#ኢ. #ና. #ን. #አ. ‹‹#የጻፍሁትን_ጽፌያለሁ::››
#ኢ
፩ኛ) #፠#ኢየሱስ_፤
፠ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከሥጋ ማርያም ጋር ተዋሕዶ፤ ከሁለት አካል አንድ አካል፥ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆኖ፤ በዘመነ ሥጋዌ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል፤ ኢየሱስ፥ ክርስቶስ፥ አማኑኤል፥ መድኀኔ ዓለም፥ መድኅን፥ የሰው ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ቃል፥ እግዚአብሔር ወልድ፥ አንድዬ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ጌታ፥ … የሚሉ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
፠ ኢየሱስና ክርስቶስ የሚሉት ስሞች ከጥንት ጀምሮ (የሰው አእምሮ ገና ያልበሰለ፤ ክፉዎች አይሁድም ነገሩን ለፌዝ፥ ለቧልት ያውሉት ነበርና፤ ምንም እንኳን በግልጽ ባየገለጹም)፤ በነቢያት የተነገሩና በመላእክት የተበሠሩ፤ የጌታን አምላክነት የሚያሳዩ፤ የጌታን አዳኝነት የሚያመለክቱ ስሞች ናቸው፤ /መ.አውሳብዮስ/፡፡ ለምሳሌ፤ ልበ አምላክ ዳዊት ‹‹እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ፤ ስሙ ከፀሐይ በፊት ነበረ፡፡›› /መዝ 71÷17/ ብሏል፤ እንዲሁም ነቢዩ ሙሴ በምሳሌ ጠርቶታል፤ የሊቀ ካህንነቱ አገልግሎት ሊቀ ካህኑ የክብርና የከፍታ ምልክት፣ የነዌ ልጅ ኢያሱም የአዳኛችንን ምሳሌ ተሸክሞ ነበር፡፡›› /ዘጸ. 25፥40፣ ዘሌ. 4፥5፡16፤ 6፥22/ ብሏል ይህንንም የመልክአ ኢየሱስ ደራሲም ‹‹አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አኅጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ፡፡›› (የስምህን አክሊል በራሱ ላይ አድርጎ የጠላትን ሀገሮች ኢያሱ ወርሷል) ብሎ አመስጥሮታል፡፡
• ይህንን ከዓለም በፊት የነበረውን ስሙን ከሰማይ ተቀብሎ ለእመቤታችን እንዲናገር የተላከው መልአክ፤ መጋቤ ሐዲስ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን ‹‹ስሙን የመሰየም›› ሥልጣን የተሰጣት ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡ ˝ኢየሱስ ትይዋለሽ˝ /ሉቃ 1÷31/
፠ #ኢየሱስ_ማለትም(ትርጓሜውም)፤
ሀ) መድኃኒተ ሥጋ ፥ መድኃኒተ ነፍስ ማለት ነው፡፡
* በዕብራይስጥ የሹኣ፥ ኢያሱ ወይም «ያሕዌ መድኃኒት ነው» የሚል ትርጉም አለው።
፠ እርግጥ ነው፥ በትንቢት፥ በምሳሌና በጥላ ቀድሞ ለተነሡት « አዳኞች» ኢያሱዎች ተሰጥቷል። (ለምሳሌ ዘካርያስ 3፥1 ላይ ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን ያስታውሷል።) ሆኖም ግን እነዚህ « አዳኞች» ያዳኑት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው፡፡ ያዳኑትም የእግዚአብሔርን ኃይልና ረድኤት አጋዥ በማድረግ ነው፤ ያዳኑት(የታደጉትም) ከምድራዊ ጠላቶቻቸው ስለሆነ ማዳናቸው ውሱን ነው፡፡
*አማናዊው ኢያሱ አዳኛችን ግን ያዳነው « ሕዝቡን» (የራሱን ሕዝብ) ነው። ያዳነውም እግዚአብሔር ተጠቅሞበት ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ስለሆነ መድኃኒት ሆኖ ነው። ሕዝቡን ያዳነውም «ከኃጢአታቸው» ነው። ይህ አነጋገር የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። በመሆኑም እንደቀድሞዎቹ እግዚአብሔር በምሳሌና በጥላ ሳይሆን ራሱ በመካከላችን በማደሩ ‹‹አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር፡፡›› እንደ ሆነና በዚህም የነቢዩ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ እንዳገኘ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ የገለጠው። ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ማዳኑም የአምላክነቱ መገለጫ ነው።
ለ) ሕዝቡን በኃጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ የሚያድናቸው መድኀኒት ማለት ነው፡፡ /ማቴ 1፥21፣ ተረፈ ኤርምያስ) (ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል፡፡ /ቅ.ኤፍሬም/፡፡) (‹‹ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን›› /ሰቈቃወ ድንግል/)
ሐ) ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልን ማለት ነው፤ ‹‹አመ ይእኅዝዎ ለኢየሱስ ፀሐይ ጸልመ›› /ቅዱስ ያሬድ፥ ድጓ/
መ) ዳግማይ አዳም ማለት ነው (የኢየሱስ የስሙ ቊጥር ከአዳም የስም ቊጥር ጋር የተባበረ ነውና)
*ኢየሱስ፡- አ=40, የ=90, ሰ=7, ሰ=7 ድምር =144፤
*አዳም፡-አ=40, ደ=100, መ=4 ድምር =144
*ዳግማይ አዳም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ወደ ኤዶም ገነት አገባው ማለቱ
ኤዶም፡-አ=40, ደ=100, መ=4 ድምር =144
#ና.
፪ኛ) #፠#ናዝራዊ_፤ ከናዝሬት የመጣ /ማቴ 2፥ 23/፤ በሌላም ትርጕምም ቸር፥ እረኛ፣ በዕብራይስጥ ደግሞ የተለየ ፣ አክሊል የተቀዳጀ ፣ የተቀደሰ ማለት ነው፡፡
፠ ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ አምላኮሙ ለናዝራውያን›› እንዲል /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤ መጽሐፈ ምሥጢር/
፠ ማቴ. 2÷23 «በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጻም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ፡፡››
፠ ትንቢቱ (በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠው) ልጄ እንደ ሶምሶን ናዝራዊ ይባላል የሚል ነው፤ ነገር ግን በ66ቱም ሆነ በ81ዱ መጻሕፍት አይገኝም፤ መጽሐፉ በምርኮ ጊዜ ጠፍቷል፤ ይህም ከ66ቱ መጻሕፍት ሌላ መጽሐፍ የለም ለሚሉ ወገኖች ማስረጃ እንደሆነ አስተውል፡፡
*፠* በመጽሐፍ ቅዱስ ስማቸው የተጠቀሰው ናዝራውያን 2ት ናቸው እነርሱም ሶምሶንና ጌታችን፤ በምን ይመሳሰላሉ ቢሉ::
**ሶምሶን በተናቀች በአህያ መንጋጋ ጠላቶቹን እንዳጠፋ፤ ጌታም አይሁድ፣ አጋንንት፣ መናፍቃን በናቁት ሞቱ ሞትን አጥፍቷል፡፡ /መሳ. 15÷9-19/
**ሶምሶን በሕይወተ ሥጋ ካጠፋቸው አሕዛብ ይልቅ በሞቱ ያጠፋቸው ይበዛሉ፡፡ ጌታም በሕይወተ ሥጋ ሳለ ካጠፋቸው አጋንንት ይልቅ በሞቱ ያጠፋቸው ይበዛሉ፡፡ /ምሳ. 16÷23-31/
#ና.
፫ኛ) #፠#ንጉሥ_፤ አፄ፣ ባለዘውድ፣ ሹም፣ አለቃ፣ ማለት ነው፡፡ /ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም እንዲል፡፡/
#አ
፬ኛ) #፠#አይሁድ_፤ ማለት የታመኑ፣ ምስጉኖች፣ ምዕመናን ማለት ነው፡፡
፠ አይሁድ የሚከው ቃል እስከ ባባሎን ምርኮ ድረስ ከ12ቱ ነገደ ያዕቆብ (እስራኤል) የይሁዳ ብቻ ነበረ፡፡ ከምርኮ በኋላ እስከ ክርስቶስ ድረስ ግን ለእስራኤል ሁሉ (ለ12ቱም ነገድ) መጠሪያ ሆኗል፡፡ /ዘፍ. 29፥ 35/
#የአይሁድ_ንጉሥ (#ማዕከላዊ_ስም)
፠ ሰብአ ሰገል ስም ማዕከላዊ (የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ) እያሉ ነው ለጌታ መብዓ ይዘው የመጡት፤ ስለምንድነው ቢሉ?
* አምላክ (ስም ላዕላዊ) እያሉ ያልመጡበት፤ ሰማይና ምድር የማይችለው ምን ወስኖት ምን ችሎት ነው ብለው እንዳይዘባበቱባቸው፡፡ አንድም ትንቢት የተነገረልን ሱባዔ የተቈጠረልን እኛ እያለን እንዴት ለእነርሱ ተገለጠላቸው ብለው እንዳይዘባበቱባቸው፤ አንድም አሕዛብ ናቸው በየት አውቀውት ብለው እንዳዘብቱባቸው ነው፡፡
* የተወለደው ሕፃን (ስም ታህታዊ) እያሉ ያልመጡት፤ በእስራኤል ሃገር በአንድ ቀን ውስጥ ብዙ ሕፃናት ተወልደው ብዙ ሕፃናት ይሞታሉ፤ ስንቱን እናውቅላችኋለው ባሏቸው ነበርና፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/finotehiwotee
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com

Telegram
ፍኖተ ሕይወት ሚድያ
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት
👍3
ለምን #ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ) (የስቅለት ማግስት ) ላይ ቄጤማ ይታደላል ወይንም ይደረጋል ???
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
ይህቺ ቅዳሜ በእነዚህ ስሞች ትታወቃለች
#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ #ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ)
#ሰንበት_ዐባይ #ቅዱስ_ቅዳሜ፤ #ቀዳሚት_ሰንበት
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ቀዳሚት_ሰንበት፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ያረፈባት ስለሆነች፤ የእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት፤ ቀዳሚት ሰንበት (የዕረፍት ቀን) ትባላለች፡፡
#ሰንበት_ዐባይ (ታላቋ ሰንበት)፤ የመጀመሪያዋ ሰንበት በመሆኗ ታላቋ ሰንበት ትባላላች፡፡
#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ እግዚአብሔር ሥነ ፈጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡
፠ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡
የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና ሌሌችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡
፠ የቻልን ሕዝበ ክርስቲያንም ይህን መነሻ በማድርግ ከዐርብ ጀምረን በማክፈል (በመጾም) እህል ውኃ ሳንቀምሱ ለሁለት ቀናት እናድራለን (እንካፍላለን)፡፡ እንደ ዋልድባና ማኅበረ ሥላሴ ባሉ ገዳማት ያሉ ታላላቅ አባቶችና ወንድሞች ደግሞ ከሆሳዕና አንዳንዶችም ከዕለተ ረቡዕ ጀምረው ለ7ት ቀናት ወይም ለ3ት ቀናት ያከፍላሉ፡፡
#ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ)
ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ (በመስቀሉ ሰ
ላምን አደረገ፥ መሠረተ)›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡
፠ ቄጠማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምደር በተጠለቀለቀች ጊዜ፤ ኖኅ ወደ መርከብ ይዟቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ልኮ እርሷም ቄጠማ በአፏ ይዛ በመመለስ የምሥራች ምልክት፥ የውኃውን መድረቅ እንደተነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡ ‹‹በክርስቶስ ሞት፤ ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስንል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት ደባትር መዘምራን ዝማሬን ካቀረቡ በኋላ ለልጆቿ ቄጠማ ታድለናለች፡፡ የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማም፤ ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን፡፡
(ፍኖተ ሕይወት)
#ቅዱስ_ቅዳሜ፤ ለ5500 በሲኦል ሲማቅቁ የነበሩ ነፍሳትን ሰላም ለሁላችሁን ይሁን ብሎ ወደ ገነት አስገብቷቸዋልና፤ ይህች ቅዳሜ ቅዱስ (የተለየች) ቅዳሜ ትባላለች፡፡
አውረድዎ፥ አውረድዎ፥ አውረድዎ እምዕፅ፤
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕዉስ፡፡

👍4
እንኳን በሰላምና በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ #ፋሲካ_ፋሲካ_ፋሲካ፤ #ተዝካረ_ትንሣኤሁ_ለክርስቶስ፡፡ /ቅዱስ ያሬድ/ #ትንሣኤ_ትርጕም_በዓሉና_አከባበሩ
(«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግስ ሲሆን፡፡ «ትንሣኤ» ማለት = መነሣት፥ አነሣሥ፥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዓይነቱ ሲተረጐም ፭ት ክፍል አለው፡፡ ፩ኛ) «ትንሣኤ» ማለት ኅሊና ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡ ፪ኛ) «ትንሣኤ» ማለት ልቡና ማለት ነው፡፡ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡ ፫ኛ) «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡ ፬ኛ) «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የዛሬው ትምህርታችንም ይህንን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ፭ኛው)ና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጕባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፥ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡ ፠ ወደተነሣንበት ርዕስ ስንመለስ የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምሥጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «#ፋሲካ_» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርዕ (በግሪክኛ) «ስኻ» ይባላል፡፡ በግእዝና በዐማርኛ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገር፣ መሸጋገር ማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛ «ስኦቨር» ይሉታል፡፡ የዚህም ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ የምንገኝ እስራኤል ዘነፍስ የሆንን ምዕመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የምናከብረው፤ በእርሱ ትንሣኤ ከኀጢአት፤ ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር ፥ ከውርደት፤ ወደክብር፣ ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ፤ ወደ ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ ከአደፈ፥ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት፤ ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገርንበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት እናከብረዋለን፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡ #የበዓሉ_አከባበር_«እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን» መድኀኒታችን ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑ የተነሣው በእለተ እሑድ፥መጋቢት 29፥ በ34 ዓ.ም እንደሆነ ታሪከ ቤተ ከርስቲያን ያስረዳል፡፡ የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረው በቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ ኋላም በየጊዜው በተነሡት ሊቃውንትና ምእመናን ነው፡፡ ድምቀቱና የአከባበር ሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂ መከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡ እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ኢየሩሳሌም ባሉ ታላላቅ ገዳማት ደግሞ በዓሉ እጅግ በጣም በታላቅና በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡ #የበዓሉ_አከባበር_ከዋይዜማው_ጀምሮ_እስከ_ሌሊት_የሚከተለውን_ይመስላል፤ በዋይዜማው ማታ በ2 ሰዓት «ለጸሎት ተሰብሰቡ» የሚል ደወል ድምፅ ይደወላል፡፡ እንደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ባሉ ታላላቅ አድባራት የተጋብኦ ከበሮ ይመታል፡፡ ካህናቱ ዲያቆናቱና ምዕመናኑ ነጭ ልብስ ይልበሱ፤ ጧፍ ያብሩ፤ ዲያቆናት ጥላ ያጥሉ፡፡ በላይ ቤት አቋቋም በሚቆሙ፤ የነቢያት ጸሎት የለም /በታች ቤት/፤ የነቢያት ጸሎት (ጸሎተ ሐና፣ ጸሎተ ሕዝቅያስ፣ ጸሎተ ምናሴ፣ ጸሎተ ዮናስ፣ ጸሎተ ዳንኤል፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣ ጸሎተ ዕንባቆም፣ ጸሎተ ኢሳይያስ፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም፣ ጸሎተ ዘካርያስ፣ ጸሎተ ስምዖን) ይድገሙ፡፡ ውዳሴ ማርያምንና ክስተተ አርያምን በዜማ ያድርሱ፡፡ ‹‹ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ›› የሚለውን ግጥማዊ የደስታ መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ መልክአ ሥዕል ከትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ ድረስ አይደረስም እሰግድ ለኪ ብለህ ተዓምረ ማርያምና ተዓምረ ኢየሱስን አንብብ እንዳበቃ ጸሎተ አኰቴት ይደርሳል፡፡ ዲያቆኑ ነጭ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ፥ አክሊል ደፍቶ፥ የመጾር መስቀል ይዞ፥ እንደ እርሱ ነጭ ልብሰ ተክህኖ በለበሱ ደማቅ የጧፍ መብራት በሚያበሩና ድባብ ፥ ጃንጥላ በያዙ ሁለት ዲያቆናት በግራ በቀኝ ታጅቦ ከመቅደስ ብቅ ብሎ በቅድስት ይቆማል፡፡ (ይህም በጌታችን መቃብር በራስጌና በግርጌ በታዩት መላእክት ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ.20-12) ቀጥሎም በመዝሙረ ዳዊት /መዝ.፸፯፥፳፭/ ያለውን፤ ‹‹ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤ ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ፡፡ (ትርጕም፤ እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ስካር እንደተወው ኀያል ሰውም፣ ጠላቱን በኋላው ገደለ፡፡» የሚለውን ምስባክ ይላል፤ ካህናቱና ሕዝቡ ከበሮ እየመቱና እያጨበጨቡ በእርጋታ እያጨበጨቡ የምስባኩን ተሰጥኦ ይመልሱ፡፡ ምስባኩንም በዲያቆኑ 2 ጊዜ በመላው ካህናትም 2 ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ ዲያቆኑም መላው ካህናትም አንድ ጊዜ ብለው 5 ጊዜ ይሆናል፡፡ 5,500 ዘመን ሲፈጸም በጌታችን ሞትና ትንሣኤ ዓለም ለመዳኑ ምሳሌያዊ ማስረጃ ነው፡፡ ቀጥሎም ካህኑ ትንሣኤውን የሚያበሥር ወንጌል ከማቴዎስ፣ ከማርቆስና ከሉቃስ አውጥቶ ያነባል፡፡ ከዮሐንስ ወንጌል ያለው የትንሣኤው ወንጌል ኋላ ለቅዳሴው ጊዜ ይቆያል፡፡ ዮሐ.
20፥1-9 በማስከተል ከሊቃውንት ደባትር መዘምራን የተመደበው መዘምር የዲያቆኑን መፆር መስቀል ይዞ «ትንሣኤከ ለእለ አመነ» የሚለውን እስመ ለዓለም ከቃኘ በኋላ ለበዓሉ ተስማሚ የሆነው 2 አርያም (ሃሌ ሉያ ለአብ፥… የሚለው) ተመርቶ በመቋሚያ ይዘመማል፤ በማስከተልም «ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፣ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን = ክርስቶስ ከሙታን ቀድሞ ተለይቶ ተነሥቷልና በሰንበተ ክርስቲያን ዛሬ ደስታ ሆነ፡፡...» የሚለውን አንገርጋሪ ያመለጥናል (ይመራል)፡፡ በግራ በቀኝ እየተነሣ መዘምራኑም ይዘምሙታል ይጸፉታል፤ ያለዝቡታል፤ ወዲያውም «ብርሃነከ ፈኑ፤ ለእለአመነ = ለአመነው ብርሃንህን ላክልን፡፡» የሚለውን እስመ ለዓለም እየወረቡ መብራት እያበሩ ዑደት ያደርጋሉ = ቤተ ክርስቲያኑን በውስጥ ይዞራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ «በጨለማ የነበራችሁ ሕዝቦች ኑ የትንሣኤውን ብርሃን እዩ፣ ብርሃኑንም ወስዳችሁ የብርሃኑ ተካፋይ ሁኑ፡፡» እያለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስታዘጋጅ የሰነበተችውን ጧፍ ለምዕመናን እንዲያበሩ ታድላቸዋለች፡፡ ሕዝቦቹም ካህናቱን ተከትለው በታላቅ ደስታና ድምቀት ዑደት ያደርጋሉ፡፡ ፠ መዘምራኑና ካህናቱ ከዑደት ሲመለሱ «ይእቲ ማርያም» የተባለው የኪዳን ሰላም ይጸፋና ኪዳን ተደርሶ ሲያበቃ እንደ በማዕርግ ከፍ ያለው ካህን ዘለግ ባለ ድምፅ በንባብ የሚከተውን ፫ት ጊዜ ሲያውጅ ካህናቱና መዘምራኑም ይቀበሉታል፤ #ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን (ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነሣ) #በዐቢይ_ኀይል_ወሥልጣን (በታላቅ ኀይልና ሥልጣን)፤

#አሰሮ_ለሰይጣን_ (ሰይጣንን አሰረው) #አግዐዞ_ለአዳም(አዳምን ነጻ አወጣው)፤ #ሰላም (ሰላም ፍቅርና አንድነት) እምይእዜሰ (ከዛሬ ጀምሮ) #ኮነ (ኾነ) #ፍሥሐ_ወሰላም (ሰላምና ደስታ ኾነ)፡፡ ፠ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ ከላይ ያለውን ዐውጆ ሲያበቃ «#ነዋ_መስቀለ_ሰላም» እያለ መስቀል ሲያሳልም ካህናትና ሕዝቡም «#ዘተሰቅለ_ቦቱ_መድኀኔ_ዓለም» እያሉ ይሳለማሉ፡፡ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ «#እግዚአብሔር_ይፍታ» ይላል፡፡ ግብረ ሕማማት ሲነበብበት ከሰነበተው ጠበልም ይረጫል፡፡ የተረፈውንም ጠበል ሕዝቡ ለበረከት ወደየቤቱ ይወስደዋል፡፡ ፠ ከዚያም ልኡካኑ ለቅዳሴ ይዘጋጃሉ፤ ሊቃውንት ደባትር መዘምራንም ምስማክ፥ መወድሱን ካዜሙ በኋላ በመቋሚያ ይዘምሙታል፡፡ አያይዞም በዓመት ፫ት ጊዜ የሚዘመረውን «ይትፌሣሕ ሰማይ …» የተባለውን መዝሙር ቃኝተው ከዘመሙ በኋላ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ = ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካውን ታደርጋለች፡፡» እያሉ ይጸነጽላሉ፡፡ አያይዘውም የመዝሙሩን ሰላም (ፍጹመ ንጉሠ ኰነንዎ …)ን ይጸፋሉ፡፡ ፠ ወዲያው መንፈቀ ሌሊት ሲሆን ቅዳሴ ተቀድሶ ይቈረባል፡፡ ከዚያም ዕጣነ ሞገር = በዕጣን ፈንታ ቅኔው ተቁሞ ሠርሖተ ሕዝብ = የሕዝብ ስንብት ከሆነ በኋላ ለመፈሰክ ሕዝቡ ወደየ ቤቱ ይሔዳል፡፡ #የትንሣኤ_አከባበር_በዕለቱ ፠ ሕዝቡ በየቤቱ፣ ካህናቱም ከቤተ ክርስቲያን በየአካባቢው ባህል በተለይ አክፋዮች መጀመሪያ ቅባት አጥቶ የሰነበተ ሆድ እንዲለሰልስ የተሞቀ የተልባ ጭልቃ ይጠጣና የሹሮ ወጥ በቅቤ፣ በአይብ፣ የበረታም በዶሮ ወጥ፣ ወይም በበግና በከብት ሥጋ ወጥ ይገድፋል፡፡ ፠ በእርጎ፣ በአይብ የተደራረበ እንጀራ በግፍልፍል የሚገድፉም አሉ፡፡ በአንዳንድ የሰሜኑ ሀገራችን ደግሞ የተልባ፣ የኑግና የሱፍ ጭልቃ ከማር ጋር ታሽቶ ከተጠጣ በኋላ በእርጎ፣ በአይብ፣ በወተት፣ በቅቤና ድልህ በተቀባ እንጀራ ይገድፋሉ፡፡ ፠ በዋልድባ ገዳም ከዓመት ዓመት ምግቡ ቋርፍ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ለትንሳኤ በዓል ከሃገራችን ካሉ ቦታዎች በተለየ ሁኔታ በዓሳ ይገድፋሉ፤ ዓሳው ሲዘጋጅም ሙሉ ለሙሉ ሆድ ዕቃው ሳይወጣ ተወቅጦ ነው፡፡ ፠ ሊነጋጋ ሲልም ከጾሙ አጋማሽ ጀምሮ ወንዱ ለእርድ የሚሆነውን ሰንጋውን፣ ሲቀልብ፣ በጉን ፍየሉን ሲሞክት ዶሮውን ሲመርጥ፣ ሲገዛ ሲለውጥ ሰንብቶ ነበርና በግልም በኅብረትም ያ ይታረዳል፡፡ ፠ ሴቶችም ቅቤውን ሲያነጥሩ፣ በርበሬውን ሲደልሁ፣ ለእንጀራና ዳቦ የሚሆነውን ዱቄት ሲያዘጋጁ ለጠላ የሚሆነውንም እኸል ሲያሰናዱ አይቡን በልዩ ልዩ ቅመም መጣጣ ሲያደርጉና ባዶ ማለትም ወገሚት የተባለውን በሽንኩርት፣ በጤና አዳም፣ ጣዕሙ እንዳይለወጥ ሲቀምሙ፤ እንደ መከለሻ፣ ጥቁር አዝሙድ የመሳሰሉትንም ሰንብተው ዝግጅቱ ተከናውኖ ነበር፡፡ ፠ ጧትም ይህ የመግደፊያ ዝግጅት በየቤታቸው ለሌላቸው ድኾች በየመንደሩ እየተዞረ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባለ ከሥጋውም፣ ከአይቡም፣ ከቅቤውም ከመጣጣሙም፣ ከእርጐውም ይታደላል፡፡ ፠ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች፤ ለወላጅ አባትና እናት፤ ለወንድምና ለእኅት ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥና የድሮ ወጥ፣ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡፡ ፠ የቻለም ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ እየተገባባዘ በዓሉን በፍስሐና በሐሴት ሲያከብር ይከርማል፡፡ ‹‹ሕያው ተንሥአ እሙታን (ሕያው ከሙታን ተነሣ፡፡)›› /ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem

❤3👍3😢1