የ3 ዓመት ሕፃን የፈላ ውኃ በያዘ ድስት ውስጥ ቢጣል ምን ይፈጠራል ብላችሁ ታስባላችሁ?
በ3ኛው ክፍለ ዘመን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ቅድስት ኢየሉጣና የ3 ዓመቱ ልጅዋ ቅዱስ ቂርቆስ ቢሸሹም፣ በጨካኙ ገዢ አሌክሳንደር እጅ ወደቁ።
እናት ኢየሉጣ ሃይማኖቷን ለመካድ ፈቃደኛ ባለመሆኗ
የ3 ዓመት ሕጻን ልጇም "እኔ ክርስቲያን ነኝ፤ ድንጋይና እንጨት ለሆነው ጣዖት አልሰግድም" እያለ በመመስከሩ
ገዢው ተናዶ ሐምሌ 19 ቀን የፈላ ውኃ በያዘ የብረት ድስት ውስጥ እንዲጣሉ አዘዘ
ነገር ግን ሕፃኑ ሲጸልይ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ እሳቱን አቀዘቀዘው፤ ከዚህ የፈላ ውኃ ሁለቱም ምንም ሳይሆኑ ወጡ።
ከድንጋይ ይልቅ የጠጠረ ልብ ያለው አሌክሳንደር ግን በመጨረሻም አንገታቸውን በሰይፍ በመቁረጥ የሰማዕትነት አክሊል እንዲቀበሉ አደረገ።
በመሆኑም ይህ ቀን የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የተገለጠበት ቢሆንም በዓሉ ግን የቅዱስ ቂርቆስ እና የእናቱ የኢየሉጣ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ዕለት ነው።
ለዚህም መጽሐፈ ስንክሳር ይገልጣል። እንዲሁም መልአክ ዘበምድር የተባለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የሐምሌ 19ኝን ክብረ በዓል ቀለም ለእነዚህ ለሰማዕታቱ ብቻ ወስኖ አመስጥሮታል።
ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
(ይወዳጁን)
👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c

ከ90 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው ቀን...
ዕለቱ ከበድ ያለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ልብን
የሚያስጨንቅ ስሜት ያዘለ ነፋስ ይነፍሳል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን
1928 ዓ.ም.!
ቁመታቸው ረዘም ያለ - ፊታቸው ዘለግ ያለ - መልካቸው
ጠየም ያለ - ዐዋቂነታቸው እና ትሕትናቸው ከገጻቸው
የሚነበብ - ጥቁር እና በጭቃ የተለወሰ የጵጵስና ካባ የለበሱ
ታላቅ አባት ችሎት ፊት በአደባባይ ቀርበዋል - አቡነ ጴጥሮስ!
“አቡነ ቄርሎስ የጣሊያንን መንግሥት ገዢነት ሲቀበሉ እርስዎ
ለምን አመጹ? ለምንስ ብቻዎን አፈንጋጭ ኾኑ?" ሲል ዳኛው
ጠየቃቸው፡፡
ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት እና ሀገሩን እና
ሃይማኖቱን እንደሚያፈቅር በሚያስታውቅ አንደበት “አቡነ
ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን
የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ! ኃላፊነትም
ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚኽ ስለሀገሬና
ስለቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለኹ፡፡ ከዚኽ በቀር ለእናንተ ችሎት
የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን
እናገራለኽ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችኹ አውቃለኹ፡፡
ስለዚኽ በእኔ ላይ የፈለጋችኹትን አድርጉ ግን ተከታዮቼን
አትንኩ" አሉ፡፡
ይኽንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት
ታዝዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልዕክት
አስተላለፉ!
“አረማዊ የኾነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን
ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን
ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ
ለመሥራት ስላልመጣ ለዚኽ ግፈኛ አትገዙ!!! ስለውድ
ሀገራችኹ - ስለቀናች ሃይማኖታችኹ ተከላከሉ!!! ነጻነታችኹ
ከሚረክስ ሙታችኹ ስማችኹ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው
ክብርን ታገኛላችኹ!!! የኢትዮጵያ ሕዝብ ኾይ! ለጠላት
እንዳትገዛ አውግዣለው!!! የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን
ብትቀበል የተረገመች ትኹን!!! በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ
ስም የተረገመች ትኹን!!!"
ወዲያውም የእረፍታቸው ሰዓት መድረሷን ስለተረዱ
ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ ምንም ፍርኃት
በገጻቸው አይነበብም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ የሚያነበው
ጣልያናዊ ዳኛ ግን ልቡ በሽብር ተሞልቶ ፍርዳቸውን ሲያነብ
ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ የፈረዱባቸውንም ዳኞች ጸልየው
በመስቀል ባረኳቸው፡፡
ከዚያም በስምንት ጥይት ተኩሰው መቷቸው፡፡ ነገር ግን
በስምንቱ ጥይት ባለመሞታቸው ሌላ ወታደር ተጠርቶ በሦስት
ጥይት የራስ ቅላቸው ላይ መትቶ ገደላቸው፡፡
አስክሬናቸውንም ማንም እንዳይወስድ በምሥጢር ተደብቀው
ተቀበሩ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም በየቤቱ ለቅሶ እና ዋይታ
ኾነ፡፡
በዛሬው ዕለት ሰማዕትነትን የተቀበሉት የአባታችን የብጹዕ
አቡነ ጴጥሮስ ረድኤት በረከት ይደርብን! ጽናታቸው አርአያ
ኾኖን እስትንፋሳችን ለኾነችው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን
በእምነት እና በጽናት እንድንቆም ያድርገን!! አሜን!!!
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇

+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++
ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።
ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ7 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።
አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።
የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!
(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.

ታላቁ ዲማ ከፈራቸው ታላላቅ ስመ ጥር ሊቃውንት መካከል አንዱ ናቸው መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፡፡ መልአከ ብርሃን ተወልደው ያደጉት በዚሁ በዲማ ነው፡፡ በመጽሐፎቻቸው መቅድም ላይ እንዳስቀመጡት “እኔ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የተወለድኩበትና ያደግሁበት የተማርኩበት ሀገሬ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዲማ ጊዮርጊስ መልአከ ብርሃን ተብየ የተሸምኩበት ብቸና ጊዮርጊስ ነው” ይላሉ፡፡ መልአከ ብርሃን አድማሱ የተወለዱት ነሐሴ ፩ ቀን ፲፰፻፹፭ ዓ.ም እግዚአብሔርን ይፈሩ ከነበሩት ደግና ርኅሩኅ ከሆኑት ከአባታቸው ከአቶ ጅነበሬ አዲሱ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ወለተ ማርያም ኃይሉ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በእነማይ ወረዳ በታላቁ ዲማ ነው፡፡ እናታቸው ወለተ ማርያም በጀርባቸው አዝለዋቸው እያሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ባሕታዊ “ይህ ያዘልሽው ልጅ ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም ነው እግዚአብሔርም የመረጠው ነውና በጥንቃቄ አሳድጊው በሰዓቱም ወደ ትምህርት ቤት አስገቢው” አሏቸው፡፡ ወለተ ማርያምም “እግዚአብሔር ያለው መቸም አይቀረም” በማለት ልጃቸውን “ያለው” ብለው ስም አወጡላቸው በተባሉት መሠረትም ያለው ጀንበሬ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ እዚያው ከተወለዱበት ታላቁ ገዳም ዲማ ጊዮርጊስ እንዲማሩ አስገቧቸው፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉንም የቤተክርስቲያናችንን ዕውቀት ሁሉ ከዚሁ ከታላቁ ገዳም ከዲማ ጊዮርጊስ ቀስመዋል፡፡ ከባህታዊው አባ ወንድሙ ከፊደል እስከ ዳዊት ከተማሩ በኋላ ወደ አጎታቸው ሊቀ ጠበብት ክንፉ ሂደው ጾመ ድጓ፣ ምእራፍ፣ ድጓ፣ ዝማሬ መዋስእት እና ቅኔን ተምረዋል፡፡ ከዚያም በዚሁ ገዳም በዲቁና፣ በመዘምርነት፣ በቅኔም፣ በመምህርነትም አገልግለዋል፡፡ ያለው ጀንበሬን አባታቸው “አድማሱ” ብለው ይጠሯቸው ስለነበር ያለው በሚለው ስም እስከ ፲፱፻፬ ዓ.ም ሲጠሩበት ከቆዩ በኋላ ሊቅነታቸው እየጨመረ በሁሉ ዘንድ ታዋቂ ሲሆኑ በአባታቸው የወጣላቸው ስም እየገነነ እንደመጣ በቅርብ የሚያውቋቸው ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሠረት እኔም መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ እያልኩ እጽፋለሁ፡፡
መልአከ ብርሃን አድማሱ ሁሉንም ትምህርታቸውን ከዲማ ከተማሩ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው አስተምረዋል ታላቅ ታሪክንም ፈጽመዋል፡፡ መልአከ ብርሃን በቁም ጽሕፈት በጣም የታወቁም እንደነበሩ ይነገራል፡፡ መልአከ ብርሃን ከትውልድ ሀገራቸው ዲማ ለመጀመሪያ ጊዜ በግንቦት ፲፪ ቀን ፲፱፻፬ ዓ.ም ለቀው ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሂደው የጻፉትን የአርባዕቱን ወንጌል ንባብ በዚያ ሸጠው ለስንቃቸው እና ለጉዟቸው የሚሆን ገንዘብ ይዘው ወደ አዲስ አበባ አቀኑ፡፡
አዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከነበሩት ወልደ ሥላሴ ከሚባሉት የብሉይ ኪዳን መምህር ዘንድ ትርጓሜ ዳዊትን፤ መጻሕፍተ ሰሎሞንን እና ትንቢተ ኢሳይያስን ከቀጸሉ በኋላ በወጡ በዓመታቸው ወደ ትውልድ ሀገራቸው ዲማ በግንቦት ወር በ፲፱፻፭ ዓ.ም ተመለሱና ከመምህር ወልደ ጊዮርጊስና ከመምህር እንግዳሽት ዘንድ ቅኔና ልዩ ልዩ መጻሕፍትን ተምረዋል፡፡ ከዚያም ወደ ደሴ በ፲፱፻፮ ዓ.ም ሄደው ከመልአከ ገነት አፈወርቅ ፍትሐ ነገሥትን እንዲሁም ከቀለም ቀንዱ መምህር አካለ ወልድ ዘቦሩ ሜዳ ዘንድ በመሄድ ሐዲሳትንና መጻሕፍተ ሊቃውንትን ተማሩ፡፡ ከዚያም በ፲፱፻፱ ወደ ጎጃም ደምበጫ ተመልሰው ከብሉዩ ሊቅ ከመምህር አለቃ ገብረ ኤልያስና ከቅኔው ሊቅ ከመልአከ ሰላም ገብረ ማርያም ዘንድ ብሉያቱን ሲቀጽሉ ቅኔውን ሲያስፋፉ እስከ ፲፱፻፲፰ ዓ.ም ድረስ በዚያ ቆዩ፡፡
ከዚህ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ዲማ በመመለስ እስከ ፲፱፻፳፬ ዓ.ም ድረስ በቅኔ መምህርነት ሲያገለግሉ ቆዩ፡፡ መልአከ ብርሃን እስከዚህ ዘመን ድረስ መተዳደሪያቸው መጻሕፍትን በቁም ጽሕፈት በማዘጋጀት እርሱን በመሸጥ በሚያገኙት ገንዘብ ነበር፡፡ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም አካባቢ የልጆቻቸውን እናት ወ/ሮ አለሚቱ እሸቴ (በኋላ እማሆይ አለሚቱ እሸቴ) ን አግብተው ሰባት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በ፲፱፻፳፭ ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡
****
የመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ታላላቅ ሥራዎች፡-
*
⚡️ ቤተክርስቲያናችን በመናፍቃን ስትደፈር እንደ ውርደት ይቆጥሩት ስለነበር ሌላው ዝም ቢል እንኳ እኔ ግን ዝም አልልም በማለት አቶ ዘመንፈስ የተባለ መናፍቅ “ተግሳጽና ምክር” በሚል ምንፍቅናውን ሲዘራ “ኰኲሐ ሃይማኖት”ን ዳግመኛም ዶ.ር አባ አየለ ተክለሃይማኖት የተባለ ካቶሊካዊ መነኩሴ “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ባሕርያት የምታምነው ትምህርት” ብሎ ክህደትን ሲጽፍ “መድሎተ አሚንን” በመጻፍ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት እንዲያፍሩ አድርገዋል፡፡ በዚህም በተለይም በመድሎተ አሚን የካቶሊካውያኑ ቅርንጫፎች የሆኑትን “ቅብዐትን” እና “ጸጋን” ድራሻቸው እንዲጠፋ በማድረጋቸው ታሪክ ሲዘክራቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን በመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ መልስ የተቀበሩትን እነዚህን ምንፍቅናዎች ዛሬ በአዲስ መልኩ በአቡነ ማርቆስ እንዲያንሰራሩ ተደርጓል፡፡
⚡️ የመጨረሻ ልጃቸውን “ምኅርካ ክርስቶስ አድማሱን” ከሞት አስነሥተዋል፡፡ ትናንት የነበርህ አምላክ ዛሬም እንዳለህ አምናለሁ፡፡ “አዝዝ በቃልከ ይሕየው ወልድየ ፤ ልጄ እንዲድን በቃልህ እዘዝ” በማለት ነበር ልጃቸውን ከሞት ያስነሡት፡፡ ይህ ሙትን የማንሣት ቅድስና በአንድ ጀንበር የሚመጣ እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ምርጥ የጸሎት አባት ሊቅ ቅዱስ እንደሆኑ በዚህ መረዳቱ አይከብድም፡፡
⚡️ ጥሩ የንባብ ችሎታ ነበራቸው፡፡ መልአከ ብርሃን ምግብ እየተመገቡ እንኳ በአንድ እጃቸው መጽሐፍ ይዘው ያነብቡ ነበር፡፡ “እባክዎ ዓይንዎ ይጎዳል” ሲሏቸውም “ለመጽሐፍ መመልከቻ ያልሆነ ዓይን ይፍረጥ” ይሉ እንደነበር ይነገራል፡፡ የሚገርመው ነገር መልአከ ብርሃን አድማሱ ለንባብ የሚመች የተለየ ቦታ ሳይኖራቸው ሳሎን ላይ ቁጭ ብለው በተመስጦ ያነብቡ ነበር፡፡ በጣም የሚያዘወትሩት የሃይማኖት መጻሕፍትን ቢሆንም የታሪክ እና የምርምር ጽሑፎችን የግለሰብ ታሪክ መዛግብትን ልብወለዶችንም ያነቡ ነበር፡፡
⚡️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከራሷ ልጆች ሊቃነ ጳጳሳትን መሾም አለባት፡፡ ከግብጽ በሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት አገልግሎታችንን መፈጸም አልቻልንም፡፡ በቋንቋችን የሚያስተምሩ ሊቃነ ጳጳሳትን ከሐገራችን ልጆች መሾም አለብን የሚለውን ታላቁን ሀሳብ ከማመንጨት ጀምረው ጉዳዩን ዳር እስከማድረስ ድረስ ታላቅ የሆነ ተጋድሎን ፈጽመዋል፡፡ ይህም ተጋድሏቸው ዛሬ ፍሬ አፍርቶ ከመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ እስከ አሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ድረስ ደርሷል፡፡
⚡️በቤተክህነቱ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳድር ላይ በመማክርት አባልነት አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ይህ አስተዳድር ቀርቶ በመልአከ ብርሃን አድማሱ የታሪክና ድርሰት ክፍል ሹም የሊቃውንት ጉባዔ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡
⚡️ በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም - ፲፱፻፶፱ዓ.ም በንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ተሹመው በቤጌ ምድር፣ በወሎ እና በትግራይ ጠቅላይ ግዛቶች በመዘዋወር ከባድ እና አስቸጋሪ የሚባሉትን የፍርድ ውሳኔዎች ሁሉ በሚገባ ያለ አድልዎ በቀላል ጥበባዊ ዘዴ ወስነዋል፡፡ ከዚህም አገልግሎታቸው በኋላ በ፲፱፻፶፱ዓ.ም በጥሮታ ከዚህ ሥራ ለቅቀዋል፡፡

⚡️ በልዩ ልዩ ድርጅቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና በብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያዎች እየተገኙ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያስተላልፉ ነበር፡፡ ከተለያዩ አቅጣጫዎችም የሚቀርቡላቸውን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች በመመለስም ይታወቃሉ፡፡
⚡️ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መጽሐፍትን እንዲመረምሩ እና እንዲተረጉሙ፣ በቤተክርስቲያናችን የሚነሡትን ዐበይት ችግሮችም እንዲመለከቱ ከጥሮታ በኋላ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ተጠሩ፡፡ በዚህም አጋጣሚ ብዙ ሊቃውንትን የማግኘት እድሉን አገኙ፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ታሪክ አልባ እንዳይሆኑ ሥራቸውም ተቀብሮ እንዳይቀር በማሰብ እነርሱን የሚዘክር መጽሐፍ “ዝክረ ሊቃውንት” በሚል ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ ይህ መጽሐፍም የታተመው እርሳቸው ከዐረፉ በኋላ በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም ነው፡፡
⚡️ ስለኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ሰዎችም የበኩላቸውን ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት “የኢትዮጵያ የጥንት ቅርስ ጥበቃ ድርጅት” ባደረገው እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፈው በጎጃም ጠቅላይ ግዛት አካባቢ ባሉ አድባራትና ገዳማት ያሉ መጻሕፍትን በድርጅቱ ከሚጠበቀው በላይ መረጃውን በማሰባሰብ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙትን መጻሕፍት በማይክሮ ፊልም በሚያነሣበት ወቅት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በብቸና አውራጃ ያሉትን ምርጥና ጥንታውያን መጻሕፍትን በማስነሣት በኩል ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ በዚህም ሥራ ተሳታፊ ነበሩ፡፡
⚡️ በዐቢይ ጾም ወቅት በኢትዮጵያ ሬዲዮ በመገኘት ተከታታይ ትምህርቶችን ሰጥተዋል ይህ ተከታታይ ትምህርታቸውም “ሐዲስ ሰውነት” በሚል መጽሐፍ ታትሟል፡፡
⚡️ መጻሕፍትን መመርመር ይወዱ ነበር፡፡ መጻሕፍትን ዝም ብለው ከመቀበል ይልቅ የያዙትን ፍሬ ነገር በሚገባ መረዳትን ይመርጡ ስለነበር ያገኙትን ሁሉ መጽሐፍ መመልከት ይወዱ ነበር፡፡ በዚህም በጣም አስቸጋሪ እና በቀላሉ ለመረዳት የሚከብዱ ቃላትን በመተርጎም ይታወቁ ነበር፡፡ ለዚህም መድሎተ አሚንን እና ኰኲሐ ሃይማኖትን ያነበበ ሰው ሁሉ ምስክር ይሆናል፡፡
⚡️ዲማ ጊዮርጊስ ለተቋቋመው የጀግኖች ማኅበር አባል ሆነውም አገልግለዋል፡፡
⚡️ ትጉህ፣ ትእግስተኛ፣ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ፣ የጸሎት አባት፣ ቅድስናን ከሊቅነት ጋር ያስተጻመሩ፣ ለሚጠይቃቸው ሁሉ መልስ የሚሰጡ ታላቅ አባት፣ አስተዋይ፣ ሐገር ወዳድ፣አርቆ አሳቢ፣ በጥልቀት መርማሪ፣ እግዚአብሔርን ፈሪ፣ ሰውን አክባሪ፣እውነትን ደፋሪ፣ ሰውን ሁሉ አስደሳች፣ የሰውን ክብር ጠባቂ ነበሩ፡፡
ታዋቂውን ሊቅ አለቃ አያሌውን ወደ አዲስ አበባ ወስደው በማስተማርም ለቤተክርስቲያናችን ሌላ እርሳቸውን የሚተካ ታላቅ ሊቅ አበርክተዋል፡፡ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው አጎታቸውም ናቸው፡፡ ስለ አለቃ አያሌውም በትህትና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሲናገሩ “እኔን ማንም ይተካኛል እኒህን ዓይነ ሥውር ሊቅ ግን ተንከባከቧቸው እርሳቸውን የሚተካ መምህር ወደፊት አይገኝምና” እንዳሉም ይነገራል፡፡
በአቡነ ፊልጶስ ተመርጠው አድማሱ ጀንበሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሉት ሹመት “መጋቤ ምሥጢር” የሚል ነበር፡፡ ይህ የሹመት ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጣቸው ለአድማሱ ጀንበሬ ሲሆን ሹመቱ በእንደዚህ ዓይነት ሰው መጀመሩ ዕድለኛ የሆነው ተሿሚው ሳይሆን ራሱ ሹመቱ ነውም ተብሏል፡፡ ይህ ሹመትም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእርሳቸው ከተሰጠ በኋላ ሌሎችም እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ ከአድማሱ ጀንበሬ በፊት “መጋቤ ምሥጢር” የሚል ሹመት የለም ነበር ማለት ነው፡፡
በ ፲፱፻፳፯ ዓ.ም ደግሞ በንጉሠ ነገሥቱ መልካም ፈቃድ የተቀበሉት ሁለተኛው ሹመት “ሊቀ ጠበብት” የሚል ነበር፡፡ ይህን ሊቀ ጠበብትነት መዓርግ ይዘው ከአዲስ አበባ ወደ ሀገራቸው ዲማ ተመልሰዋል፡፡
መልአከ ብርሃን ተብለው የተሾሙበት ብቸና ጊዮርጊስ ደብር
በ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም ደግሞ በታላቁ ብቸና ጊዮርጊስ “መልአከ ብርሃን” ተብለው ተሾሙ፡፡ እስካሁንም ድረስ የሚጠሩት በዚሁ ስማቸው ነው፡፡ በመጽሐፎቻቸውም ውስጥ የሚጠቅሱት ይህንኑ መዓርግ ነው፡፡
🔥 መጋቤ ምሥጢር ሊቀ ጠበብት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የሀገራችንን ሊቃውንት ስም ለማስታወስ እና ሥራቸው ከመቃብር በላይ እንዲሆን ለማድረግ እንቅልፍ አጥተው ታሪከ ሊቃውንትን አሰባስበው “ዝክረ ሊቃውንት” የተሰኘው መጽሐፋቸውን በማዘጋጀት ላይ ሳሉ ነበር በድንገተኛ የአእምሮ ድካም (ስትሮክ) ሀምሌ ፳፬ ቀን ፲፱፻፷፪ ዓ.ም ይህ መጽሐፋቸው ሳይታተም ያረፉት፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበትም በእግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ “ፍሬ ሊቃውንት” የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፍ ግን ቀብራቸው ቅድስት ሥላሴ ተፈጽሟል ይላል፡፡

ለአርባ ቀን መታሰቢያቸው አለቃ ተገኝ የገጠሙላቸው ግጥም።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c
በዛሬው ዕለት የተመረቃችሁ ውድ የሰንበት ትምሕርት ቤታችን አገልጋዮች
ወንድም ሣሙኤል እና እኅት ሠናይት ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ አላችሁ ከዚህ በላይ ፍሬያችሁን ያሳየን ትላለች።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c
ወንድም ሣሙኤል እና እኅት ሠናይት ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ አላችሁ ከዚህ በላይ ፍሬያችሁን ያሳየን ትላለች።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c
ከ4 ዓመት እስከ 6 ዓመት ላሉ ሕጻናት "ተስፋ ቤተክርስቲያን" በሚል መጠሪያ በዘመናዊው የKG ሕጻናት የትምሕርት አሰጣጥ ሂደት በሀገረ ስብከታችን ሰ/ት/ቤታችን ቀዳሚ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህም ሰ/ት/ቤታችን ለቅድመ መደበኛ ማስተማሪያ መጽሐፍትን እንዲያዘጋጅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በመመረጡ የተሰጠውን ኃላፊነት በመወጣት በአዘጋጅነት የተሳተፈበት የቅድመ መደበኛ "ሀ" እና "ለ" መጽሐፍትን በቀጣዩ የትምሕርት ዘመን በተግባር ላይ በማዋል በእትም ላይ ውሏል።
በዚህ አገልግሎት ላይ ጊዜያችሁን እና እወቀታችሁን ለበረከታችሁ የሰ/ት/ቤታችን የመጽሐፍ ዝግጅት ኮሚቴ አገልጋይ መምህራንን እያመሰገን ድካማችሁ ፍሬ ላይ እንደዋለ ለማብሰር እንወዳለን።