እንኳን ለጥንተ ትንሣኤ እና ለጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳቹህ
#እግዚአብሔር_ዓለምን_ከፈጠረበት_ጥበቡ_ይልቅ_ከድንግል_ማርያም_ሰው_ሆኖ_ዓለምን_ያዳነበት_ጥበቡ_ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም፤
፠ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረበት ጥበቡ፤ 7ቱ ዕለታትን፣ 20ው ዓለማትን፣ 22ት ሥነ ፍጥረታትን ካለመኖር ወደ መኖር፤ ከፈጠራቸውም ላይ አሻሽሎ አስገኘ
፠ ዓለምን ያዳነበት ጥበብ፤ሰማይና ምድር የማይወስኑት፤ ከጽርሐ አርያም በላይ ጠፈሩ፥ ከበርባሮስ በታች መሠረቱ፥ ለአድማስና ለናጌብ ዳርቻቸው የኾነ አምላክ በአጭር ቁመትና
በጠባብ ደረት ለሰው ልጅ ቤዛ ለመሆን ወደ ፈጠረው ምድር በፈጠረው አካል ላይ የሰማይ ዙፋኑን ሳይለይ መጥታል
#ብስራትና ፅንሰት በአንድ ዕለት ነው የተከናወኑት፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ በማህፀነ #ማርያም የተፀነሰው ልክ ቅዱስ #ገብርኤል ‹‹ ትፀንሺያለሽ ›› ሲላት እርሷም “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ” ‹‹ እንደቃልህ ይደረግልኝ ›› ብላ በተቀበለች
ጊዜ የእግዚአበሔር ቃል በማህፀነ ድንግል ማርያም ተፀነሰ፡፡ አብ አፀናት መንፈስቅዱስ አነፃት
ወልድ በተለየ አካሉ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተዋሐደ (ሉቃ 1፤33)፡:
እመቤታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕት መቅደሱ ናትና ፤ ነገሩን አስቀድማ ጠንቅቃ ትወቅ ሲል ቅዱስ ገብርኤልን ልኮታል ( ሉቃ ፩፥፳፮ -፳፷)
ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡:ቅዱስ ገብርኤልም ብርሃናዊ መልአክ መሆኑን ለማጠየቅ እና የሥላሴ ማደርያ መኾኗን ለማስረዳት 3 ጊዜ ተመላልሷል ፡፡
ሉቃ 1 ፥33 ማቴ 18፥ 16
#ሊቀ_መላእክት ቅዱስ ገብርኤልም በደስታ ተውጦ ለመላእክት ጉባኤ “በቅድስት ድንግል ማርያም የይሁንታ ቃል ምክንያት ዓለም ዳነች” ብሎ የምስራች አላቸው፡፡ ነቢዩ ሕዝቅኤል “… በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ” (ሕዝ.1፡26) ብሎ እንደገለጠው እግዚአብሔር አምላክ ለመላእክት በሰው ምሳሌ ተገልጦ ይታያቸው ነበር እንጂ እርሱን ገጽ በገጽ አያዩም ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ገብርኤል የፀንሰቱን ነገር ለመላእክት በነገራቸው ጊዜ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ቃል ሰው በመሆን በአካል ሊያዩት እንደተቃረቡ ተረድተው ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማያውቅ ታላቅ የሆነ የደስታ ዝማሬ ዘመሩ፡፡
በዚያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ደስታቸው ድርብ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ደስታቸው የሰው ልጆች መዳን ሲሆን ሁለተኛው ግን አምላካቸውን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ለማየት በመብቃታቸው ነበር፡፡
#_1 ቅዱስ ገብርኤል ለማብሰር የተመረጠውም
#በማብሠር የታወቀ ስለሆነ(መሳ 13) ሊቃ 1 #_2 #የስሙ ትርጓሜ ሥራውን ስለሚገልጽ ፡፡ ገብር ሰው ማለት ሲሆን ኤል ደሞ አምላክ ማለት ነው ስለዚህ አምላክ ወሰብእ ማለት ነው (አምላክም ሰውም) ስለዚህ የአምላክ ሰው የመሆንን ምሥጢር እንዲያበስር ተልኳል ፡፡
#_3.#ሳጥናኤል አምላክ እኔ ነኝ ብሎ መላእክትን ባሸበራቸውጊዜ ‹‹ነቁም በበህላዌነ እስከ ነአምሮ ለአምላክነ (የፈጠረን ይህ አይደለምና ፈጣሪያችንን እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንጽና ) ብሏል፡፡ ይህን ያለበት አንደበቱ የአምላክን ሥጋዌ ለእመቤታቸን ለመንገር አብቅቶታል ::
ይህ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት አምላክ በማኅፀነ ማርያም ያደረበትን የፅንሰቱን በዓል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት በማኅሌት፣ በቅዳሴ፣ በትምህርት መጋቢት ፳፱ ቀን ስታስብ ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት ውስጥ አንደኛውና የመጀመሪያው አድርጋ ታስበዋለች፡፡
ይህ በዓል በፆም ወቅት ሰለሚውል መጋቢት 29 ቅዱስ አበው በሰሩልን ሥርዓት መሠረት ልዋጭ በዓሉን ታኀሣሥ 22 ብሥራቱን በድምቀት እናከብረዋለን ፡፡
ፍትሐ ነ አነድምታ አ.15
#ጥንተ ትንሣኤ
«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግስ ሲሆን፡፡ «ትንሣኤ» ማለት = መነሣት፥ አነሣሥ፥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቆል በሥጋ ከሞተበት ቀን መጋቢት 27 ፤ ሦስተኛው ቀን መጋቢት 29 ነውና ይህች ዕለት ቅድስት ትንሣኤው ውሎባታል በከበረች ልዩ የሆነች ትንሣኤው የዓለም ድኀነት ሆነ ፡፡ በረቀቀ ጥበቡ በዚህች ቀን
ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል ፡ያመ
የጽንሰቱ በዓል ተደርቦባት ነው እንጂ ልናስበው የሚገባ ትልቅ ዕለት ነው ::
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/finotehiwotee

👍6❤3
#ሆሣዕና (#በዓለ_ተፂዕኖ) (#የፀበርት_እሑድ) #ወሥርዐተ_ማኅሌት
፠ የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን፤ የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፤
፠ በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን ትርጕሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን፤ አንድም መድኀኒት›› ማለት ነው፡፡ በትንቢተ ዘካርያስ ላይ በአህያ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (በግእዙ ተፂዕኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ኢየሩሳሌም በክብር) ስለሚል በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል
ከጥንት ጀምሮ በዋነኛነት ‹‹የተፂዕኖ በዓል›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ዘንባባ በግእዙ ፀበርት እየተባረከ ስለሚሰጥ ‹‹የፀበርት እሑድ›› ይባላል፡፡
፠ በዚህ ዕለት ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡... ቤተ ፋጌ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫ ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡
በምስጢሩም የአዳምን ልጆች ከዲያብሎስ ቁራኝነት ሊፈታ እንደ መጣ ለማጠየቅ ነው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት አመጡ፤ እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣
2ቱን ምዕራፍ (ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ) በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጫላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡
#ለምን_ጌታችን_በአህያ_ውርንጫ_ተቀምጦ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_ገባ
* ቀድሞ በነቢያት ዘመን ጸብዕ (ጥል) በሆነ ጊዜ በፈረስ ተቀምጠው፥ የጦር ዕቃ ይዘው፥ ዘገር ነቅንቀው፥ ጦር ሰብቀው፥ (ነጋሪት እያጎሰሙ፥ መለከት እያስነፉ) ይታዩ ነበር፤ ዘመነ ሰላም፥ ዘመነ ምሕረት በሆነ ጊዜ ደግሞ በአህያ ተቀምጠው፥ መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በነቢያት ሥርዐት ‹‹ዘመነ ሰላም ይዤላችሁ›› መጣሁ፤ በ7ቱ መስተጻርራን /ተጣልጠው የነበሩ/ (በሰውና በእግዚአብሔር ፣ በሰውና በመላእክት፣ በሥጋና በነፍስ፣ በተገዘሩት በሕዝበ እሥራኤልና ቆላፍ በሆኑት በአሕዛብ መካከል) የነበረው ጠብ ማብቃቱን ለመግለጥ እንዲሁም በነቢያት የተተነበየውን ሊፈጽም፤ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ 117፥25-26 ‹‹በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡›› ብሏል፤ ነቢዩ ዘካርያስም በትንቢቱ በአህያ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር ‹‹የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡›› /ዘካ. 9፥9/፡፡
* ጌታችንም ኢየሩሳሌምን ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላሟን አውጆላታል፤ በሌላ አንቀጽም ከተማይቷን እየተመለከተ አልቅሶላታል፡፡(ስለ ሰላምሽ የሚሆነውን አንቺስ ብታውቂ … … ፡፡) /ሉቃ. 19፥24/፡፡
* የተዋረደች እንስሳ (አህያም) በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ መቀመጫ አደረጋት፤ ሸክም ያቆሰላት፥ ዱላ የሰለቻት፥ ዕረፍት የናፈቃት ‹‹ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜ ቀላል ነው›› ያለ ንጉሥ ተቀመጠባት፡፡
#ለምን_የዘንባባ_ዝንጣፊ (ፀበርት)፤ (የቴምር ዛፍ ዝንጣፊና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ) ይዘው #ዘመሩ
* በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ደቀ መዛሙርቱና በግራና በቀኝ የነበሩ ሕዝቦችም ‹‹እንኳን አንተ የተቀመጥክባትም አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም›› እያሉ ግማሹ ልብሱን፥ ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ አነጠፉለት፤ ክብሩንና መድኀኒትነቱን ገለጡ፡፡
* አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፣ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሃገሯን ሊወር የመጣውን ሆሎፎርኒስ የተባለ የአይሁድ ንጉሥ በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው አመስግነው ነበር፤ በዚያ ልማድ ጌታችንንም ዘንባባ ይዘው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፥ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፥ ሆሣዕና በአርያም›› /መዝ. 8፥2፣ ሉቃ. 19፥38/ እያሉ አመሰገኑት፤ ዘመን የተቈጠረለት፥ ምሳሌ የተመሰለለት፥ ትንቢት የተተነበየለት፥ ምሥጢር የተመሠጠረለት የዳዊት ልጅ፤ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን መሰከሩ፡፡
* አይሁድም ሕፃናት ሲያመሰግኑ ሰምተው በቅንአት በታወረ ልቦናቸው ‹‹ዝም አስብላቸው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ አፍ ምስጋና ለራስህ አዘጋጀህ›› /መዝ. 8፥2/ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በሌላም አንቀጽ ዝም በሉ እያሉ ሊያስቆሙ ሲሞክሩ የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው አመስግነውታል፤ ይህንንም ተመልክተው አፍረዋል፡፡
* አንድም ዘንባባ እሾኻም ነው የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤
* አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤
* አንድም ዘንባባ ረጅም (ልዑል) ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ አንጥፈው ተቀብለውታል፡፡
* አንድም ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ አንተም የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ፤
* ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ፤
* ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ፡፡
፠ ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በዚያ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በመቆጣት የለዋጮችን ገበታ እየገለበጠ አስወጣቸው፡፡
፠ ይህ በዓል ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ እኛም የዕለቱን ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡
፠ ታሪኩ በነቢያት መጻሕፍትና በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)፨

❤6👍1
በዓለ ሆሣዕና 2013 ዓ.ም
ከፎቶ ማስታወሻ
ከፎቶ ማስታወሻ
❤6👍2