፤ ሚያዝያ 27 ።
8👍3
#ዜና_ዕረፍት
መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ
ከ1937 - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት

‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38

* የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፡፡

* ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸምበትን ዕለት እና ሰዓት እናሳውቃን።

፨፨
መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ በመናገሻ አውራጃ በአዳ በርጋ ልዩ ስሙ ደብረ ጽሙና ገዳም ከአባታቸው ከአቶ መልካሙ ባሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ጥሩነሽ የለሙ ሰኔ 12 ቀን 1937 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በዛው በደብረ ጽሙና ገዳም የንባብ መምህር ከነበሩት ከየኔታ ወልደ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የንባብ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው አጠናቅቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዜማ መምህር ከነበሩት መምህር መንበሩ ገብረ ሕይወት ጋር በመሄድ የዜማ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በደብረ ጽሙና ገዳም የቅዳሴ መምህር ከነበሩት ከአባ ንዋይ ወልደ ማርያም የቅዳሴ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ በ1953 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 1959 ዓ.ም ከ ወ/ሮ ትምክህተ ታደሰ ጋር በህገ ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻን በተማሩበት በደብረ ጽሙና ገዳም ፈጽመዋል ከጋብቻውም አንድ የልጅ ፍሬ አግኝተዋል፡፡ ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ በመስከረም 25 ቀን 1960 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡

በትውልድ አካባቢያቸው በቅስና ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ቆይተው መጋቢት 5 ቀን 1962 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከመምሬ መኮንን ወልደ ሥላሴ ጋር በመምጣት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም በዲቁና ተቀጥረው ማገልገል ጀመሩ፡፡ ነገር ግን የመንግስት ለውጥን ተከትሎ መሬታቸው በመወረሱ ምክንያት እን በወቅቱ ይከፈላቸው የነበረው በዓመት 15 ብር የድጎማ ገንዘብ ቤተሰብ ለማስተዳደር በቂ ባለመሆኑ ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን በመንግስት መስሪያ ቤት የፍትህ ሚኒስቴር በመቀጠር ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1971 ዓ.ም በደብሩ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በወቅቱ የነበሩት የአጥቢያው ሽማግሌዎች ልጆቻችን ይመለሱ በማለታቸው ከተመለሱትና ዳግመኛ የሙሉ ሰዓት አገልግሎታቸውን ከጀመሩት አገልጋዮች መካከል የያን ጊዜው ሊቀ ዲያቆን የአሁኑ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ አንዱ ናቸው፡፡

መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ በደብሩ በሊቀ ዲቁና፤ በዳቦ ቤት ሽያጭ፤ በዳቦ ቤት ተቆጣጣሪነት፤ በደብሩ ገንዘብ ያዢነት፤ ደመወዝ ከፋይነት፤ በቄሰ ገበዝነት ለሁለት ጊዜ፤ በሰበካ ጉባኤ ተወካይነት፤ በልማት ኮሚቴነት፤ እንዲሁም በአሁን ሰዓት በስርዓተ ጋብቻ አስፈጻሚነት ተመድበው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ የንስሃ ልጆቻቸውን እና በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር ለቤተ ክርስቲያኑ አስፈላጊ የሆኑ ንዋየ ቅድሳትን በማሟላት ለተከታታይ 52 ዓመታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፤

የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን !

#የሥርዓተ ቀብር ሰዓቱን የምናሳውቅ ይኾናል ።

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ።
#share

.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
😢19👍102
+ የአባታችን የመጋቤ ሐብታት ታደሰ መልካሙ #የቀብር_ሥነ_ሥርዓት ለ 53 ዓመታት ባገለገሉበት በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነገ #ሐሙስ ከ #4 እስከ #5 ይፈጸማል ።

+ ዛሬ ከምሽቱ ዠምሮ በማሕሌት በሰዓታት እና በጸሎተ ፍትሐት በቁመት ይታደራል።

#ከአባታችን በረከት ያሳታፈን ።
👍25😢8
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ_ሚያዝያ_

ማርቆስ የሚለው ስም 3ት ፍቺዎች አሉት ንብ፣ አንበሳና ካህን::
ሀ) *ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ነው፤

ለ) *አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር፤ በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው፡፡

ሐ. *ካህን የሚለው ትርጕም ደግሞ በሐዋ. 14፥13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው::

፠ ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው፤ ሐዋ. 12፥12፡፡ አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ፡፡ እናቱ ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት
ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን (በተነሣ በ50ኛው ቀን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሐዋ. 2፥1 ፤ 12፥12፡፡
፠ የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር ፥ በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል:: ሐዋ. 12፥25፣ ቈላ. 4፥10፣ 1ኛ ጴጥ. 5፥13
፠ በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡ እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ::

፠ ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ፥ ተአምራቱን አይተው አመኑ፥ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም፤ ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው፤ በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፤ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12ኛው ሲጀመር ፥ ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ.ም. ባለው ጊዜ/ ነው::

፠ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቊጥር በዝተው፥ በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር
በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፤ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፤ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም፥ አልሸሽም አለ፡፡ እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ፥ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ፡፡ ወደጌታ ቢያመለክት፤ ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ፤ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት፥ በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥልላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ፤ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ፥ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ፥ የፀሐይም ብርሃን ተሠወረባቸው፤ በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል፡፡ ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው በክብር ሥጋውን በአሌክሳንድርያ ቀብረውታል::

፠ በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 ዓ.ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት፤ በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር።
ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የሮማው ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ፤ ቅዱሱ ባረፈ በ1900 ፥ በተወሰደ በ1140 ዓመት አጽሙ ሰኔ 17 ቀን 1960 ዓ.ም.
ፈልሶ ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ፡፡ ሲመለስም ጃንሆይም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወ መንግሥት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ
በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት ፥ አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ፥ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኰሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ፥ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ፥ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ፥ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን፥ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ
ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው፥ ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው፥ በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከ4ኛ ክ/ዘ/ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እስከ አቡነ ቄርሎስ 20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ፥ ሥርዐታችን ከሥርዓታቸው የተስማማ
6👍2
፥ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን ፥ እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡
---------------
፠ በፎቶ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤
* ሰላ ድንጋይ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ምኒልክና የተሠራና የአቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ በልዩ አሠራር በ42 ቆመ ብእሲ (ዐምድ) የታነጸ፡፡
* መናገሻ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአቡነ ማቴዎስ የተሠራና መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ ውጭው ክብ ውስጡ ግን ከሌሎች ክብ አብያተ ክርስቲያናት ልዩና ድንቅ በሆነ አሠራርና ሥዕላት የተሞላ፡፡ቀ
* ጎጃም ደብረ ማርቆስ፤
* መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ከቤተ መንግሥታቸው ላይ ቦታ ቀንሰው ያነጹት ቤ.ክ.፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::
  #share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram...  https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
     www.finotehiwotsundayschool.com 
YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
👍2
ꔰ ꔰꔰእንኳን ለእመቤታችን 2030ኛ ዓመት በዓለ ልደት አደረሳችሁꔰ ꔰꔰ
ꔰ  #ልደታ_ለማርያም  ꔰ
#ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል? ꔰ
ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ
ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ
#የግንቦት_ልደታ_ለማርያም_ክብረ_በዓልና_የእመቤታችን_በዓላት
በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል›› ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ. 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል፤ ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ. 111፥7በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 33ት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡

#ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል?
      በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› ይላል፡፡ 1ኛ ዜና 29፥29

#የእመቤታችን_የልደቷ_ታሪክ
የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ‹‹ሐና››ና ኢያቄም/ዮአኪን በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሐና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሐና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ እርግብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡
ስለ ሐና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡

#እመቤታችን_የት_ተወለደች?
እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሐሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሐሳቦች የሚያነሱ ሲሆን፤ አንደኛዉ ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች›› የሚል ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ሐሳብ ደግሞ ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሐና የክሩሲድ ቤ/ክ በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡
የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፊንቄ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ›› መኃ. 4፥7 የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምሥጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡

#የልደታ_ለማርያም_በዓል_መቸ_ነዉ?
እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ ና7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅ/ ዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡
የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬ.ክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀዉልት በማቆም ዐስር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡

#የድንግል_ማርያም_ልደት_ለምን_ይከበራል?
* ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅ/ገብርኤል አንደበት‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› በማለት ተነግሯል (ሉቃ 1-14)፤ ምክንያቱም ቅ/ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ፥ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ፤ የድንግል ማርያም ልደትማ ምንኛ የሚያስደስት ይሆን!?፡፡ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡
* የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል
* እመቤታችን  ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፤ በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡
* ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት ‹‹መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››፤ ‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››፤ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ››፤ …. ብለዉ የተናገሩላት ቅ/ድ/ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ደስታችንም ነዉ፡፡ (መዝ. 86፥1፣ ኢሳ. 11፥1፣ መኃ. 4፥7)ጂነአ
* በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል፤ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል፡፡ ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ግን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን!

#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር
ሐናና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳውያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ፈንድሻ የሚጥሉ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡
👍15
ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ
ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ
ማርያም ሥመሪ ወጸሐቂ እንበለ ንትጋ ፤
ለማየ ንጽሕኪ ትረስዩኒ ፈለጋ፤
እስመ ንጽሕ   ይሁብ ምገሰ ወጸጋ፡፡


/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤      የተዘጋጀ ::


  #share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.Telegram...  https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
     www.finotehiwotsundayschool.com 
YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .